በአሜሪካዋ መዲና የሚገኘዉ የፈርስት ሒጅራህ ፋዉንዴሽን በትላንትናዉ እለት የኢፍጣር፣የአንደነትና ለዉድ የኢስላም ልጆችና ለህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አጋርነት ያሳየበትን ዝግጅት አዘጋጅቶ ነበር። በዝግጅቱ ላይ ህጻናት፣ታዳጊዎች፣ወጣቶች ጎልማሶችና አረጋዉያን በነቂስ መሳተፋቸዉ ነዉ የታወቀዉ። ይህ ዝግጅት ድንበር ዘለል የሆነዉ የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ከፋፋይ ረጅም እጅን በመግፋት የአንድነት ተምሳሊትነቱ በተለያዩ አገራት ይቀጥል ዘንድ አስተዋጽኦ ያደረገም ነዉ ይላሉ የዝግጅቱ ታዳሚዎች። አዘጋጆቹ ዝግጅቱ የተሳካ እንደነበር ያስረዳሉ። በዚህ ዝግጅት ከመቶ ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ መዋጣቱ የታወቀ ሲሆን ይህም በመላዉ ዲያስፖራ የሚገኘዉ ሙስሊም ማህበረሰብ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብሮችን ለሰላማዊ ትግሉ ማበርከት እንደሚችል ጠቋሚም ነው ተብሏል። “ከነጻ ያነሰ ብይን አንቀበልም!” በማለት ያስተጋቡት ፈርስት ሒጅራዎች የድምጽችን ይሰማን መርሃ ግብሮች በመተግበር ከኮሚቴዉ ጎን እንደሚቆሙ ቃል ኪዳን ገብተዉ ነበር። ዝርዝር ዘገባዉን በስፍራዉ የተገኘዉ ባልደረባችን ሳዲቅ አህመድ አዘጋጅቶታል።
The post በአሜሪካዋ መዲና የሚገኘዉ የፈርስት ሒጅራህ ፋዉንዴሽን በትላንትናዉ እለት ለዉድ የኢስላም ልጆችና ለህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አጋርነቱን አሳየ appeared first on Zehabesha Amharic.