ሰበር ዜና! ትንቅንቁ አሁንም በመረረ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው!!
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የጥቃት አድማሱን አስፍቶ በአማራ ክልል አዋሳኝ ከተሞች ላይ በሰፈረው የሕወሓት ጦር ላይ ጥቃት እየፈፀመ እንደሚገኝ ተሰምቷል!!
ጀግኖች የአርበኞች ግንቦት ሰባት አርበኛ ታጋዮች በትናንትናው ዕለት /ሰኔ 26/2007 ዓ.ም የአማራ ክልል አዋሳኝ በሆኑ እና ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቦታዎች ማለትም ጓንጋ አሳግላ እና ማይ እምቧ ላይ ከ 24ኛ እና 44ኛ ክፍለ ጦር ጋር ለሶስት ሰዓታት የዘለቀ ምድርን ያናወጠ ውግያ አድርገዋል፡፡
…
የአርበኞች ግንቦት 7 ጀግኖች የነፃነት ታጋዮች ጓንጋ አሳግላ ላይ ከቀኑ ስድስት ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት ከ24ኛ ክፍለ ጦር ጋር ተፋልመው በትንሹ 15 ወታደሮችን ገድለው 10 አቁስለዋል፡፡
በተጨማሪም ጀግኖች አርበኛ ታጋዮች ማይ እምቧ ላይ አመሻሽ ከ11 ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ለተከታታይ ሁለት ሰዓታት ህወሓት መራሹን 44ኛ ክፍለ ጦር በጥይት በመቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በዚህ እጅግ በጣም መራራ የሆነ ፍልሚያ በትንሹ 70 ወታደሮችን ገድለው 60 ያቆሰሉ ሲሆን በአካባቢው የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ጠርናፊ የሆነው ኮማንደር ካህሳይ እንደሻው፣ የ44ኛ ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዦች ሻለቃ ሐለቃ እና መቶ አለቃ በቀለ ተስፉ ከተገደሉት ውስጥ ይገኙበታል፡፡
ሰሞኑን በትግራይ፣ እንዲሁም በትግራይና በአማራ ክልል አዋሳኝ የሆኑ ልዩ ልዩ ቦታዎች
የተጀመረው ጦርነት በቅርብ ቀን ወደ ሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተስፋፍቶ የሚቀጥል መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከወዲሁ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይገልፃል፡፡
The post ሰበር ዜና – የአርበኞች ግንቦት 7 ጀግኖች የነፃነት ታጋዮች ጓንጋ አሳግላ ላይ ከቀኑ ስድስት ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት ከ24ኛ ክፍለ ጦር ጋር ተፋልመው በትንሹ 15 ወታደሮችን ገድለው 10 አቁስለዋል appeared first on Zehabesha Amharic.