Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በወያኔ እብሪት- ወደ ጦርነት –ይገረም አለሙ

$
0
0

 

«ሕዝቦች የነጻ ምርጫ እድል ከተሰጣቸው ከምርጫ ሳጥን ወደ ጥይት ማጮህ የሚቀርብላቸውን ጥሪ አይቀበሉም »

                                                                                       አብርሀም ሊኒከን

tplf-addis-620x310

ተኩስ አልባው ትግል የህዝብን የሥልጣን ባለቤትነት ከማረጋገጥ ይልቅ የአንባገነኖችን አገዛዝ ለማራዘም ከጠቀመ፣ዴሞክራሲን ከማምጣት ይልቅ ለጭቆና መስፋፋት ከረዳ፣ የህግ የበላይነትን ማስከበሩ ቀርቶ ለህገ ወጥነት ምቹ ሁኔታ ከፈጠረ ፣ወዘተ ለታጋዮቹ የሚኖረው ምርጫ ሶስት ነው፡፡ የመጀመሪያው አባልና ደጋፊያቸውን መስዋእት እያስከፈሉ  በድል አልባ ትግል የገዢውን እድሜ እያራዘሙ ተቀዋሚ እየተባሉ በዚሁ መቀጠል፡ ሁለት በድል አልባ ትግል ዜጎችን ለመስዋእትነት አንዳርግም ለገዢዎች እድሜ መራዘምም ምክንያት አንሆንም ብሎ ከትግሉ ገለል ማለት፤ ሶስተኛው ደግሞ ሰላምን ለጠላ ሕግ ለማይገዛው በጠመንጃው ታምኖ በእብሪት ለታብየው በሚገባው ቋንቋ ምላሹን እንስጠው ማለት ነው፡፡ሰሞኑን የተሰማውም ይሄው ነው፡፡

ወያኔ በቃል እንጂ በተግባር የማያውቀውን ሰላማዊ ትግል ለማለማመድ 24 ዓመታት የተደረጉ ጥረቶች መክነዋል፡፡ በእነዚህ አመታት   አያሌ ኢትዮጵያውያንን አጥተናል፣እኛ ሰላማዊ ትግል ብለን ጠመንጃ ሳይሆን ብዕር ጨብጠን፣ ጫካ ሳይሆን ከተማ ሆነን፣ ታጋይ ተጋዳላይ አሰልፈን ሳይሆን ሕዝብን አሰልፈን ሳንገድል እየሞትን ብለን ስንታገል ወያኔ በጠመንጃ የተገኘ ሥልጣን በጠመንጃ ይጠበቃል  ሥልጣን ወይንም ሞት ብሎ ጉልበት ከሥርዓት እየተጠቀመ ገድሏል አሁንም እየገደለ ነው፡፡ ለሥልጣኔ ያሰጉኛል ያላቸውን በተለያየ መንገድ ከትግሉ አስወግዷል ፣የማይቻለውን ሁሉ ችለው የቀጠሉትን ደግሞ በሀሰት ወንጅሎ በግፍ አስሮ አሰቃይቷል እያሰቃየ ነው፡፡ ታፍነው ተወስደው አድርሻቸው የጠፋውን በድብቅ ተገድለው የተጣሉትን ሀገር ጥለው የተሰደዱትን ቤት ይቁጠራቸው፡

ወያኔ ለሥልጣኑ ቡራኬ ለማግኘት የሚያካሂደውን የይስሙላ ምርጫ የምር ምርጫ አድርገው በማያውቀውና ሊለምደው ባልቻለው  ምርጫ ተወዳድረው  ያሸነፉትን  ምርጫ ማሸነፍ ዘር ማጥፋትና ሀገር ክህደት ሆኖ በዚህ ወንጅሎ አስሯል፣ለመሸነፌ አስተዋጽኦ አድርገዋል ያላቸውን ወጣቶች በመላ ሀገሪቱ ገድሏል በገፍ አስሮ አሰቃይቷል፡፡ ሕዝብ እየተራበ የሀገሪቱን ሀብት ንብረት ስልጣኑን ለማስጠበቅ ይጠቀምበታል፤ ኢትዮጵያውያን ይህን ሁሉ ችለን ከዛሬ ነገ እያልን ቢብሰንም ብሶት የወለደው ብለን ባለመነሳታችን ወያኔ እብሪቱ ከፍቶ ማን አለብኝነቱ ገደብ አጥቶ በዛው ልክ ፍርሀት እያርበደበደው መቶ በመቶ አሸነፍኩ ያለበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ነገር ግን አላማው ረግጦ መግዛት ዒላማው ሰላሳና አርባ አመት በሥልጣን መቆየት ነውና መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎም ያስራል ይገድላል፡፡ በዚህ መልክ ያልተገባ መስዋዕትነት እየተከፈለ የወያኔን እድሜ ማራዘምና የእኛን ስቃይ ማስቀጠል የነገውንም ተስፋ ማጨለም ከዚህ በኋላ  ተመራጭ ሊሆን አይችልም፡፡  ስለሆነም የወያኔ ማሰርና መግደል የኢትዮጵያውያንም ሞትና  ስቃይ እድሜውን እያራዘመለት ከሆነ ነገሩ ተገልብጦ ገዳይ ሟች ሟች ገዳይ ሊሆን ግድ ነው፡፡

ነገር ግን ይህ ድርጊት ( ጦርነት)እንደ ወያኔ አባት እናትን ወንድም እህትን እየገደሉ የሀገር ሀብት እያወደሙ የሚሸለልበትና የሚፎከርበት ሳይሆን በጥቂት የወያኔ እብሪተኛ መሪዎች አንባገነናዊ ተግባር ምክንያት  ወደው ሳይሆን ተገደው መርጠው ሳይሆን ተገፍተው የገቡበት መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ የትግሉ አራማጆችም ይህን በግልጽ ማስረዳት ብቻ ሳይሆን አቋማቸው ማድረግ አለባቸው፡፡ አለበለዚያ ወያኔዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ገድለው ባህር አቋርጦ ድንበር ተሻግሮ የመጣ  ወራሪ ጠላት የገደሉ ያህል ይፎክሩ እንደነበረው መሆን ይመጣል፡፡ ይህ ደግሞ ለትግሉ ስኬትም ሆነ  በድሉ ማግስት ለሚፈለገው መረጋጋት ጥሩ ሁኔታ አይፈጥርም፡፡ የዶ/ር ብርሀኑን አባባል ልዋስና መቼም በምንም ሁኔታ እኛ ወያኔን መሆን የለብንም፡፡

ከተኩስ በሻገር ያሉትን አማራጮች ሁሉ በመዝጋት የሌላው ኢትዮጵያዊ ጣት ቃታ መሳብ አይችል ይመስል ከህውኃት በስተቀር ዱር ቤቴ ማለቱን ተኩሶ መግደሉን ሌላው ኢትዮጵያዊ አያውቅበት ይመስል ወንድ ከሆናችሁ እኔ በመጣሁበት መንገድ ኑ እያለ በመመጸደቅ የትግሉ አቅጣጫ እንዲለወጥ ያደረገው ወያኔ በመሆኑ ጦርነቱ ለሚያደርሰው ሰብአዊም ሆነ ቁሳዊ ጥፋት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂው እሱ ነው፡፡ይህም ሆኖ አማራጭ በማጣት በተገባበት ጦርነት የሚሞተው ኢትዮጵያዊ የሚወድመውም ሀብት የኢትዮጵያ በመሆኑ የነጻነት ታጋዩ  ገደልኩ ማረኩ ብሎ እንደ ወያኔ ከበሮ የሚደልቅና የሚያቅራራ እንደማይሆን እንገምታለን፡፡ እንደውም በእያንዳንዱ ወታደራዊ ውሎ ዜናና መግልጫ ለሆነው ሁሉ ከልብ እናዝናለን ቢባል መልካም ይመስለኛል፡፡ የመከላከያ ሰራዊቱንም በጅምላ የወያኔ ሰራዊት አድርጎ ማየት ተገቢ አይሆንም፤የመምረጥ እድል ያገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በምርጫ 97 ቅንጅትን መምረጣቸውን ማሰብ ብቻ እውነታውን ለመገንዘብ የሚያስችል ይመስለኛል፡፡

ሳይፈለግ በወያኔ እብሪት በተገባት በዚህ ጦርነት ሊደርስ የሚችለውን ጥፋትን ለመቀነስ ሀለት ጎን ለጎን መሄድ የሚችሉ እንደውም የአንዱ እውን መሆን ለሁለተኛው መሳካት አመቺ ሁኔታ የሚፈጥር አማራጮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው የጦሩ አባላት እኔ የኢትዮጵያ ሰራዊት እንጂ የወያኔ ተገጋዳላይ አይደለሁም በማለት ለጥቂት የወያኔ ሹማምንት ስልጣን ሲሉ ወገናቸውን ላለመግደልና እነርሱም ላለመሞት ወስነው በሚችሉት መንገድና አጋጣሚ ራሳቸውን ከውጊያ ውጪ ማድረግ፡፡ ከቻሉም የአንባገነኖችን እድሜ ለማሳጠር አኩሪ ተግባር መፈጸም፡፡ ሁለተኛው ጦርነቱ ተባብሶ የሰው ህይወትም ሆነ የሀገር ሀብት በከፍተኛ ደረጃ ከጠፋ በኋላ መንግሥታትም ሆኑ አለም አቀፍ ድርጅቶች ለማደራደር የሚያደርጉት መሯሯጥ አንድም ጉልበት ከተፈተሸ በኋላ የሚደረግ ጥረት ከባድ ስለሚሆን ሁለትም ተሳክቶ እርቅ ቢፈጠር የአንድ ሰው ህይወት አንኳን የማይመልስ በመሆኑ አሁኑን ጥረት ቢጀምሩ፡፡

ብረት አንስቶ ዱር ቤቴ ያለን መናቅ ምን እንደሚያስከትል ከወያኔ በላይ የሚያውቅ ያለ አይመስለኝም፡፡ ከወያኔ ጋር ለመደራደር ቀርቶ ስሙን አንኳን ለመጥራት ይንቅና ይጸየፍ የነበረው ደርግ በስተመጨረሻ ድርድርን ለምኖም ሊያገኘው አልቻልም፡፡  ለድርድር እጅ መስጠት ሽንፈት ሲመጣ ሳይሆን ገና በሙሉ ጉልበት ላይ ባሉበት ወቅት ነው፡፡ ጉልበት ዘላቂ ገዢነትንም ሆነ በክብር ከሥልጣን መውረድን አያስገኝምና፡፡ ሌላው አባቶች ጋን በጠጠር ይደገፋል እንደሚሉት ትግሉ ግዜም ብዙ መስዋእትነትም ሰይፈጅ ለድል መብቃት እንዲቻል የወያኔ አገዛዝ በቃ የሚል ሁሉ ትንሽ ትንሽ ጠጠር በማኖር ጋኑን መደገ

The post በወያኔ እብሪት- ወደ ጦርነት – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>