ከቀናት በፊት የወጣው አዲሱ የመስፍን በቀለ አስረሽ ምቺው ዘፈን መልዕክቱ አነጋጋሪ ነው:: ግጥሙን ይዘንላችኋል ከዘፈኑ ጋር አብረው ያንብቡት::
ስንቱ የጨዋልጅ ስታብጂ እያበደ
ከአንቺ ጋር እስክስታ ገጥሞ ተዋረደ
ቁንጅና ሰቶሻል አፍላ ጉልበት ያንቺው
ምን አለብሽ እና አስረሽ አስረሽ ምችው
ካልተገረፈ ገላ እንደክራር ድምፅ አያወጣም
ምችው ደስ ይላል
የተኛው ሁሉ ነቅቶ እስኪረበሽ በይ አስረሽ
ምችው አስረሽ ደርበሽ……
እየተደለቀ ሲርገፈገፍ ገላ (አስረሽ ምችው ይሁና)
ዳር ቆሜ አልልሽም ምችው እንደ ሌላ ……
ያንችማ ትከሻ ያንችማ ጭፈራ (አስረሽ ምችው..
እንደ ፀበል ፃድቅ ይደርሳል በተራ……
ስላልወደድኩት ዋ…
ይህንን ነገር እውይ እዋ..
ነብይ አትበይኝ ዋ…..
ታይቶኝ ብናገር እውይ እዋ..
ጣል አርገሽ ተይው ዋ…..
ለ ፍቅር ብለሽ እውይ እዋ…
ለ ጀምበር ዕድሜ ዋ….
ቶሎ ለሚመሽ እውይ እዋ…
ሆላ እንዳያምሽ እጅሽን ዞሮ
ቀስ አርገሽ ምችው ይህን ከበሮ
ያዥና ምችው ወይ መተሽ ያዥው
ጀግናም ይረግፋል ስትወዘውዥው
አስረሽ ምችው ይሁና……!!!
(ሁለተኛ ዙር ግጥም)
የዘፈንሽው ሁሉ ደንቆ እየተወራ
ይታጨድልሻል ፍቅር እንደ አዝመራ
የ ተወጠረውን ክሩን አርግቢና
ቅኝቱን ቀይረሽ ሞክሪ እንደገና……
( ተሳትፎ)
ግጥም ደራሲ:- ኑረዲን ኢሳ
ዜማ……….:- መስፍን በቀለ
The post በውስጠ ወይራ ተናግሮ አናጋሪ የሆነው አዲሱ የመስፍን በቀለ “አስረሽ ምቺው” ዘፈን (ግጥሙን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.