ዳኞች እስከዛሬ አቃቤ ህግ ያቀረባቸውን የሐሰት ምስክሮች ቃል በዝርዝር አንብበዋል!
ነገ ደግሞ የወኪሎቻችን የመከላከያ ምስክሮች ቃል በችሎቱ ተነቦ ውሳኔ ይሰጣል ተብሏል!
ረቡእ ሰኔ 24/2007
የዛሬው ችሎት ተጠናቋል!
እስካሁን በነበረው ሂደት ዳኞች በወኪሎቻችን ላይ እስከዛሬ የቀረቡ የሐሰት ምስክሮችን ቃል ሲያነቡ መቆየታቸው የታወቀ ሲሆን በነገው እለት ደግሞ ወኪሎቻችን ያቀረቧቸው ምስክሮች ቃል ተነቦ ወደውሳኔ የሚኬድ ይሆናል፡፡ እውነተኛ ፍትሕን የምንጠብቀው ከጌታችን አላህ በመሆኑ ሁላችንም በዱዓ እንድንበራታ አደራ እንላለን!
-
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
The post የኮሚቴዎች የዛሬው ችሎት ተጠናቋል! – ድምጻችን ይሰማ! appeared first on Zehabesha Amharic.