Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

መስፍን በዙ! የጥላሁን ገሠሠ ሌጋሲ ወራሽ ወይስ አደር-አፋሽ ?

$
0
0

tamagne beyeneስሜነህ ባዘዘው

አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ እዚሁ አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ለሽልማት መታጨቱን ስሰማ በጣም ነበር ደስ ያለኝ። ይገባዋል!!! ብያለሁ።
ወዲያው ደግሞ በሽልማቱ ሥነ ሥርዓት ላይ “ታማኝ በየነ ሽልማት አይገባውም!” የሚሉ ሁለት የሱማሌ ወጣቶች ተቃዉሟቸውን ሲያሰሙ የሚያሳይ የቪዲዮ ክሊፕ አየሁና ገረመኝ። ተቃዋሚዎቹ “እንዳለቀ ቢራ ጠርሙስ” አንገት አንገታቸው ተይዞ እዳሪ ሲጣሉ ስመለከት ደግሞ ልቤ እስኪፈርስ ሳቅኩ። ከእንዲህ አይነቱ ውርደት ይሰውራችሁ….

የሱማሌዎቹ የተቃውሞ ምክንያት፤ የክልላችን ፕሬዝዳንት አሜሪካ በመጣበት ወቅት ተቃውሞ አደራጅቶ ያዋረደብን ታማኝ ነው ! የሚል ነበር ። ጉዳዩ ግን ሌላ ነው …
በዚሁ ክሊፕ ላይ ሱማሌዎቹ ወጣቶች ልብሳቸው የታኘከ እስኪመስል ተጨመዳደው ከአዳራሽ ከወጡ በኋላ ይህን ተቃውሞ ያቀነባበረው መስፍን በዙ የሚባለውን የወያኔ መሽሩፍ ተቀባይ ሰው እንደ ናዝሬት በርሜል እየገፉ ሲያስወጡት ተመለከትኩ። መስፍን የሚሉት ሰው ለምን ይሄን አደረገ? ለሚለው ወደ ኋላ ልመለስበትና በተቃውሞው ይዘትና በተቃዋሚዎቹ ማንነት ዙሪያ ጥቂት ልበል።

መስፍን በዙ የሱማሌ ወጣቶችን ቀጥሮ ለተቃውሞ ያሰማራው ሌላ ተባባሪ ስላጣ ይመስለኛል። ታማኝን ለመሸለም በታደመ ወገን መሃል ቆሞ በታማኝ ላይ ተቃውሞ ማቅረብ ምን ሊያመጣ፤ ምን ሊያስከትል እንደሚችል ከወዲሁ የተረዱ ሌሎች የወያኔ ቅጥረኞች መስፍንን ሊተባበሩት አልፈለጉም። ጎመን በጤና ብለውታል ።እናም “ጣጣ” የለንም የሚሉትን የሱማሌ መርቃኞች የበርጫ በጥሶ አሰማራቸው። እንዳሰቡት ሳይሆን ከጣጣም ጣጣ ገጠማቸው።

ይህ ሰው(መስፍን በዙ) የጥላሁን ገሠሠ የመጨረሻ የትዳር ጓደኛ (የመጀመሪያም ብቸኛም አለመሆኗን ለማመልከት ነው) ወንድም በመሆኑ ብቻ የጥላሁን ገሠሠ ሌጋሲ ወራሽ ሆኖ ለመታየት የሚያደርገው ሩጫ በጣም የሚገርም ነው። ሲጀመር፤ ጥላሁን የሕዝብ ልጅ ነው።ወራሹም አሳታዋሹም የኢትዮጵያ ህዝብ ነው።ሲቀጥል፤ የግድ የቅርብ ወራሽ ይኑር ከተባለም በመጀመሪያ ረድፍ የሚቀመጡት ልጆቹና የልጆቹ እናቶች በሙሉ ናቸው። ከመጀመሪያ የትዳር ጓደኛው እስከ መጨረሻዋ ..
መስፍን በዙ በመጀመሪያው ረድፍ ካልተቀመጥኩ ብሎ የሚሟዘዘው ለምን እንደሆነ የማይገባኝም ለዚህ ነው። የጥላሁን ገሠሠ የመጨረሻ ሚስት ወንድም መሆኑ ልዩ የአደር-አፋሽ ወራሽነት መብት ያሰጠው ይሆን?

mesfin-bezu-tg-tv ድሮ..! ድሮ..! ልጅ ሆነን ቆርኪና ብይ ደርድረን ስንጫወት፤ ተጫዋቹ ሁሉ በየተራ ይሞክር ይሞክርና እያንዳንዱ እንደችሎታው ያገኘውን(የበላውን) ይወስዳል። በመጨረሻ
ላይ የሚሞክረው ግን በሙከራው ካገኘው ውጭ ያደረውን(ሳይበላ የቀረውን) ቆርኪ ሁሉ ሰብስቦ ይወስዳል። እናም “መስፍን በዙ የጥላሁን ሌጋሲ አደር-አፋሽ ወይስ ወራሽ? ” የሚለውን ጥያቄ ለርዕስነት የመረጥኩትም ለዚሁ ነው። ሌላ ምን ልበል ….?
ለነገሩ ይህ ሰው የወያኔ ቅጥረኛ መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች በገሃድ በማሳየቱ አካሄዱና እንቅስቃሴው ሁሉ ምንና ለምን እንደሆነ ለማንም ይጠፋዋል አልልም። ይሁንና እንደ መብት ካየነው ያሻውን መደገፍ መብቱ ነው። መብቱ ያልሆነው በጥላሁን ገሰሰ ስም በከፈተው የቴሌቪዥን ጣቢያ መነገድ ነው። የጥላሁን ቤተሰቦች(ልጆቹ) ቢያንስ የቴሌቪዥን ጣቢያውን ስም እንዲለውጥ ማስደረግ አለባቸው የሚባለውም ለዚህ ነው።

ጥላሁን የህዝብ ነው ስንል። በጥላሁን ጉዳይ ሁላችንም ያገባናል ማለታችን ነው። ስሙ እንዲከብር እንጂ ታሪኩ እንዲመዘበር አንፈቅድም። ጥላሁን እንባ ከጉንጮቹ እየተቀዳ ሃገሩን ዘክሯታል። ሃገሩም በክብር ትዘክረው ዘንድ ይገባል። ሃገር ማለት ደግሞ ህዝብ ነውና በጥላሁን ጉዳይ ኢትዮጵያዊው ሁሉ ያገባዋል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ የአብራኩ ክፋይ የሆኑት ልጆቹ የበለጠ ያገባቸዋል። ለዚህም ነው የጥላሁን ልጆች ይህን “አደር አፋሽ” አድብ! የማይሉት ለምንድነው? የሚለው ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚነሳው።
አደር-አፋሹ መስፍን ስለ ታማኝ በየነ ብዙ ብዙ ይላል። ታማኝ ጥላሁንን በድሏል ሲል ይወተውታል። እኛ ያየነው ደግሞ ጥላሁን ገሠሠ በህይወት ሳለ “ታማኝ ከልጆቼ የማለየው ልጄ ነው” ሲል ለልጆቹ መመስከሩን ነው። የጥላሁን ገሰሰ ልጅ ንጹህ ብር ጥላሁን አባቷ የሰጣትን የጣት ቀለበት ለታማኝ በየነ አሳልፋ ስትሰጥ የመሰከረቺውም ይህንኑ ነው። ቀለበቱም የታማኝና የጥላሁን አባትና ልጅነት ቃልኪዳን ነው።

አደር-አፋሹ ፦ የሚነግረን ግን በጥላሁን የመጨረሻ ሰዓት የአማችነት ቅርበት ስለነበረው ወራሽም፤ አስታዋሽም፤ዘካሪም፤መስካሪም እሱ እንደሆነ ነው ። እኔ ደግሞ

• መስፍን በዙ ሆይ! አንተ የጥላሁንን ስም አስነዋሪ እንጂ ዘካሪ አይደለህም።
• የጥላሁን ሌጋሲ አደር-አፋሽ እንጂ ወራሽም አትሆንም።እለዋለሁ፦ አደራ እናተም እንደኔ በሉት!
መስፍን በዙ ጥላሁንን በዊልቸር ላይ ከዋለ በኋላ ኮንሰርት ሊያሰራው ፈልጎ ታማኝ በየነ “ጥላሁን በዊልቸር ላይ ሆኖ አይዘፍንም፤ ይዝፈን ከተባለም አርቴፊሻል እግር ገብቶለት ይዝፈን እንጂ በፍጹም ለገንዘብ ተብሎ ይህ አይሆንም” በማለቱ ከዶላር ወዳዱ መስፍን በዙ ጋ እንደተጋጨ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች አጫውተውኛል፡፤
መስፍን በዙ አፍቅሮተ-ንዋይ የተጠናወተው ስለመሆኑ ደግሞ ለነፍሰ ገዳዮች ተቀጥሮ በሚሰራው ሞራል የለሽ ስራ መረዳት አይከብድም። እናም አደር-አፋሹ መስፍን ጥላሁን በዊልቸር ላይ ተቀምጦ ኮንሰርት ቢሰራ የሚገኘውን ዶላር እንጂ በጥላሁን ላይ ሊደርስበት ስለሚቸለው የሞራል ጉዳት ሊያስብ እንደማይችል ስለምረዳ ከታማኝ ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባቱም አይገርምም።
የእንጀራ ነገር ሆኖባቸው የወያኔ መንግስት በረጅም ሰንሰለት አስሮ ዲያስፖራ ውስጥ የለቀቃቸው ጥቂት የማይባሉ ውሾች የግንባር-ሥጋ ሆነው ሥርዓቱን በሚቃወሙ ወገኖች ላይ ሁሉ ለመጮኽ ሲሞክሩ በተለያዩ አጋጣሚዎች እያየን ነው። መስፍንም በታማኝ ሽልማት ላይ የሞከረው ነገር ከዚህ የተለየ አይደለም። ጌቶቹ የታሰረበትን ሰንሰለት አጠር ሲያደርጉበት የታማኝን ዱካ እየተከተለ ይጮሃል፤ ሰንሰለቱን አስረዝመው ሲለቁት ደግሞ ኢሳት ላይ ለመጮህ ይሞክራል(እንዳቅሚቲ)። ሰሚ አለው ወይ? ሌቦች ሊሰሙት ይችሉ ይሆናል። የውሻን ጩኽት ልብ ብሎ የሚሰማው ሌባ አይደል?

በመጨረሻም፦የጥላሁን ገሰሰ የአብራኩ ክፋይ ለሆኑት ልጆቹ አንድ ጥያቄ አለኝ? ለመሆኑ የአባታችሁን ከወርቅ ጸዳል የሚያበራ ታሪክና ስራ በአግባቡ መዘከር እንኳ ባትችሉ፤ ስሙ የፖለቲካ መነገጃ እንዳይሆን መከላከል ለምን አቃታችሁ? ችግሩ ምንድነው? ጥላሁንና ፖለቲካ ምን አገናኛቸው ብላችሁ ለምን አትጠይቁም?።ይህን “አደር-አፋሽ ወራሽ” ከጥላሁን ገሠሠ ራስ ላይ እንዲወርድ የማድረግ የደምም የሞራልም ሃላፊነት አለባችሁና ከተወቃሽነት ለመዳን አንድ ነገር ታደርጉ ዘንድ ይገባል እላለሁ። በተረፈ እመኑኝ የመስፍን በዙ ዕውቀትና ችሎታ አልባ ሩጫ ራሱንና ምናልባትም…. ከማዋረድ በስተቀር ማንንም አይጎዳም እያልኩ በነኚህ ስንኞች ልሰናበታችሁ!
ያቅበጠብጠዋል አዱኛ ርቆበት!
ማጀቱን ጠብቁ የእጅ አመል አለበት!

ቸር እንሰንብት
ስሜነህ ባዘዘው
semenehbazezew@gmail.com

The post መስፍን በዙ! የጥላሁን ገሠሠ ሌጋሲ ወራሽ ወይስ አደር-አፋሽ ? appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>