Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የታሰሩት 7 የዓየር ኃይል አባላት ነገ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸው ሰባት የአየር ኃይል አባላት ነገ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ይቀርባሉ፡፡
ethiopian airforce
አቃቤ ህግ በሰኔ 7/2007 ዓ.ም ባቀረበባቸው ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ ተከሳሾቹ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 32(1)(ሀ)ን እና የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 7(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በሽብተኝነት ተከስሰዋል፡፡ በክሱ የተመለከቱት ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው፣

1ኛ. መ/አ ማስረሻ ሰጤ……አድራሻ ድሬዳዋ
2ኛ. መ/አ ብሩክ አጥናዬ……. ›› ድሬዳዋ
3ኛ. መ/አ ዳንኤል ግርማ…… ›› ድሬዳዋ
4ኛ. ገዛኸኝ ድረስ………. ›› ድሬዳዋ
5ኛ. ተስፋዬ እሸቴ…….. ›› ምስራቅ ጎጃም
6ኛ. ሰይፉ ግርማ……. ›› አዲስ አበባ
7ኛ. የሻምበል አድማው…… ›› ምስራቅ ጎጃም፣ ናቸው፡፡

በአቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመለከተው ተከሳሾች ‹‹….ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል የማፈራረስ ዓላማ ይዘው ….በሽብር ድርጅት ውስጥ አባል በመሆንና በሽብር ድርጅት ተግባር ላይ ለመሳተፍ በማሰባቸው….›› የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

ተከሳሾች ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል በመክዳት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊያመሩ ሲሉ ባህር ዳር እና ጎንደር ላይ እንደተያዙ በክሳቸው ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የሽብር ድርጅት አባል በመሆን፣ ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በመመልመል እና መረጃ በማቀበል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
የአየር ኃይል አባላት ተከሳሾቹ በነገው ዕለት አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተከሳሾች ለወራት ከቆዩበት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ወጥተው በአሁኑ ወቅት ቂሊንጦ እስር ቤት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

The post ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የታሰሩት 7 የዓየር ኃይል አባላት ነገ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>