ጦቢያን ገረመው
ኃይሌ በዜግነት ምክንያት ፕሬዝደንት ይሆናል አይሆንም የሚባለው ቀልድ ጉንጭ አልፋ ነው፡፡ ወቅታዊ ቀልድም ይመስለኛል፡፡ መለስ ዜናዊና በረከት ስምዖን በፍላጎታቸውና በወፍዘራሽ የዜግነት ፍልስፍናቸው ‹ኤርትራዉያን› ሆነው ሲያበቁ ‹የጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያን› አንቅጥቅጠው እየመሩ ባሉበት ሁኔታ ኃይሌን ከኢትዮጵያዊነት አንጻር ማማት ለራሱም ሳያስቀው አይቀርም፡፡ ያ ዓይነቱ ጨዋታ የፖለቲካ ጨዋታ ነው፡፡ ‹በእውኑስ አሁን ኢትዮጵያ እየተመራች ያለችው በኢትዮጵያውን ነውን?› ብለንም መልሱ በአንድዬ እጅና በታሪክ ማሕጽን ውስጥ የሚገኝ ጥያቄ መጠየቅ እንችላለን – ለራሳችን፡፡ ኃይሌን በዜግነት ችግር ማንቀራበጥ ለወያኔ ድራማ ማጠናከሪያ ውሻል ማቀበል ይመስለኛል፡፡ አንደኛ ነገር ወያኔ ሕግ ማውጣት እንጂ ማክበር አያውቅበትም፤ እንዲያውም ያቆመው ሕግ የማይጠቅምና በረዳቶቹ ዘንድ ትዝብት ውስጥ የሚጥለው መስሎ ካየው በአንድ አዳር ያን ሕግ ተብዬ ሰርዞ በምትኩ ሌላ ሊያወጣ የሚችል የዘመኑ መንግሥታዊ ጨቡዴ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ እናም ችግሩ የዜግነት እንደማይሆን ይገባል ይልቁንስ፡፡ የኃይሌ ሀገርን መምራት ያለመቻል ችግር ያለው ከዜግነት አንጻር ሊመስለኝ አልፈልግም፡፡ ስንትና ስንት የፈጠጠ ጉድለት እያየንበት በዚህ ውሃ የማያነሳ ጉዳይ ጊዜ ማባከኑ በማይሠራ ሕግና ከ‹ተጻፈበት ቀለም› የዘለለ ዋጋ በሌለው ወረቀት ላይ በከንቱ ከመጯጯህ ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡
ከሰሞነኛ የሀገራችንና የዓለማችን አንዳንድ ሥራ ፈት የዜና ማዕከላት ወሬዎች መካከል አንዱ የኃይሌ ገ/ሥላሤ የሥልጣን አራራ መሆኑን በግሌ መረዳን ሳላሳውቅ ወደሁለተኛው አንቀጽ በመግባቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ እናም በግሌ – ጉዳዩ በቀጥታ እንደሚያገባው አንድ ኢትዮጵያዊ – ስለዚህ መካሪ ያጣ የገንዘብና የሥልጣን በሽተኛ ሰውዬ የሚሰማኝን ጥቂት ነገር ልበል፡፡ ያገባኛል ያልኩት ያለኝ ዜግነት አንድ ብቻ – ያም ኢትዮጵያዊነት ብቻ በመሆኑም ብቻ አይደለም፤ ያገባኛል ያልኩት ከኢትዮጵያ ውጪ ሌላ መመኪያና መኩሪያ ስለሌለኝ ብቻም አይደለም፤ ያገባኛል የምለው ይህን ሰው በሚገባ ስለማውቀው እንኳንስ ሀገርን የመሰለ ትልቅ ነገር ለመምራትና ቤቱንም በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያቅተውና በዘመናዊ የቴክሎጂ መሣሪያ ቢመረመር የጤናማነቱ ጉዳይ ቤተሰብ ለመመሥረት ጭምር የማያስቸለው እንደሚሆን በከፍተኛ ደረጃ ስለምጠራጠር ነው – የኔ ‹ሥራ› መጠራጠር ነው – የ‹አልጠረጠርም› ባይ ሥራ ደግሞ ጥርጣሬን ማስወገድ የሚያስችል ማስረጃ ማቅረብና ጠርጣሪን ማሣፈር ነው፡፡ አዎ፣ ደደብን ደደብ ካላሉት ቤተ መንግሥት ውስጥ በማያውቀው ነገር ገብቶ ይፈተፍታል ይባላል፡፡ ኃይሌ እውነቱን ይረዳው – ሕዝቡ አብጠርጥሮ ያውቀዋል – ከዋናው በር እስከመኝታ ቤቱ እናውቃለንና ዝምተኝነታችንን አይበዝብዝብን፤ በሀብቱ ወይም በወያኔያዊ ጥገኝነቱ ፈርተን የማንናገር ከመሰለው ተሳስቷልና ከአሁኑ ይታረም – ቢያንስ እሱና እሱን መሰል ቅሌታሞች እንዲፈነጥዙብን አንፈቅድም – እውነቱን በመናገር የእሱነቱን ማንነት እናጋልጣለን፡፡ እናም ዘመድ ካለው በጊዜ ይምከረውና የሥነ ልቦና ዐዋቂ/ሐኪም እንዲያክመው ያድርግ፤ አለበለዚያ ብዙ ጣጣ ውስጥ ይገባል፤ በእልህ የጀመረውን የዕብድ ውሻ መንገድ እገፋበታለሁ ካለ በግል ሕይወቱ ጭምር እየገባሁ በምዘባርቃቸው አንዳንድ ጉዳዮች በጣም ላስከፋው ከወዲሁ ቃል እገባለሁ፤ ከዛሬ ጀመርኩ፡፡ ይሉኝታ የሚሠራው ይሉኝታ ላለው ነው፤ ከፈጣሪ መንገድ እንዳፈነገጥሁ ይገባኛል – ጊዜ ካለኝ ንስሃ እገባለሁ እንጂ እንዲህ ያለውን መናኛ ስብዕና ከማጋለጥ አልመለስም፡፡ በሚሆነው አዝናለሁ – ምርጫ ግን የለኝም፡፡
እርሱ በኛ ላይ ከሚያደርገው ብልግና ይልቅ የአንድን ሰው ገመና ገሃድ ማውጣትና ሀፍረትን የሚያውቅ ከሆነ በሀፍረት እንዲሸማቀቅ ማድረግ ከተቆርቋሪ ዜጎች ይጠበቃልና የእርሱን ብልግና የምታውቁ ሁሉ ከእንግዲህ አትሳሱለት፤ ለይሁዳ የሚሳሳ አንጀት ሊኖረን አይገባም፡፡ ገና ለገና ባንዲራችንን – ሊያውም ኋላ ኋላ ላይ ኢትዮጵያን በትክክል የማይወክል የወያኔን ደባደቦ ባንዲራ እየመረጠ – አውለብልቧል ብለን እላያችን ላይ ሲያቀረሽ ዝም ማለት የለብንም፡፡ ይሄ ቆሻሻ የውሻ ልጅ በኢትዮጵያማ እንዲህ አይጨማለቅም! የሌሎቹ አነሰንና ደግሞ ይህ ማይም የወያኔ እግር አጣቢ በስማችን ይነግድብን? አላሙዲንና ኃይሌን ለመሰሉ ውሾች – በአእምሮ ሣይሆን በሆድ የሚያስቡ ደንቆሮ ዓሣሞች የሚያዝን ኅሊና የለኝም፡፡ ይቅርታና ምሕረት ሌላ ነው – ሆን ብሎ ሀገርን ለገንዘብና ለዝና እንዲሁም ለሥልጣን የሚሸጥ የዲያብሎስ አጋንንት ግን በምንም መንገድ ሊታለፍ አይገባም፡፡ ወያኔ ጋር እየተሸራሞጡና ሣምባን ከካሊፕሶ እየጨፈሩ ሕይወቴን የቀን ጨለማ እንዲውጠው ያደረጉትን ሁሉ – ማንም ይሁኑ ማን – ምንም ይሁኑ ምን – በተቻለኝ ሁሉ ሌላው ቢቀር በብዕር እዋጋቸዋለሁ፡፡ የነዚህን ሰዎች ግፍና በደል ለመሸፈን የሚሞክር ሁሉ የነሱ ተባባሪና ረዳት ነውና በበኩሌ ጥቁር ውሻ እንዲወልድ እራገማለሁ፤ እናም ተራገምኩ – ‹ይህን መልእክት ሆን ብሎ ያፈነ ወይ ያሳፈነ በዚህ መልእክት ውስጥ የተጠቀሰ የመርገምት ቃል ሁሉ በራሱና በትውልዱ ይድረስ!›፡፡ ከአሁን በኋላ ለኃይሌ የሚራራ አንጀት ያለውና ከእርሱ ጎን የሚቆም ሁሉ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተባብሮ ታሪክንና ሀገርን ለማጥፋት ከጥልቁ የእሳት ባህር የመጣ እንጂ ሕዝባዊ ወገናዊነት ያለው ጤናማ ዜጋ ሊሆን አይችልምና ኃይሌንና መሰል የወያኔ ቡችሎችን የማይቃወም ከወያኔ አንድ ነው – ስለሆነም እየመጣ ያለው የእሳት ዝናም በእርሱም ላይ ይዝነብ፡፡ ዕድሜውም ልክ እንደወያኔ ሁሉ አጭር ይሁን፤ የወያኔ ጣዕረሞት የርሱም ዕጣፋንታ እንዲሆን ፈቃደ መለኮት ይሁንልኝ – ‹እንዴት? በምን ምክንያት?› እያላችሁ አትጠይቁ (መጠየቅ ያስቀስፋል! Kidding … )- የወያኔ ዕድሜ በሰማያዊ የጊዜ አቆጣጠር በክፍልፋይ ሴከንዶች የምትቆጠር ናት – ወያኔ ጣር ላይ ነው፡፡ ጣር ላይ ያደረሰው የምሥኪኖች ዕንባና የሚዋኝበት የደም ባህር እንጂ የሌላ እንዳይመስላችሁ በተለይ አንዳንዶች በሰው ሥራ ላይ እንዳትመኩ – ማለቴ እንዳትኮፈሱ፡፡ የታዘዘው ኃይል ገና ተገቢ ሥራውን በቅጡ አልጀመረምና! (የነቢይነት ተሰጥዖ የለኝም – እምናገረው የውስጤ የሚነግረኝን እንጂ እንደሁሴን ጅብሪል ፊት ለፊቴ የተሰቀለ ጀንዲ ወይም አንሶላ ላይ የተነጠፉ ቃላተ ትንቢትን እያነበብኩ አይደለም – ስለዚህ ይህን ‹ስሜት ወለድ› ፈለገ-ሃሤት ጠቅሶ ሰውን ማስደሰት እንዳይቻል በማይም ቃሌ ገዝቻለሁ – ቆዳ ታጣቂውና አንበጣ በሊታው ዮሐንስ በባዶ እግሩ በበረሃ እየዞረ ምን ነበር ያለው? … (አሃ፣ ወዴት ጠጋ ጠጋ – የስሙኒ ቲማቲም በኪሎ 25 ብር ገዝተው ‹እየቆረጡ›ና የአንድ ብሩን ነጭ ፊያሽኮ ቪኖ በ45 ብር ገዝተው ‹እየኮመኮሙ› የምን ‹ጊዜው ቀርቧል፤ ንስሃ ግቡ› እያሉ በከተማ በረሃ ባስካርባ እየሄዱ መጮህ ነው?)ዓለም
ኃይሌ ፍጹማዊ ገብጋባ ነው – ከሚቋምጥለት ሥልጣን ጋር ምን አገናኘው እንዳትል – ትስስሩን እናገራለሁ፡፡ ገብጋባነቱ ደግሞ አንድና ሁለት ብቻ ሣይሆን ዓለም የምትጠቀማቸው ቁጥሮች አይገልጹትም፡፡ እንዴ! ለመሆኑ ኃይሌ ከነአካቴው ሰው ነው ማለትስ ይቻላልን? ቀጣዩን የአንዲት ቀን ገጠመኝ (anecdotal episode) እዩና ራሳችሁ ፍረዱ፡፡ ይህ ሰው ልምራችሁ ሲልም ይታያችሁ፡፡
ኃይሌ ይህን እውነተኛ ታሪክ እንዲያስታውስ ወዳጆቹ ንገሩት – የዚህን ደብዳቤም ግልባጭ ላኩለት፡፡ አንድ ወቅት ወደርሱ ቤት የሚገባ የውሃ ጉድጓድ ይቆፈር ነበር፡፡ የቁፋሮው ሥራ እየተካሄደ ሳለ ከሚቆፍሩት ወዛደሮች አንድኛው በናዳ ሕይወቱ ያልፋል፡፡ ያን ሬሣ ወዳገሩ (ወደጎጃም) ለመላክ ሥራውን ይቆጣጠር በነበረ አንድ ጓደኛየ አማካይነት የአካባቢው ማኅበረሰብ ገንዘብ እንዲያዋጣ ይጠየቃል፡፡ ቦታው ቦሌ ነው፡፡ ሁሉም የቻለውን ረዳ፡፡ ያ ከዚያን ጊዜ በፊት ኃይሌን ከቆንቋናነት አንጻር የማያውቀው ጓደኛየ ኃይሌን ከቤቱ አስጠርቶ ችግሩን ይገልጥለትና የረድኤት እጁን እንዲዘረጋ ይጠይቀዋል፡፡ ሀገርና ወገን ወዳዱ ኃይሌ፣ በኦሎምፒክ ሜዳዎች ባንዲራ ሲሰቀል የዐዞ ዕንባውን የሚረጨው አስመሳዩ ኃይሌ ወዲያውኑ ሃያ ብር ያወጣና ይሰጣል፡፡ ጓደኛየ ክው ብሎ ይደነግጣል – እዚያ አካባቢ የነበሩ ወዛደሮችና አላፊ አግዳሚ ተራና በጣም ድሃ ዜጎች ከዚያ ገንዘብ እጅግ የሚበልጥ ሰጥተዋልና የጓደኛየ ድንጋጤ የሞት ያህል ሆኖ አጽናኝ አስፈልጎት እንደነበር ከብዙ ዓመታት በኋላም አሁን ድረስ እያንዘረዘረው ያስታውሰዋል፡፡ ጓደኛየ ሲረጋጋ “ምነው ኃይሌ? ይህን ያህልማ እኔም አያቅተኝም፤ ከአንተ እኮ የምንጠብቀው … ይህ ልጅ እኮ ሲሰራ የነበረው ወዳንተ ቤት ይገባ በነበረ መስመር ነው፡፡ ካንተማ …” በማለት ሲወተውተው “እንዴ – ደም ተፍቼ እኮ ነው የማገኘው፤ መሬት ወድቆ እኮ አላገኘሁትም …”ብሎ እያጉመተመተ ቤቱ ይገባና ያቺን ሃያ ብር አስቀርቶ 200 ብር ይሰጠዋል፡፡ ኃይሌ እኮ ለጫማ ጠራጊ አንድ ብር ሰጥቶ ሃያ አምስት ሣንቲም መልስ ለመቀበል ዝርዝር እስኪገኝ ድረስ ግማሽ ሰዓት የሚጠብቅ እጅግ ሰፍሳፋና ‹ሀገርና ወገን ወዳድ› ብርቅዬ ዜጋ ነው፡፡ …
መስጠት አለመስጠት የግል ጉዳይ ነው – በመሠረቱ፡፡ እኔ የምለው ግን የዚህ ዓይነት የተለዬ ጋብሮቭ ኢትዮጵያን ልምራ ብሎ መናገር ሳይሆን ማሰብም አይገባውም፡፡ ይቅርና በወያኔ የውሸት ሥልጣን፣ በነገይቱ ኢትዮጵያም ቢሆን ማሰብም የለበትም፡፡ አመራር ከቸርነት ይጀምራል፤ ያለውን አለምክንያት ይበትን ወይ ይዝራ ማለት አይደለም – ግን እስከዚህን አስተዛዛቢና አንጀትን እስከወዲያኛው የሚቆርጥ ደረጃ የሚንገበገብ ሰው የቤቱንም ቆሎና ስኳር እየቆጠረ – የሞሰብ እንጀራ ላይ በሣር ምልክት እያደረገ በሻይሎካዊ ባሕርይ ሌሎችን ሰላም መንሳቱ አይቀርምና ወደ ቁጩም ሆነ ወደእውነተኛ የሥልጣን ወንበር ሊጠጋ አይገባውም፡፡ ከነብሂሉ ‹ሆዳም ሰው ፍቅር አያውቅም›፡፡ ገብጋባ ሰው ሆዳም ነው፤ ሆዳም ሰው ገብጋባ ነው፤ ገብጋባ ሰው ራሱን አይወድም፤ ገብጋባ ሰው ሰውን አይወድም፤ ገብጋባ ሰው ሀገር አያውቅም፤ ገብጋባ ሰው ፍቅር አያውቅም፤ ሆዳም ሰው ለሆዱ ሲል ሀገሩንም ወገኑንም ቤተሰቡንም ይሸጣል፡፡ ኃይሌ ለገንዘብና ለዝና ሲል ዓለምን ሸጦኣል ፤ ዓለምም ዘወርዋራ ናትና ፊቷን አዞረችበት – በመጨረሻም የሀብትና የዝና ጥሙ አንጎሉ ላይ ሲያናፍልበት ተመልክታ ብታስጠነቅቀውም ሊሰማት ባለመቻሉ እሷም ናቀችው – ከሕዝብ ጋር ሲላተም እያየችም አላዘነችለትም፤ በቂ የጥሞና ጊዜ ስጥታው ነበርና – ዓለም እንዲህ ነች፤ ሕይወትም፡፡ ተፈጥሮው ለአመራር ሳይሆን ገንዘብና ዝና ለማሳደድ ነው – ኃይሌ ገንዘብና ዝና አይጠግብም – እሱን መሰሎችም እንዲሁ፡፡ ኃይሌ ያቋቋመው በጎ አድራጎት አለ? ኃይሌ እንዲህ ያለ መልካም ነገር ለእገሌ ሠራ ተብሎ ያውቃል? በመጀመሪያ ለዕርዳታና ለመሰል የበጎ አድራጎት ሥራዎች ወደኃይሌ ቤት የሚሄድ ሰው ያለም አይመስለኝም – ሁሉም ስለሚያውቀው – ማን አፉን ያበላሻል? ለወትሮ ጅብ ነበር ወደማያውቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ የሚል፤ ዛሬ ደግሞ ዘመን ተዛወረና ደደቡና ማይሙ ኃይሌ በሚታወቅለት ለፍዳዳ አንደበቱ የሕዝብን የነጻነት ትግል ለማኮላሸት ከሀገር መሠሪ ጠላቶች ጋር ይለፋደድ ያዘ፡፡ ‹ልጅ አይውጣለት› ብዬ አልረግመው ነገር ሆኖብኝ ተቸገርኩ እንጂ ሰውዬው ብዙ ያናግራል፡፡ ብቻ እግዜር ይይለት – ዕድሜውንም እንደሚያመልክበት እንደመለስ ያድርገው! በቃ፡፡ ከጠሉ ወዲያ ልምምጥ የለም፤ የኛ ነበር – የኛነት አስጠላው – የዝና ሰይጣናዊ መንፈስ እኛን እንዲጠየፍ አስገደደው – በኛም ላይ ሽንቱንና ለከት ያጣ ቅርሻቱን ይለቅብን ጀመረ፡፡ ስለዚህ ሞቱን እንጂ ብልግናውን ላለማየት ቆርጫለሁ – ይሆናል፡፡ እንኳን ኃይሌ ጎብላላዎቹ ሐምሌና ነሐሴም ያልፋሉ፡፡
የኃይሌ ተፈጥሮ ሀገርን መምራት ሳይሆን ሮጦ የራሱን ስምና የሀገርን ስም ማስጠራት ነው፡፡ ሁሉም ሰው የየራሱ ተፈጥሮ አለው፡፡ ለመሪነት የራሱ የሆነ ግርማ ሞገስና የዕውቀት ደረጃ አለው – እንዳሁኑም የወያኔ ዘመንም ሆነ እንዳለፉት መሪር አገዛዞች ሳይሆን እንደጥንቱ አፍላጦናዊ ፍልስፍና፡፡ ማይሙ ኃይሌ ተፈጥሮ የለገሰችው ችሎታ መሮጥን ነው – በቃ፤ እግርና ጭንቅላት ደግሞ ለዬቅል ናቸው – በአቀማመጣቸው እንኳን ተቃራኒዎች መሆናቸውን ያጤኗል፡፡ ከተፈጥሮ ችሎታው ከሩጫ አልፎ መሪ አድርጉኝ ቢል ግን ወጥ መርገጥና አሳዳጊ የበደለው መሆኑን በይፋ ማሳወቅ ነው – ለወያኔ ሥልጣን አይመጥንም ማለት እንዳልፈለግሁ ግን አስረግጬ መናገር እፈልጋለሁ – ለወያኔ ሹመት በትንሹ ግዑዝ ድንጋይ መሆን ከበቂ በላይ ነው – አምባሳደር ለመቀበልና ለመሸኘት ደግሞ እንደራስ ሆቴል አንበሣ በምሥል መልክ ወንበር ላይ የሚዘፈዘፍ ግርማ ወልደጊዮርጊሳዊ ጥውርም ሲበዛ ነው፡፡ ኃይሌን በሚመለከት አጥንቴ ድረስ ዘልቆ ክፉኛ የተሰማኝ የኢትዮጵያን ሕዝብ መናቁና ሀገር ሻጭ ወያኔን መጠጋቱ ነው – ምንም ነገር ሳይቸግረውና ማይማዊ ደደብነቱ አስገድዶት (በነገራችን ላይ እንደወያኔዎች ሁሉ በሰይጣናዊነት እንደሚታማም አውቃለሁ – በማስጠንቆል የደረሰበትን የሀብትና የዝና ጣሪያ የማናውቅ መስሎትም ከሆነ ተዘናግቷልና እንደምናውቅ ይወቅ፤ ከተመቸኝና ከፈለግሁ ወደፊት በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እመለስበታለሁ)፡፡ እንኳንስ እርሱ እኔ ራሴ – ኃይሌ ንፍጡን እያዝረከረከ ደብተሮቹን በጉያው ወትፎ ወዳልጨረሰው ትምህርቱ ይሄድ በነበረበት ሰዓት ከፖለቲካው ባልራቀ ሁኔታ ሀገሬን አገለግል የነበርኩትና በመቶዎች የሚቆጠሩ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው መጣጥፎችን ለሀገሬ ያበረከትኩት ሰውዬ ለቀበሌ አመራር እንኳን እበቃለሁ ብዬ አላስብም፤ ምክንያቱም ተፈጥሮየ ለአመራር ሳይሆን ለመጻፍና ምናልባትም ለማላውቀው ለሌላ ነገር ነው፡፡ ምቹ ሁኔታ ተፈጠረልኝ ብዬ እንደኃይሌ ‹ለዚህ ቦታ ምረጡኝ› ብል መናገሩንና መወዳደሩን እንደምችል ባውቅም ካለተፈጥሮ ዝንባሌና ችሎታ ገብቼ መፈትፈቱ ግን የኋላ ኋላ ችግር እንደሚያመጣብኝ እረዳለሁና አልሞክረውም፡፡ ይህን የምለው ለጊዜው ሌላ እውነተኛ ማነጻጸሪያ ስላጣሁና እውነቴንም ስለሆነ ነው፤ ጊዜ ሰጠኝ ተብሎ ወደአንድ ነገር ቢሞጀሩበት ችግር ነው – የግብጹ ሞሐመድ ሞርሲን ልብ ይሏል – የተፈጥሮ ጥሪን መረዳት ተገቢ ነው ወንድሞቼ እንዲሁም እህቶቼ፡፡ እናም ኃይሌ መቶ ሀገር ቀርቶ አንድ ሺህ ሀገር ቢዞርም በኢሣት እንደሰማሁት አዟዟሩ የሩጫ እንጂ ፖለቲካዊ የሥራ ጉብኝት ባለመሆኑ ዙረቱ እንደተባለው ዕቃ ለመሸመትና ያማረ ሆቴል ተከራይቶ ለመንፈላሰስ ካልሆነ በስተቀር ለምንም ዓይነት የፖለቲካ ተሹዋሚነት አያበቃውም፡፡ ይህ ሰው ጭንቅላት የሚባል ነገር በጭራሽ ስለሌለው እንጂ – እንደእንስሳ ሽምጥ ለመጋለብ ከሚጠቅም ደመነፍሳዊ አንጎል በስተቀር ማለት ነው – ትንጥዬ አንጎል ብትኖረው ኖሮ ወደዚህ ቅሌትና ውርደት አይገባም ነበር፡፡ በደደብነቱ ሳቢያ ልቦናው ታውሮበት እንጂ እኔና እርሱ እንደዮሐንስ መጥምቁ አባባል የጫማቸውን ማሠሪያ ለማሰር ወይ ለመፍታት የማንበቃ ስንትና ስንት ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ኢትዮጵያውን ቀኒቱን እየተጠባበቁ ናቸው – በበሣል አመራራቸው እንደእስራኤል በጥቂት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ሌሎች ሀገሮች ወደደረሱበት የሥልጣኔና የዕድገት ማማ ለማድረስ(አባብሌ ዲግሪው ላይ አለመሆኑን ‹ፕሊዝ› ተገንዘቡልኝ – ለዲግሪ ለዲግሪውማ ‹ፕሮፌሰሮች› ክንፈ አብርሃምና አንድርያስ እሼቴስ ነበሩን አይደል? በአካልም በመንፈስም በኅሊናም ሙታን ሆነው ሀገር ሻጮች ጋር ተባበሩብን እንጂ)፡፡ ከዚህ ሰው ሳይሆን ምቹ ሁኔታን የማጣታችን ሁኔታ አኳያ የዚህን ንፍጣም ሰውዬ ምኞትና የሕጻን ፍላጎት የሚመስል ጤንነት የጎደለው ቅዠት ስታዘብ አንዳች የመደፈር ጸጸት ይወረኛል፤ በምትንቀው መናኛ ሰው እንደመደፈር ያለ ደግሞ የጸጸት መንስኤ የለም – ደግሜ ልራገም መሰለኝ – የሥራውን ይስጠው፤ እሱ ሕዝብን እንደናቀ በዓለምም እንዳስገመተን ሞት ግን ውለታ ይዋልልንና ንቆ አይተወው፡፡ ራስን ያለማወቅ ችግር – እርግጥ ነው – የዓለማችን ራስ ምታት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ይሁንና ራስን አለማወቅ የፈለገውን ያህል ችግር ያስከትል እንጂ እንደኃይሌ ያለ ሰው በምናውቅለት የሥራና የትምህርት ወይም የችሎታና የልምድ ታሪክ ከመሬት ተነስቶ የጠላት መሣሪያ ልሁን ብሎ መነሳቱ ዕብደት ካልሆነ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡
‹ምላሴ ጥቁር ነው፤› እርግማኔ አይደርስም አልልም፡፡ በሥርዓት ደረጃ እየዘገየብኝ ተቸገርኩ እንጂ በግለሰብ ደረጃ እርግማኖቼ ዒላማዎቻቸውን መትተው ወደሰገባቸው የሚመለሱባቸውን ጊዜያት ማስታወስ አይከብደኝም፡፡ አበበ ገላው በመብረቃዊ የቁጣ ድምጹ የተሸሸገና በያዝ ለቀቅ የፖሊስና ሌባ ጨዋታ ከሟች ጋር ድብብቆሽ ይጫወት የነበረን ነቀርሣ አፋፍሞ የመለስን ሞት ማፋጠኑ አይዘነጋም፡፡ በዚያም ምክንያት የጎጃም ባላገር እንዲህ ብሎ ስንኝ መቋጠሩ በ‹ኢቲቪና በኢትዮጵያ ኤፍ ኤሞች› በስፋት ተዘግቧል፡፡
ሽጉጥ አልታጠቀ መትረየስ የለው፤
ባንደበቱ ገዳይ አበበ ገላው፡፡
እኔም በእርግማን ሰው መግደሌ ይፋ ሆኖ ወደሕዝብ ጆሮ የሚደርስልኝ ከሆነ ያገሬ ባላገር እንዲህ ብሎ ሳይቀኝልኝ እንደማይቀር ተስፋ አደርጋለሁ፤ ምኞት መቼም አይከለከልም፡፡
ሞይዘር አልታጠቀ ፊሻሌ የለው፤
በጠሎቱ ገዳይ ጦቢያን ገረመው፡፡
ስለዚህ ኃይሌን እረግሜያለሁና ‹ከኔ እርግማን› ነጻ መውጣት ከፈለገ አሁኑኑ ይቅርታ ጠይቆ ከ‹ውድድሩ› ይውጣና አርፎ ሌላ የሚችለውንና የሚገባውን ሥራ መሥራቱን ይቀጥል፡፡ በበኩሌ ጦሬን ሰክቻለሁ – በፈጣሪ ፊት ተንበርክኬ የእርሱን መጨረሻ እንዲያሳየኝ በዕንባ ጭምር ጠምጄ ይዠዋለሁ – ሌሎችም ዕርዱኝ – እንረዳዳና ይህን ተናግሮ አናጋሪ የወያኔ ዕብድ ውሻ እናስወግድ – የተከፋች ‹አብዮት ልጇን› እንደምትበላም እናሳየው፡፡ መዳኛው አንድና አንድ ብቻ ነው – ያም ተጸጽቶ ሕዝብንም ይቅርታ ጠይቆ መመለስ ብቻ ነው(በወያኔ ትዕዛዝ ወደ አሥመራ ተልኮ ሻዕቢያ ሥር በመደፋት የአማራውን ሕዝብ ለውርደት የዳረገው ንጉሤ አስገልጥ(?) የተባለ ቀልማዳ ከሃዲ እንዴት እንደሞተና ሕዝብ አድሞበት ሬሣው በኩሊ እንደተቀበረ ልብ ይሏል፤ ሕዝብ ከጠላ መድረሻ የለም – በተለይ የኢትዮጵያ! ያቆየንና ገና ብዙ እናያለን ውድ ወርቃማ ኢትዮጵያውያን!) ፡፡ ይህን ደግሞ ይወቅ – ከተገፋና በበደል ብዛት ከሚንተከተክ አእምሮ ኃይል ይመነጫል፤ ያ ኃይል ደግሞ አጥፊም አልሚም ሊሆን ይችላል – ጦርም ዳቦም ከአእምሮ ይፈልቃል፡፡ እየተረጋገምን ዘር ከምናጠፋ እየተሳሰብን ዘር ብናለማ ይሻላልና ይህን መልእክቴን – ሳታናንቁብኝ – ለርሱው ለደንቆሮው ኃይሌ አድርሱልኝ – ሁኔታዎች ቢመቻቹ በአካል ባገኘውና እስከዶቃ ማሰሪያው ብነግረው በወደድኩ – ግን … ፡፡ (እንዳስፈላጊነቱ እቀጥላለሁ!)