Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ኢትዮጵያን ባሰብኳት ግዜ አለቀስኩኝ!!! –ከ-ሳሙኤል አሊ

$
0
0

ከ-ሳሙኤል አሊ (ኖርዌይ)

ሳሙኤል አሊ

ሳሙኤል አሊ

ፍቅር እንደ ሻማ የተላበሰች አገር፤ ጀግነትን እንደ ባህል የያዘች አገር፤ ጥበብን ለልጆቿ ስታስተምር የኖረች አገር፤ ፍልስፍናን ለአለም ስትገልጽ  የቆየች አገር ፤ በሁሉ ቀዳሚ የሆነች አገር መሆናን በአፍ  ሳይሆን በተግባር ገልፃ ያሳየች እንደሆነች እናውቃለን። ፍደልን ቀርፃ ዘመንን ቀምራ የተገኝች ብችኛዋ  አፍሪካዊት አገር ፤ ኢትዮጵያ የዜማና የፍልስፍና አስተምሮ የበቀለባት አገር፤ በቀኝ ያልተገዛች ቅኝ ገዢወችን አሳፍራ ያባረረች የአፍሪካ  ፈር ቀዳጅ ውዷ አገራችን ኢትዮጵያ ናት። ይሄንን ለመግቢያ ያክል አልኩኝ  እንጂ ዛሬ ግን ይህ ሁሉ ክብርና ዝና  ሀይልና መፈራት   ፍቅርን እና መዋደድን አንድነት እና መስማማትን  ከኢትዮጵያ አገሬ ጠፍታል። ለምን ይሆን? ማን ነው አጥፍው? ተጠያቂውስ ማን ይሆን በዚህ ዙርያ ትንሽ ልበል፦

ኢትዮጵያ የሀዘን ካባዋን ደርባ  ነጠላዋን አዘቅዝቃ  ሀዘን ከተቀመጠች ድፍን 24 አመታትን አስቆጥራለች። ከ24 አመት በፊት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ የነበሩት መንግስታቶች በህዝብ ላይ አንባገነን ሆነው ከፍተኛ በደል ቢያደርሱም ቅሉ በኢትዮጵያ  ጉዳይ ግን አይደራደሩም  ነበር።  ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከ24 አመት በፊት የምትፈራ የምትከበር ህዝቡም በፍቅር የሚኖርባት ነበረች። አሁን ላይ ግን በዘመነ ወያኔ  ዜጎች በማንነነታቸው ከየት አካባቢ ብሄር የመጣኸው/ሽው? እዚህ ለመኖር፣ ለመስራት፣ ለመሳሰሉት የመኖሪያ ፈቃድ አለህ/ሽ ወይ? በሚል ብሄርን ከፋፍሎ መለያ በመስጠት ተከባብሮ የኖረን ህዝብ በትውልድ ሀገሩ እርስ በርሱ እንዲጋጭ  እየተደረገ ነው ።

እትዮጵያ ማለት ከአንባገነንም በላይ አንባገነን የነገሰባት የአንድ ዘር የበላይነት የታወጀባት ሆና እርስ በርሳችን እንደንጠላላ የማድረግ ስራ እየተሰራባት ኢትዮጵያ የምትባል  አገር በአለም የተናቀች አድርጎ ሕዝባችንን በሃገሩም የተገፋ በስደትም የተናቀ እንዲሆን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።

ከኢትዮጵያ በፊት ዘሬን ላስቀድም የሚል ትውልድ መፍጠር ለዚህም በዘር ከፋፍሎ ለሁሉም ዘር ባንዲራ መስጠት እና ያንን ባንዲራ  በየክልሉ እንዲውለበለብ በማድረግ ልዩነት እንዳለን በማስመሰል የእከሌ ዘር ይህንን ባንዲራ የእከሌ ዘር ያንን ባንዲራ  ብሎ ከኢትዮጵያዊነት ዝቅ ብሎ ዘር ተራ አውርዶ ዘሩን እንዲያስብ  ማድረግ ወያኔ ያመጣው ሰይጣናዊ አመለካከት ነው።

በመሰረቱ ወያኔንም እስከአሁን በስልጣን ላይ ያቆየው  የዘር ፖሊሲው ነው  ይህ ቁማር ለጊዜው  የሚጠቅመው ለወያኔወች ሊሆን ይችላል በሃላ ግን ለልጅ ልጆቹ የማይፋቅ እዳም እያስቀመጠ  ያለውም ወያኔ ነው።  ክልል ብሎ በከለለው  እንኳን  ብንሄድ  ድንጋያማዋን ትግራይን ይዞ ቁጭ ብሎ የደም እንባ የሚያነባውና የሚራበው ወያኔ  ቆሜለታለው የሚለው የራሱ ሰዎች ናቸው። ሌሎቹን ብንመለከት ግን ሰፊ ለም መሬት ሰፊ የውሃ  ሃብት አላቸው ዛሬ ደስ ብሎህ የምትንጫጫ የወያኔ  ጉጅሌ  ሁላ  ነገ እንደ ወንዝ የማያባራ  እንባህን ትዘራታለህ ሁሉም የእጁን ነው የሚያገኝው  እዚህ ላይ ግን በዚህ  አካሄድ ላሰምርበት የምፈልገው ብዙ ያልተረጋጉ ሁኔታወች  አመኔታ ያላገኙ የክልል ክለላወች  እንዳሉ እሙን ነው።  ይሄ ነው የኔ፡ እዚህ ድረስ ነው፡ የኔ የሚል እሰጣ ገባ ውስጥ ከወያኔ ውጪ ሌላው ህብረተስብ መግባት እንደሌለበት ለመናገር እወዳለው።  አይ የለም መገባት አለበት የሚባል ከሆነ ግን  ተመልሰን እንደጋርዮሽ ስረአት ቀድሞ  የኔ ቦታ  እዚህ ድረስ ነበርና  ማስመለስ አለብኝ  የኔ ግዛት ትንሽ አንሳለች እና   ማስፋፋት አለብኝ  ወደሚለው መሄዳችን ግልጽ ነው።  በፍቅርና በአንድነት ስንኖር  እንኳን ለኛ ኢትዮጵያን ቀርቶ ለአለም የሚተርፍው አገራችንን በይገባኛል ተራን የማይረባ ነገር አገራችንን ሲኦል እንዳናደርጋት  አደራ  እላለው ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ኢትዮጵያ ጠፈታለች  አንድ ዘር ከአንድ ዘር ጋር በጎን እንዲተያዩ  እየተደረገ ነው።  አንዱ ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት ጋር ጥላቻ እያስፈኑ ነው። ክልል ድንበር እያለ  በኢትዮጵያ ምድር  በነፃነት እንዳንቀሳቀስ  እያደረጉን ነው።  ይህን ሁሉ የኢትዮጵያ ሰላም ያናጋ የኢትዮጵያን ፍቅር ያጠፋ ወያኔ የተባለ የተደራጀ ዘራፊ ሰይጣናዊ ቡድን ነው።  ይህንን ዘራፊ ቡድን  ባስቀመጠልን የመከራ ክልል ሳንወናበድ፧ ወያኔ በዘረጋው የዘር ከዘር ልዩነት ሳንከፋፍለን፧ ኢትዮጵያን የማዳኑን ስራ የመስራት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ  ነው።  ከወገኔ አንድ ሰው ቢሞትብኝ አልቅሼ የምቀብረው   አገር ሲኖር ነው። አገር ከሞተች ግን እንኳን በደስታ መኖር ይቅርና   በክብርም መቀበርያ  እናጣለን አገር እየገደለ ያለው ወንበዴ ወያኔን ቀድመን ልንገለው ግድ ይለናል።

ኢትዮጵያን ሁሉ ዘር ሳይለያየን ሃይማኖት ሳይከፋፍለን  ከዳር እስከዳር  እጅ ለእጅ ተያይዘን  በደስታ፧ በነፃነት ፧ በእኩልነት፧ የምንኖርባትን አገር ለመመስረት  ኢትዮጵያን እየገደላት ያለውን ወያኔ የተባለውን ገዳያን እንግደልላት ከጸጋዋ  ተካፍለን በፍቅራ እንድንጠለል ፍቅር አጥፊውን ወያኔን እናጥፋ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

ከ -ሳሙኤል አሊ ( ኖርዌይ)

Email samilost89@yahoo.com

June 14.2015

The post ኢትዮጵያን ባሰብኳት ግዜ አለቀስኩኝ!!! – ከ-ሳሙኤል አሊ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>