ሼህ መሐመድ አላሙዲ-ከመንግስት ባለስልጣናት-ከልማታዊ አርቲስቶቻችን
ቱጃሩ ‘ሼክ’ መሐመድ አል አሙዲን፤ጋጠወጦቹ የወያኔ መንግስት ሹማምንቶች፦ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የፌደረሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን፣ እንዲሁም ታላላቅ ‘የተከበሩ’ እንግዶችና የአርቲስት ቤተሰቦች በተገኙበት፤ በትላንትናው እለት የትዝታው ንጉስ ጋሽ ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙያ ጉዞ በማስመልከት የተዘጋጀ ዝግጅት ሲከበር፤ ከወጣቷ አክትረስ ማህደር አሰፋ ጋር ከትዳራቸው ውጭ ሲማግጡ ታይተዋል። ይህ ከሃገራችን ባህልና ወግ በእጅጉ የሚፃረርና የወደፊት ተተኪውን ትውልድን ወደ አልባሌ ድርጊት የሚገፋፋ ነውረኛ ተግባር ነው።
ማህደርና ሼሁ ለብዙ ጊዜ ሲታሙ መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን ንቀት ካልሆነ በቀር እንደዚህ ጋጠወጥ የሆነን ድርጊት በአደባባይ ማድረጉ ለምን አስፈለገ? የወያኔ ሊቀመናብርት ባለስልጣናትን በመዳፋቸው በማስገባት የሃገሪቱን ሃብት የሚዘርፋት ሼክ መሃመድ አል አሙዲን በልማታዊ አርቲስቶቻችን ሰይፉ ፋንታሁን፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ሙሉዓለም ታደሰ፣ ማዲንጎ አፈወርቅና በሌሎችም አማካኝነት ታዳጊ ወጣት የሃገራችን ልጃገረዶችን በሃብታቸው በማማለል ከአላማቸው በማሰናከል ንፅህናቸውን እንዲያረክሱ ያስገድዷቸዋል። ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት የሚያውቁት የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ከማድረግ ይልቅ በተጋበዙበት ግብዣ እንኳን ከትዳራቸው ውጭ እየማገጡ እያዩ በጭብጨባ አጅበዋቸዋል።
ወያኔና ጀሌዎቹ ላለፉት 24 ዓመታት የኃገራችን ሃብትና ንብረትን የዘረፉት አንሷቸው፤ ታሪካችንን ሲያጠለሹ፣ ሲያጠፉ፣ የታሪክ መፅሃፍትና ቅርስ ለባዕድ ሲሸጡ፣ ሲያቃጥሉ፣ ባህልና ወጋችንን ሲያንኳስሱ፣ የእምነትና ሃይማኖት ስፍራዎችን ሲያረክሱና ሲያቃጥሉ፣ እንዲሁም አያሌ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ መቆየታቸው ፀሃይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለእኔ በዚህ ደረጃ ተንኮታኩታ ጥበብ በአደባባይ ረክሳ፣ ሃገር ተደፍራና አንገታችንን አስደፍታ ማየት ያመኛል። ልማታዊ አርቲስቶቹና የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት በሼሁ ፍርፋሪ ገንዘብ ህሊናቸው ታውሯል። ልማታዊ አርቲስቶቹም በጥቅም በመደለል የወያኔ ሎሌ ሆነዋል። በቅኝ ግዛት ተገዝታ የማታውቀው ሃገራችን ኢትዮጵያም ሼክ መሐመድ አል አሙዲን እንደፈለጉ የሚፈነጩባትና እሚያዙባት ሃገር ሆናለች።
ሼህ መሐመድ አል አሙዲን 28 ክርስቲያን ወንድሞቻችን ISIS በሚባለው እስላማዊው አሸባሪ ቡድን ከታረዱ ወዲህ ለብዙ አርስቲስቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብሮች በስጦታና በሽልማት መልክ አበርክተዋል። ለአብነት ያህል ለአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅና ለንዋይ ደበበ ሁለት ሁለት ሚሊዮን ብር፣ ለመሳፍንት 9 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በትላንትናው ዕለት ለአርቲስት ማህሙድ አህመድ 5 ሚሊዮን ብር በሽልማት መልክ ለግሰዋል። እውን ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ለአርቲስቶቻችን እውነተኛ አክብሮት ኖሯቸው ይሆን!? እውነተኛ ምክንያታቸው ይህ ቢሆን ኖሮ በርካታ ታላላቅ አርቲስቶቻችንና እውቅ ዜጐቻችን በሼሁ ብሮች በተጥለቀለቁ ነበር። ይልቁኑስ በዙሪያቸው የተሰባሰቡት አርቲስት ተላላኪዎቻቸውና ሎሌዎቻቸው በወንጀል ያደፈ ልባቸውን፣ በዝርፊያ የተጨማለቀ እጃቸውንና፣ ውስጠ ሚስጥራቸውን ስለሚያውቁ በውለታ መልክ ጠፍረው ለመያዝና አንዳንድ የዋህ ዜጐችን ለማምታታት ይመስላል።
ሼሁ በእውነት ለሃገራችን ደራሽ የሆኑ ቅን ሰው ቢሆኑ ኖሮ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃዘን ቅስሙ በተሰበረበት፣ መሪር ሃዘኑ በከፋበት፣ የልጆቹ አንገት በቢላዋ ሲቀላ በአደባባይ ተመልክቶ ባዘነበት በዛ ድቅድቅ ጨለማ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሃዘናቸውን በገለፁ ነበር፤ እንደሌላውም ቅን ኢትዮጵያዊ ልጆቻቸው ለታረደባቸው ቤተሰቦች እርዳታ ባደረጉ ነበር። ዛሬ ደግሞ አይናቸውን በጨው አጥበውና የኢትዮያን ህዝብ ንቀው፤ የልጅ ልጃቸው ከምትሆነው ከወጣት ተዋናይት ማህደር አሰፋ ጋር፤ ከኢትዮጵያ ባህልና ወግን ባልተከተለ መልኩ ባደባባይ ባልባለጉ ነበር። ሼሁ በISIS ልጆቻቸው ለተጎዳባቸው ቤተሰቦች ሃዘናቸውን ያልገለፁትና ያለመርዳታቸው፣ ያለሃፍረትም እንዲህ ያስፈነጠዛቸው ምክንያት በሃዘናችን ተደስተው ይሆን!? ወይንስ ሌሎችም እንደሚታሙት ለISIS አጋርነታቸውን እየገለፁ!?~መጠርጠር አይከፋም!።
የኢትዮጵያ ታሪክና ወግን አስጠብቀን ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ ወያኔን ማስወገድ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም በልጆቿ ተከብራ ትኑር!
እናቸንፋለን!
The post የፍቅር ትርያንግል አዙሪት(Lovers Triangle) (በሥዩም ወርቅነህ) appeared first on Zehabesha Amharic.