Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Hiber Radio: ምርጫ 97ን ተከትሎ ሰኔ አንድ በአጋዚ ጥይት የተገደሉ ሰማዕታት ሊታሰቡ መሆኑ፣ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች በጋራ እንዳይዘክሩ ማስፈራሪያ መኖሩ፣አሜሪካ አይ.ሲ.ስን በመሳሪያ ረድታለች የሚል ወቀሳ መቅረቡ፣ አሸባሪው ቡድን በሊቢያ ሁለት ኤርትራውያንን በጭካኔ ገደለ ከታፈኑት ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ አይቀርም መባሉ፣ኢትዮጵያ ፍትህ በማዛባት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ መሆኗን ሪፖርት ማመልከቱ፣ ቃለ መጠይቅ ከምርጫ 97 የሰማዕታት ቤተሰቦች ሰብሳቢ ጋር እና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የግንቦት 30 ቀን 2007 ፕሮግራም

< …በምርጫ 97 ሰኔ ቀን 1 እኔ የተገደሉ ሰዎችን ሬሳ ሳነሳ ነበር። ወንድሜ መገደሉን አላወቅኩም። ሰዎች እንዳልደነግጥ እጁን ተመቷል ነው ያሉኝ ከእናቴ ጋር ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄጄ ሳውቅ በደርግ ቀይ ሽብር በተገደለ ወንድማችን ሀዘን የተጎዳችው እናቴ በወንድሜ ሚሊዮን ከበደ ሞት ደግሞ ምን ትሆን ብየ ደነገጥኩ… የሰማዕታት ቤተሰብ እያልክ መሰብሰብህን እንድታቆም የሚል ተደጋጋሚ ማስፈራሪያ ደርሶኛል እነዚያ ንፁሃንን የገደሉት…>አቶ ኢዮብ ከበደ የምርጫ 97 ሰማዕታት ቤተሰቦች ኮሚቴ ሰብሳቢ ለህብር ሬዲዮ ሰኔ 1 ቀን 1997 በአጋዚ ጦር ወንድሙን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን የተገደሉበትን ቀን በተመለከተ ካደረግንለት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…የተቃዋሚዎች ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ ለህዝቡ ለውጥ ለማምጣት ከተከፈሉ መስዋእትነቶች ጎን ለጎን የእርስ በእርስ ንቁሪያ እና ስም ማጥፋት በስልጣን ላይ ያሉ ገዥዎችን ሲጠቅም ትግሉን በከፍተኛ ደረጃ ጎድቷል። እንዲህ አይነቱ መናቆር እንዲወገድ… > ወይዘሮ ፀዳለ እጅጉ የቀድሞ የኢህአፓ ታጋይ በተቃዋሚው ጎራ ስላሉ ተቃዋሚን መቃወምና ተራ ስም ማጥፋትን እንደ ትግል የሚቆጥሩትን አንዳንድ የስም ተቃዋሚዎች ሁኔታ በተመለከተ አነጋግረናቸው ከሰጡን ሰፋ ያለ ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በተቃዋሚዎች ላይ ከሚፈፀመው እስር ድብደባና የፈጠራ ክስ ጎን ለጎን በእስር ቤት የሚደርሰውን ስቃይ ፍርድ ማግኘት ባይቻል እንኳን ተበደልኩ ብሎ በፍርድ ቤት መናገር ይከለከላል… አቶ ማሙሸት አማረ በእስር ቤት የጤናቸው ሁኔታ…> አቶ ለገሰ ወልደሃና ከመኢአድ በምርጫ ቦርድ ህገወጥ ውሳኔ የተባረረው ህጋዊው አመራር ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በሊቢያ በአሸባሪው ቡድን የታፈኑ ኤርትራዊያንና ኢትዮጵያዊያን እጣ ፈንታ ምን ይሆን? (ልዩ ዘገባ)

የፊፋው ፕሬዝዳንት ላይ ኤፍ. ቢ. አይ የሙስና ምርመራ ጀምሮ ይሆን? ታዋቂ የቀድሞ ተጫዋቾች እና የስፖርት ባለስልጣናት ፊፋን ስላተራመሰው የሙስና ቅሌት እየሰጡት ያለው አስተያየት ( ልዩ ዘገባ )

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የምርጫ 97 ሰኔ 1 ቀን ሰማዕታት አስረኛ ዓመት በአዲስ አበባ ይዘከራል

ሰማያዊ ፓርቲም ጥሪ አቅርቧል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የህግ የበላይነት ከሌለባቸውና የፍትህ ስርዓት ከተዛባባቸው አገሮች በስተመጨረሻ ላይ መገኘቷን ሪፓርት አመለከተ

አሸባሪው የአይሲስ ቡድን ሁለት ኤርትራዊያን ስደተኞችን በዘግናኝ ሁኔታ መግደሉ ተዘገበ

አሜሪካ ለአሸባሪው ቡድን በተዘዋዋሪ የጦር መሳሪያ አቀብላለች ተብላ ተወነጀለች

ኬኒያ ከኢትዮጵያ ለምትወስደው የኤሌክትሪክ ሐይል በዜጎቿ እንቅፋት ገጠመኝ ስትል አማረረች

ዜጎች የሚደርስባቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፍ/ቤት እንኳ መግለጽ ተከለከሉ

በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ለፍርድ ቤት ያለውን ንቀት በይፋ አሳየ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በቀጥታ በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽና በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።

The post Hiber Radio: ምርጫ 97ን ተከትሎ ሰኔ አንድ በአጋዚ ጥይት የተገደሉ ሰማዕታት ሊታሰቡ መሆኑ፣ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች በጋራ እንዳይዘክሩ ማስፈራሪያ መኖሩ፣አሜሪካ አይ.ሲ.ስን በመሳሪያ ረድታለች የሚል ወቀሳ መቅረቡ፣ አሸባሪው ቡድን በሊቢያ ሁለት ኤርትራውያንን በጭካኔ ገደለ ከታፈኑት ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ አይቀርም መባሉ፣ኢትዮጵያ ፍትህ በማዛባት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ መሆኗን ሪፖርት ማመልከቱ፣ ቃለ መጠይቅ ከምርጫ 97 የሰማዕታት ቤተሰቦች ሰብሳቢ ጋር እና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles