Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: ማር እና ሎሚን ቀላቅሎ መጠቀም ለጤና፣ ለቆዳ ውበት እና ለጸጉር ያለው ጠቀሜታ

$
0
0

honey
ማር በጣፋጭነቱ እና ባለው በርካታ የጤና ጠቀሜታ በብዙዎቻቸን ዘንድ ይዘወተራል።

ሎሚም በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት በተለያዩ ጊዜያት የተሰሩ ጥናቶች ይመከራሉ።

ማር እና ሎሚ በውስጣቸው አንቲኦክሲዳንት እና አንቲባክቴሪያ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን በመያዛቸው የሰው ልጅን በሽታ የመከላከል አቅም በመጨመር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።

ሁለቱን አንድ ላይ በማዋሃድ መጠቀም ደግሞ ክብደትን ለመቀነስ፣ ለቆዳ ውበት እና ለጸጉራቸን እንዲሁም ለጤናችን በርካታ ጠቀሜታዎችን ያስገኝልናል።

ማር እና ሎሚን በመቀላቀል የምናገኛቸው ጠቀሜታዎች፦

አስም፣ ጉንፋንና ብሮንካይትን ለማከም፦ ማር እና ሎሚን አንድ ላይ ቀላቅለን በመጠጣት ከመተንፈሻ አካላት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ እንደ አስም፣ ብሮንካይት እና ጉንፋን አይነት ህመሞችን ለማከም ይቻላል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ 2 የሻይ ማንኪያ የሎሞ ጭማቂና 1 የሻይ ማንኪያ ማር አንድ ላይ በማድረግ በ1 ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አንድ ላይ በመደባለቅ በቀን ውስጥ ደጋግምን መጠጣት ይመከራል።

በፊትና በቆዳ ላይ የሚወጡ እንደ ብጉር እና ሌሎች ችግሮችን ለማከም፦ ማር እና ሎሚ በተፈጥሮ የጸረ ባክቴሪያ ነጥረ ነገር ስላላቸው በባክቴሪያ እና ተያያዥ ነገሮች አማካኝነት በቆዳ ላይ ሚከሰቱ እንደ ብጉር እና ሌሎች የቆዳ ህመሞችን ለማከም ወይም ለማስወገድ ይረዳሉ።

እንዲሁም ለስላሳ እና ጤነኛ ቆዳ እንዲኖረንም ይረዳሉ።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሎሚ እና ማርን በአንድ ላይ በመደባለቅ ቢያንስ በሳመንት ሁለት ጊዜ መጠቀም አለብን ተብሏል።

የሰውነት ቁስልን ለመፈወስ፦ የሎሚ እና የማር ውህድ ቁስልን ቶሎ ለመፈወስ እና ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር በማድረግ ረገደም ጠቀሜታ አላቸው ሲሉ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

ማር በተፈጥሮ ባለው የስኳርነት ባህሪ አማካኘነት ማይክሮ ኦርጋኒዝሞችን የሚከላከል ሲሆን፥ ሎሚ ደግሞ ባክቴሪያዎች እንዳየራቡ በማደረግ ቁስል ቶሎ እንዲድን ያደርጋሉ።

ስለዚህ የሎሚ እና የማር ውህድ በመጠጣት ከቁስል ቶሎ መፈወስ እንችላለን።

ከልክ ያለፈ ውፍረትን እና ቦርጭን ለመቀነስ፦ ማር ከስብ ነጻ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፥ ሎሚ ደግሞ ዝቅተኛ የክሎሪክ መጥን እንዳለው ይነገራል።
ታዲያ የነዚህ ሁለቱ ውህድ በሰውነታቸን ስጥ ያለውን የስብ መጠን ለመቀነስ ይረዳሉ ተብሏል።

ስለዚህ ከልክ ያለፈ ውፍረትን እና ቦርጭን በቀላሉ ለመከላከል ለብ ባለ አንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ 3 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ችማቂ እና 1 የሻይ ማንኪያ ማር በመጨመር በደንብ አዋሀዶ መጠጣት ይመከራል።

ለጸጉር እንክብካቤ፦ የሎሚ ጭማቂ ጸጉርን ለመንከባከብ እንደሚረዳም ተነግሯል።

በተለይም የጸጉር መድረቅና የማሳከክ ስሜት ለሚሰማቸው ሰዎች የሎሚ ጭማቂ አይነኛ መፍትሄ ነውም ተብሏል።

የሎሚ ጭማቂን በቀጥታ የጸጉር ራስ ቅላቸን ላይ በመቀባት ጸጉር የማሳከክ ስሜትን ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን፥ እንዲሁም ጸጉራችን ተፈጥሯዊ ውበት እንዲኖረው ይረዳል ተብሏል።

ምንጭ፦ healthdigezt.com

የተርጉሞው፦ በሙለታ መንገሻ

The post Health: ማር እና ሎሚን ቀላቅሎ መጠቀም ለጤና፣ ለቆዳ ውበት እና ለጸጉር ያለው ጠቀሜታ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>