Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

“ሙስሊሙን ህብረተሰብ መናቅ ከባድ ዋጋን ያስከፍላል!”–ድምጻችን ይሰማ!

$
0
0

የተፈረደው እኛው ላይ ነው!
ሙስሊሙን ህብረተሰብ መናቅ ከባድ ዋጋን ያስከፍላል!
አርብ ግንቦት 28/2007

ሶስት መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎችን አንስተን ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› ማለት ከጀመርን 175 ሳምንታት አለፉ። እነዚህ ጥያቄዎች እንኳንስ ግድያ፣ እስራት፣ ማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ ስደት፣ ሃብት ዘረፋ፣ ወሲባዊ ትንኮሳ፣ ሃይማኖትን ማራከስ፣ የእምነት እሴቶቻችንን ማብጠልጠል፣ በአደባባይ ስምን ማጥፋት አና ሌሎች በደሎችንም ሊያስከትሉ ይቅርና መጀመሪያውኑ ሳይጠየቁ መከበር የነበረባቸው ናቸው። ሆኖም ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንደ ቀደምት አባቶቹ ዛሬም ቢሆን በሃገሩ ላይ እንደ ዜጋ ሳይቆጠር እጅግ ያነሱና አሻሚ ያልሆኑ፣ቢከበሩ ማንንም የማይጎዱ ጥያቄዎችን በማንሳቱ ብቻ ላለፉት 3 ዓመታት በጅምላ በተለያየ ደረጃ የመከራ ገፈት እየቀመሰ ይገኛል።
Muslim in ethiopia
በመንግስታት ደረጃ እንኳን ሊታሰቡና ሊጠበቁ ያልቻሉ የስነ-ስርአት መርሃ-ግብሮችን ለሃገር ሰላምና ለህብረተሰብ ደህንነት ባሰበና ባከበረ መልኩ ስንተገብር ቆይተናል። ይህንን ሁሉ ስናደርግ አማራጭ በማጣት፣ አልያም የመንግስትን እርምጃ በመፍራት ሳይሆን ለአገራችን ካለን ጥልቅ ፍቅርና
የሰላምን ዋጋ ካለፈው ታሪካችን እጥብቀን በመረዳታችን ብቻ ነበር፡፡

ባለፉት ቀናት በወንድም ዓሊ መኪ እና በወንድም ዓብዱልዓዚዝ ጀማል ላይ የተላለፈው የፖለቲካ ውሳኔ በመላው ሙስሊም ህብረተሰብ ላይ የተላለፈ ቅጣት ነው። ሰደቃ ማዘጋጀት እና ‹‹ንጹሃን እስረኖች ይፈቱ›› ማለት 15 ዓመታት የሚያስፈርድ ወንጀል ከሆነ በእርግጥም የተፈረደው በእኛው ላይ ነው… በፍትህ ፈላጊዎች ሁሉ ላይ! የ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› እንቅስቃሴ የግለሰብ እና የቡድን ጥያቄ ሳይሆን የመላው ሙስሊም ህብረተሰብ እና የፍትህ ወዳዶች በሙሉ ጥያቄ ነው። በሃሰት ክስ ወንድሞቻችን ላይ የተፈረደው የፖለቲካ ፍርድ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የተወረወረ የንቀት መልእክት ነው። ሕዝብን መናቅ እና ህዝብን ማስቆጣት ደግሞ መጨረሻው ምን እንደሆነ ከታሪክም ባለፈ መንግስት የተቀመጠበትን የስልጣን ወንበር ማየት ብቻውን በቂ ምስክርነት ነው።በመሆኑም በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት የሚኖሩ ሰላም ወዳዶችና ፍትህ ፈላጊዎች በሙሉ ይህንን ህዝብን የመናቅ ተግባር አጥብቀው ሊያወግዙት እና ሊታገሉት ይገባል። ሁላችንም ‹‹የተፈረደው እኛው ላይ ነው! የተናቅነው እኛው ነን! ሕዝብን መናቅ ደግሞ ዋጋን ያስከፍላል!›› ልንል ይገባል!

የፖለቲካ ፍርድ አንቀበልም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post “ሙስሊሙን ህብረተሰብ መናቅ ከባድ ዋጋን ያስከፍላል!” – ድምጻችን ይሰማ! appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>