በአሜሪካን ሀገር በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮዽያዊያን ስደተኞች ይኖራሉ! እነዚህ ስደተኞች ከጥቃቅን ስራዎች አንስቶ እስከ_ታላላቅ ካምፓኒዎች በወዛቸው ያገኙዋትን ዶላር አጠራቅመው አንድ ቀን ሀገሬ እገባለው ከሚል ተስፋ ጋር ሕይወትን ይገፋሉ::
ህልሙ የሞላለት ጥቂቱ ጠቅልሎ ሲመጣ አብዛኛው ግን በዥዋዥዌው የአሜሪካ ህይወት ባለበት ሰምጦ ይቀራል! ስደት የእድሜ ወፍጮ ነው! በአምስት አመት ውስጥ ሀገሬን አያታለው ያለ ዲያስፖራ ሳይታሰብ ስምንት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ምርጫ መታዘቡን ሲያሰላው ስደት ከወጣም ከሰላሳ አመት መዝለሉ ትዝ ይለዋል! ነገ ያሉት እቅድ ተራራ የመግፋት ያህል ይከብድና የተስፋ ሞተርም እየቀዘቀዘ ይመጣል! ይሄ ሁሉ “ምን ይዤ ልግባ?” ከሚል ይሉኝታ የሚፈጠር ሰውኛ ጭንቀት ነው! በእርግጥ ዲያስፖራዎች ያሳዝናሉ::
ለአንድ ራሳቸው የሚሆን ቅሪት ቢፈጥሩ እንኩዋን አናት_እያከከ የሚጠብቃቸው ነብሳት ብዙ ነውና ሀገር ቤትን እንደ_ናፍቆታቸው ሊመለሱበት ይፈሩታል! እናም “ወይ_ሀገሬ” ከሚል የትዝታ ዜማ ጋር የአሜሪካ ሰፊ ከርስ ውጦዋቸው ይቀራል! እንደዚህም ሆኖ ሀገራዊ ምስላቸው ሸጋ ገፅታ ይዞ ኖሮዋል! ሰሀንም አጥበው ነገን ለፈጣሪ ይተውታል እንጂ ገንዘብ ፍለጋ አጉል መንገድ አይሞክሩም! ባለፈው ማርች ወር ግን እውነት ይሄ ሰው የአበሻን ውሃ የጠጣ ነው? ያስባለ ጋንግስተር ኢትዮዽያዊ የአሜሪካ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር! ኢትዮዽያ ውስጥ የተወለደው የ42 አመቱ “ወሰን_አሳየ” እ.ኤ.አ ከ2013 ኦክቶበር አንስቶ 12 ባንኮችን መዝረፉ ሳያንሰው በህግ ጥላ ውስጥ ከዋለ በዋሃላም ጀብዱ መስራቱን አላቆመም! በፖሊስ ታጅቦ ከሄደበት ሆስፒታል የፖሊሱን ሽጉጥ ነጥቆ በማምለጥ በሂሊኮፕተር ሳይቀር በተደረገበት ክትትል ተይዞ ዛሬ 122 አመት ተፈርዶበታል::
The post ኢትዮዽያዊው በአሜሪካ 122 አመት ተፈረደበት appeared first on Zehabesha Amharic.