ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ
ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ 04.06.2015 Munich ሰአት 13:00
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካህደውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የዲሞክራሲ እና የነጻ ፕረስ መታፈን፣ ኢንዲሁም የምርጫ ማጭበርበር በመቃወም ሁሉም ለኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እና የ ዲሞክራሲ እንዲሁም የሰላም ተቆርቋሪ የሆናችሁ ሁሉ ኑ በአንድ ላይ ድምጻችንን እናሰማ
የሰላማዊ ሰልፍ አላማ
በጀርመን የአመቱ ፕሬዚደንትነት አዘጋጅነትና ጋባዥነት በዚህ አመት 2015 06.-07.June 2015 በ ሙኒክ ከተማ ጀርመን በሚካህደው የ G 7 ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ዉስጥ ጋዘጠኞችን በብዛት በማሰር እና ምርጫ ማጭበርበር እንዲሁም በከፍተኛ ሰብአዊ መብት መጣስ የሚከሰሰውን ኢንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ስደተኛ አመንጪ የሆነዉን የኢትዮጵያን አምባገነን ስርአት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን መገኘት አጋጣሚ በማድረግ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተዘጋጅቶዋል
የሰላማዊ ሰልፍ አላማ
፩፣ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲቆም
፪፣በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የፖሊቲካ እስረኞች በጠቅላላ ባስቸኩዋይ እንዲፈቱ
፫፣የጀርመን መንግስት እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት እና የ G7 አገሮች ሁሉንም አምባገነን በእኩል አይን እንዲይዩ ለቆሙለት በቆሙበት ለሚመሰክሩለት ደሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ለኢትዮጵያ ሲሆን ፊታቸውን ማዞር የሚያቆሙበት ጊዜ መሆኑን ተረድተው በኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን ላይ ላለው አምባገነን ስርአት የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቆሙ እና በአንጻሩ ለዴሞክራሲ ለህግ የበላይነት ለስብአዊ መብት መከበር ድጋፋቸውን እንዲሰጡ እንጠይቃለን ፦፦፦
የጀርመን እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት እና የ ጂ፯ አገሮች መራጭ ዜጎች መንግስቶቻቸው በከፍተኛ ደረጃ ሰብአዊ መብትን ከሚረግጥ ፣የዲሞክራሲን እና የነጻ ፕረስን አፍኖ ከሚያጠፋ፣ለህግ የበላይነት ለማይገዛው በኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን ላይ ላለው አምባገነን ስርአት የሚሰጡትን ድጋፍ
እናጋልጣለን
ሰልፉ የሚጀምርበት ሰአት 13:00
ሰልፉ የሚጀምርበት ቦታ Stachus (Karlsplatz), München
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ
Contact Tel:. +49 160 4357232
E-mail:menschenrecht-ethiopia@
The post የሰላማዊ ሰልፍ 04.06.2015 Munich G7 ኃይለማሪያም ደሳለኝ appeared first on Zehabesha Amharic.