የራስ ምታት በአብዛኞቻችን ላይ የሚከሰትና እረፍት በማድረግ ወይንም ህመም ማስታገሻን በመውሰድ ወደ ቀደሞ ጤንነታችን መመለስ እንችላለን። ነገር ግን አልፎ አልፎ የራስ ምታት ህመም የሌላ ከባድ የሚባል ህመም መገለጫ ሊሆን ስለሚችል ወደ ሀኪም መሄድ እና ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።
እነዚህም ሁኔታዎች
✔ ለመጀመሪያ ጊዜ የራስ ምታት ተሰምትዎት የእለት ተዕለት ስራዎ ላይ ተጽእኖ ካስከተለ
✔ ድንገተኛ እና ከባድ የሆነ የራስ ምታት ከተሰማዎ
✔ ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ የራስ ምታት ከተሰማዎ
✔ ከራስ ምታቱ ጋር ተያይዞ ለመናገር መቸገር፣ ለማየት መቸገር እና የእጅና እግር የእግር አለመታዘዝ ካለዎት
✔ በ24 ሰአት ውስጥ እየባሰ የመጣ የራስ ምታት ካለዎት
✔ ትኩሳት፣ የአንገት ህመም ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ከራስ ምታቱ ጋር ከመጡ
✔ የራስ ምታቱ የመጣው ራስዎ ላይ በደረሰ የመመታት ወይንም የመጋጨት አደጋ ምክንያት ከሆነ
✔ ግማሽ ራስዎን ከፍሎ የሚያምዎ ከሆነ እና ከራስ ምታቱ ጋር የአይን መቅላት ወይንም ህመም ካለዎት
✔ ከ50 አመት እድሜ በላይ ከሆኑ እና የራስ ምታት ህመም የጀመርዎ ከሆነ
✔ከዚህ ቀደም በካንሰር ህመም የተጠቁ ከሆነ እና አዲስ የራስ ምታት ከተሰማዎ ናቸው።
The post Health: የራስ ምታትዎን በተመለከተ ሃኪምን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው? appeared first on Zehabesha Amharic.