Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ፍርሃትን ድል የነሳ ታጋይ ሕዝብ!!! ቅዳሜ ግንቦት 15/2007 ድምጻችን ይሰማ!

$
0
0

ferehat
አምባገነን ስርዓቶች የህዝብን ጥያቄ በመመለስና ብሶቱን በማድመጥ ህዝብ ዘንድ ከመከበርና ከመወደድ ይልቅ የህዝብን ጥያቄዎች በሀይል በማፈንና ለብሶቱ ምላሻቸውን ሌላ ብሶት የሚፈጥር በደል በማድረግ መፈራትን ይመርጣሉ፡፡ አምባገነኖች ቀና ብሎ የሚሄድ፣ ብሶቱን በአደባባይ የሚያሰማ፣ ግዴታዎቹን በማክበር መብቱን የሚጠይቅ ህዝብ ፈፅሞ አይሹም፡፡ ይልቁንም የሰጡትን የሚቀበል፣ የከለከሉትን የማይጠይቅ፣ የተናገሩትን ሁሉ እውነት ብሎ የሚቀበልን ህዝብ ለመፍጠር የፍርሀትን ድባብ በሁሉም አቅጣጫ ይዘረጋሉ፡፡

አሕባሽ ከተሰኘው መንግስታዊው እስልምና መምጣት በኋላ «የሀይማኖት ነፃነታችን በህገ-መንግስቱ መሰረት ይከበር!» ሲል አደባባይ የወጣው ህዝበ ሙስሊም አምባገነኖች የዘረጉትን የፍርሀት አጥር ማለፍ ችሏል፡፡ከመነሻው ህዝቡ ተቃውሞውን እንዲገታ ማስፈራሪያዎች የነበሩ ቢሆንም ህዝበ ሙስሊሙ ለእምነቱ ያለው ቀናዒነት የፍርሀት ድባቡን ማፍረስ አስችሎታል፡፡ መንግስትን ህዝባዊ ወኪሎቻችንን ጠርቶ እንዲያወያይ ያስገደደው ይኸው በፍርሀት ያልተለጎመው የሙስሊሙ አንደበት ነው፡፡

የፍርሀት ድባቡን አልፈው የህዝብን ሀላፊነት ከዳር ለማድረስ ያለ እረፍት ሲደክሙ የነበሩ ኮሚቴዎቻችን ደግሞ በአንጻሩ ለህዝቡ ተጨማሪ ጀግንነትን ያላበሱ ህያው ተምሳሌቶች በመሆናቸው ነበር የከፋ የበደል በትር ያረፈባቸው፡፡ በፍርሀት የማይሸበቡ፣ ቀና ብለው ተራምደው ለሌሎች ቀና ማለት ምሳሌ የሚሆኑ መሪዎች ያሉት ትግል መዳረሻ ድል መሆኑን በመረዳትም ነው ህዝብን ከመሪዎቹ ለመነጠል የሞከሩት፡፡ በተደጋጋሚ አስከፊ ጥቃቶችን በመፈፀም በህዝብ ሙስሊሙ ልቦና ውስጥ የሚዘዋወረውን የፍርሀት አልበኝነት ስሜት በፍርሀት ለመቀየር ጥረት አድርገዋል፡፡ በኮሚቴዎቻችን እና ለዚህ ህዝባዊ የመብት እንቅስቃሴ በጎ አመለካከት ባላቸው ላይ በየእስር ቤቱ የተፈፀመው ግፍ በአደባባይ «መብቴ ይከበርልኝ!» ሲል እያስተጋባ ያለውን ህዝበ ሙስሊም አንደበት ለመለጎም የታሰበ ነበር፡፡ ግና የሆነው በተቃራኒው ነው። የእነርሱ ግፍና በደል በበረታ ቁጥር የህዝብ ወኔ፣ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት እየጨመረ በመሄድ ሊፈጥሩ ሲሞክሩ የነበሩትን የፍርሀት አጥር መናድ ችሏል፡፡

በተቆጣጠሯቸው የህዝብ ሚዲያዎች የሚተላለፉት መሰናዶዎች በዋነኝነት ዓላማ ያደረጉት ህዝበ ሙስሊሙን ማሸማቀቅና አንገት ማስደፋት፣ ብሎም የፍርሀት ማቅን ተከናንቦ ከጀመረው የእምነት ነፃነቱን በህገ-መንግስቱ መሰረት የማስከበር ሰላማዊ ትግል እንዲያፈገፍግ ማድረግን ነው፡፡ እነዚህ ፍርሀትን እንዲወልዱ ተጠንቶባቸው የሚሰሩ ዝግጅቶች ለእምነቱ ባለው ቀናዒነት የደነደነውን ልቡን አልፈው መግባት ግን አልቻሉም፡፡ በስም ማጥፋቱ፣ በእስሩ፣ በድብደባው፣ በግድያው ማግስትም ድምፁን ከማሰማት ወደኋላ ባለማለት ፍርሀትን ማሸነፉን አመላክቷል፡፡ አምባገነኖች የሚፈጥሩትን የፍርሀት ድባብ ድል የነሳ ህዝብ ዘወትር ቀና ብሎ ይኖራል። የኢትዮጵያ ሙስሊምም በበደል ወጀብ መካከል ለመፍጠር የሞከሩትን የፍርሀት ድባብ ድል ነስቶ ቀና ብሎ እየኖረ በዳዬቹን አሳፍሯል!

ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post ፍርሃትን ድል የነሳ ታጋይ ሕዝብ!!! ቅዳሜ ግንቦት 15/2007 ድምጻችን ይሰማ! appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>