ቢቢኤን፡- ግንቦት 13/2007
መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ሃይማኖት ጣልቃ በመግባት የአህባሽ አስተምህሮን በፌድራል ጉዳዪች አስተባባሪነት፤በመጀሊስ ሽፋንነት የህገ-መንግስቱን አንቀጾች በመጣስ የሚፈጽመውን አስነዋሪ ተግባር አጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ
ከግንቦት7 እስከ 8 የፌድራል ጉዳዪች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ከአዲሱ በርሳቸው ትእዛዝ ከተመሰረተው አዲሱ የአህባሽ መጅሊስ ፕሬዝዳንትና ሌሎችም በተገኙበት ከዚህ ቀደምም የአህባሽ ጠመቃ በተካሄደበት የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ሰጥቷቸዋል፡፡
”የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አደጋ እና የመታገያ ስልቶች ” በሚል ርእስ በተሰጠው ስልጠና ላይ ዶክተር ሽፈራው ያስቆመጧቸውን የመንግስት መጅሊሶች ኢህአዴግ እንዲመረጥ የሚችሉትን እንዲያደርጉና ከዚያ በሁላ የአህባሽ አስተምህሮትን በሰፊው ለማዳረስ ያላቸውን እቅድ ተነጋግረዋል፡፡
ምርጫ ሊደረግ ጥቂት ቀናት በቀረቡት ዶክተር ሽፈራው የተለመደ ጣልቃ ገብነታቸወን መቀጠላቸው ኢህአዴግን ምረጡ አህባሽን በግዳጅ እንድጠመቁ የሚል መልክት እያስተላለፉ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ተችተዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ኢህአዴግ ዛሬም ከሙስሊሙ እምነት ላይ እጁን እንዳላወረደ አመላካች ነው ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ከነዶክተር ሽፈራው ጋር የህዝብን ጥያቄ ይዘው ሂደው ሲወያዩ የነበሩት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በአሁኑ ጊዜ በማረሚያ ቤቱ በኩል በህወሃት ደህንነቶች ትእዛዝ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡
ድምጸችን ይሰማ በበኩሉ ትላንት ባወጣው መግለጫ ከምርጫ በፊትም ሆነ በሁላ ህዝበ ሙስሊሙ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥለበት መግለጹ ይታወቃል፡፡
The post መንግስት በምርጫ ዋዜማ የሀይማኖት ጣልቃ ገብነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል * ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ከአዲሱ መጅሊስ ጋር በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ አህባሽን ከምርጫ በሁላ የማስቀጠያ መንገዶቹን ተነጋገሩ appeared first on Zehabesha Amharic.