Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: በቀላል አማራጮች ክብደትዎን ይቀንሱ

$
0
0

በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ

መፍትሄ ከታጣለት እና ለመቆጣጠር ከሚከብድ የውፍረት ችግር ለመላቀቅ ሰዎች የመረጡትን የመፍትሄ መንገድ ለመከተል በዚህ ወቅት የተመቻቸ አማራጭ አለ፡፡ ጊዜው እንኳን ወፍረውለት እንደ ሳር ቀጥነው ተፍ ተፍ ብለውለት እንኳን አብረውት የሚሄዱት አይነት አልሆነም፡፡ ለጤና ጥንቅነቱን ወደ ጎን ትተን የወፈርን እለት እኮ ፀሐዩ ለእኛ ብቻ የተሰየመ ይመስል የሚበረታብን ተፈጥሮውም የተፈጠረውም የሚጨክንብን እየመሰለን ሆድ ይብሰን ይሆናል፡፡ ስለዚህ ጨከን ብሎ አማራጮችን መፈለጉን ያስቡበት፡፡
የሚከተሉት ነጥቦች በተለያዩ የሳይንስ እና የተፈጥሮ የምርምር ውጤቶች ከሚሰፍሩባቸው ታማኝ የመረጃ ገፆች ላይ የተገኙ በመሆናቸው ከምንሰጋቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች በፀዳ መልኩ ጤናዎን ጠብቀውና አላስፈላጊ ክብደት ቀንሰው የተስተካከለ አካላዊ ቁመና ያላብስዎታል፡፡
loose weight
– በቂ እንቅልፍ ያግኙ፡፡ የእንቅልፍ እጦት ግሄሬሊን የተሰኘ እና ምግብ ፍላጎትን የሚጨምር ሆርሞን በውስጥዎ እንዲመነጭ የሚያደርግ ሲሆን ለምግብ አመንጪ ውፍረት እራስዎን አጋለጡ ማለት ነው፡፡ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የሚያመጣው ድካምም ማለዳ ላይ ለማከናወን እቅዶ ላይ የነበረን የዋና እንቅስቃሴና ሩጫ፣ እንዲዘሉ ምክንያት ሲሆንዎ ዘወትር ማለዳ መነቃቃትን ፍለጋ ስኳርን እና ካፍዬንን የመውሰድ ግዴታ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ስለዚህ መደበኛውን የእንቅልፍ ክፍለ ጊዜ በተቻለ መጠን ላለመዝለል ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

– ሰናፍጭ ያልታወቀለት ውፍረት መቀነሻ መንገድ መሆኑን ያውቃሉ? ሰናፍጭ ኤፓድሪን የተሰኘ እና በውስጣችን ስብን ለማቅለጥ የሚረዳንን ሆርሞን በተፈጥሯዊ መንገድ እንድንገነባ ይረዳናል፡፡ በኦክስፎርድ ብሩክስ ዩኒቨርሲቲ የሰው ልጅ አመጋገብ ላይ የሚመራመሩት ፕሮፌሰር አንድ ሾርባ ማንኪያ ሰናፍጭ ልፍስፍስ ወገብ ካለዎት በ20 በመቶ ችግርዎን እንዲቀርፉ ያስችሎታል ነው የሚሉት፡፡

– የምግብ ፍላጎትዎ መቆጣጠር ከሚችሉትም በላይ ነው? ረሃብን ሆድዎ የሚጠይቅዎ ሲሆን ህይወቶን ለማቆየት መብላትም ግዴታ ነው፡፡ ነገር ግን አዕምሮዎ ከሰውነትዎ ጋር በመናበብ ከፍተኛ የምግብ ፍጆታ ይጠይቅዎ ይሆናል፡፡ የእርስዎ ችግር ሱሰኝነትዎ በተለይ ለጣፋጭ እና ስብ አመንጪ ምግብ ከሆነ ለበሽታ የመጋለጥ ዕድልዎ የሰፋ ስለሆነ መፍትሄ ያሻዎታል፡፡ በዚህ ረገድ ተመራማሪዎች በዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች በከፍተኛ ፍጥነት ወደ አንጀት የማይዘዋወሩና ከፍተኛ የፋይበር መጠን ያላቸው ምግቦችን መጠቀም አማራጭ እንደሆነ ያስቀምጣሉ፡፡ ከፍተኛ ፋይበር፣ አፕል፣ ብርቱካን፣ ጎመን፣ ዝኩኒ እና ሌሎች አትክልት ፍራፍሬዎች ውስጥ እንዲሁም ባቄላ ውስጥ ያገኙታል፡፡
እነዚህን የመመገብ ባህል ማዳበር ለስኳር ህመም የሚወስድ የኢንሱሊን መድሃኒት በአጭር ጊዜ ልዩነት የመውሰድ አጋጣሚን ከማስቀረቱም ባለፈ በቀላል መንገድ መፍትሄ የተጣለበትን ውፍረትዎን በመቀነስ ረገድ የተዋጣለት አማራጭ ሆኖ ተቀምጧል፡፡

– ባገኙት አጋጣሚ ማለትም ሲራመዱ፣ ሲቀመጡ እንዲሁም ምግብ ሲያበስሉ ሆድዎን ወደ ውስጥ ይሳቡት፤ ይሄም የሆድዎ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች እንዲጠነክሩ በማድረግ ቦርጫምነትን ይከላከላል፡፡

– ባቄላን ያዘውትሩ በአንፃራዊነት በሀገራችን በዝቅተኛ ዋጋ ከሚገኙ የምግብ አማራጮች መካከል ሲሆን እንደውም የብዙዎቻችን የዘወትር ብፌ ነው፡፡ ሆን ተብሎም ሆነ ዕድል ባመቻቸው ሁኔታ ይሄን ፍሬ ማዘውተር ጥቅሙ የበዛ አስተዋፅኦ ያጎናፅፋል፡፡

ባቄላን ማዘውተር ለልብዎ ከሚሰጥዎ ጥቅም በላፈ የአጠቃቀምዎ ሁኔታ ባደገ ቁጥር በዛው ልክ ውፍረት ለመቀነስ ይረዳዎታል፡፡ በፋይበር የበለፀገ እንዲሁም ወደ አንጀትዎ የመከማቸት የጊዜ ምጣኔው ዝቅተኛ መሆኑ ሆድዎ በፍጥነት እንዳይጠይቅዎ በማድረግ ለረዥም ጊዜ እንደጠገቡ መቆየት ያስችልዎታል፡፡
– በራስዎ ይተማመኑ፡፡ ምን ያህል ጊዜ የሸንቃጣዎችን ስኬት በማድነቅ እንዲሁም ‹‹እኔም እንደዚህ መሆን እፈልጋሁ ነገር ግን አልችልም›› በማለት ራስዎን በመገደብ ይቆያሉ? የስኬትዎን ጫፍ አይገድቡ፡፡ የፈለጉትን ከማሳካት የሚገድብዎ የእርስዎ አመለካከት ብቻ ነው፡፡
– በማንኛውም አጋጣሚ ጨውን ከምግብዎ ለማራቅ ይሞክሩ፡፡ ሶዲየም (ጨው) የደም ግፊትዎን በመጨመር እና ደምዎን በማቀዝቀዝ ብቻ አይገድብም ተፅእኖው ይልቁንም ከፍተኛና ከሚያስፈልግዎ መጠን በእጅጉ የላቀ ውሃ እንዲወስዱ በማድረግ ለበሽታና ክብደት መጨመር ያጋልጦታል፡፡ ውሃ መጠጣት ለጤና ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ባልተናነሰ መልኩ ጉት ማስከተሉን መዘንጋት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ ነጥብ ነው፡፡

– የመመገቢያ እና የልምምድ ወቅትን በጊዜ መገደብ ያስፈልጋል፡፡ ከእንቅስቃሴ በፊት በምንም ሁኔታ መመገብ አደገኛ ነው የተባለ ሲሆን ከ30 እስከ 60 ደቂቃ ከእንቅስቃሴ በኋላ ቆይቶ መመገብ የተሻለው አማራጭ ነው፡፡ ይሄም የሚፈልጉትን ሰውነት ለመገንባት የሚረዳዎ አካሄድ ነው፡፡

– ውፍረታቸውን ለመቀነስ ያቀዱ ሰዎች ቲማቲም፣ አረንጓዴ አትክልቶችን ስብ የሌለባቸውን ፕሮቲኖች በአመጋገብ እቅዳቸው ውስጥ ያካትታሉ፡፡ ከእቅዳቸው ውጪም አይመገቡም፡፡

– ሁለት ፍሬ እንቁላል ውፍረቶን ለመቆጣጠር ለጠዋት ቁርስዎ ዳቦን ከመጠቀም ጥሩ አማራጭ ተደርጓል፡፡

The post Health: በቀላል አማራጮች ክብደትዎን ይቀንሱ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>