Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ነጻነት፥ ሰብአዊ መብትና፥ ዲሞክራሲ ወሳኝ ግብዓቶች ናቸዉ።

$
0
0

ግንቦት 10 ፤ 2007

Ethiopia-and-the-Horn-628x319የኢትዮጵያ ሳተላይትና ሬዲዮ ድርጅት (ኢሳት) ከምሁራንና ከሌሎች ወሳኝ አካላት ጋር በመተባበር ከግንቦት 1-2 2007 ዓ.ም. ኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ: ለዲሞክራሲ ለሰላምና ለብልጽግና የወደፊት አቅጣጫ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀዉን የሁለት ቀን ሲምፖዝየም እጅግ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል። ስብሰባዉ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት፥ ባህሎችና፥ አመለካከቶች የተስተናገዱበት ከመሆኑን በላይ የአፍሪካ ቀንድ አሁን ያለበትን ጆግራፊያዊ፥ ሃይማኖታዊ፥ ባህላዊ፥ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችና ፍልሰቶችን ትክክለኛ ገፅታ ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት እጅግ የተሳሰረ መሆኑን አሳይቷል። ታሪካችን አብሮነትን ያንጸባርቃል።

ይህ በትክክለኛ ወቅት ላይ የተካሄደዉ ሲምፖዝየም ያተኮረባቸዉ ዋና ዋና ነጥቦች

  1. በሰብአዊ መብት፥ በአስተዳደር፥ በሲቢል ማህበረሰብ፥ በዘዉግ አስተሳሰብ፥ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፥ በጅምላ ስደት፥ በሙስና፥ በህገወጥ የገንዘብ ሸሽት እና ዝዉዉር
  2. በ2007 የኢትዮጵያ ፓርላማ ምርጫ ገፅታ
  3. በአዲስ ፖሊሲ ቀረፃና የወደፊት አቅጣጫ የአመለካከት ለዉጥ
  4. በወደፊት እቅድና አቅጣጫ ላይ አጠቃላይ መግለጫ

የስብሰባዉ ተሳታፊዎች በመፈራረስ ላይ ያሉ ወይም የመፈራረስ አደጋ የተጋረጠባቸዉ አገሮች ላይ የሚታዩ፥ ሆን ተብለዉ ህዝባዊ አመጽ ሊፈጥሩ በሚችሉ፥ የመገንጠል አደጋ በሚያመጡ፥ አለመረጋጋትን እና አሸባሪነትን በሚያስፋፉ የግጭት ምክንያቶችንና መንስኤዎችን ላይ በዝርዝር ትንተናና ክርክር አድርገዉባቸዋል። ኢትዮጵያ በመልካም ጎኗ ለአጠቃላይ አፍሪካ ቀንድ ብሎም ለምስራቅ አፍሪካ በፖለቲካና በስትራቴጂ እጅግ ጠቃሚ አገር መሆኗን የስብሰባዉ ተሳታፊዎች ተስማምተዋል። እምቅ የተፈጥሮ ሃይሏ፥ ከሰዉ ሃብቷና እ.ኤ.አ. በ2014 ካገኘችዉ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ የዉጭ እርዳታ ጋር ተዳምሮ አካባቢዉን በማረጋጋት እና መስመር በማስያዝ በኩል ክፍተኛ ጠቅሜታ ቢኖራትም፥ በአንድ ፓርቲ የበላይነት የምትተዳደር፥ ሃይማኖታዊና የዘዉግ ቁርቋሶ የሚስተናገዱባት፥ ሃብቶቿ በሙስና የሚባክኑባት፥ የፖአቲካና ማህበራዊ መጫወቻ ሜዳዎቿ ተጠርቅሞ የዘጋባት፤ መሰረታዊ የነጻነትና ሰብአዊ መብቶቿ ያልተከበረባት፥ የህግ የበላይነት የሚጣስባት፥ እዉነተኛ መድበለ ፖለቲካ የተከለከለባት አገር በመሆኗ፥ የነበራት አቅም፥ ተሰሚነትና ሃይሏ ቀስ በቀስ እያሽቆለቆለና እየተሸረሸረ መጥቷል።

 

የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች ከ1983 ዓ.ም. በፊት ጀምሮ በጉልበት ስልጣን ላይ የተቆናጠጠዉ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢህአዴግ) ህዝቡን ለማስተዳደር ብቃት እንደሌለዉና ተአማኒነትና እንዳጣ በሙሉ ድምፅ ተስማምተዋል። ኢህአዴግ ህዝቦችን የሚያቃቅሩ ማለትም ፍርሃት፥ ግብታዊነት፥ ሽብርተኝነት፥ የእርስ በእርስ ሽኩቻ የመሳሰሉ እኩይ ሁኔታዎችን በመፍጠር አገሪቷን አደጋ ላይ ከመጣሉም ባሻገር፤ ለሉአላዊነቷም ከፍተኛ አደጋ ሆኖ ተጋርጧል። እነዚህም ችግሮች አብዛኞቹ ወጣቶች በሚሆኑ በመቶ ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን ህይወት ላይ አስነዋሪ ጥላ ሊጥሉ የሚችሉ ናቸዉ። የሰብአዊ መብቶች ድርጅት (Human Rights Watch) በርዕሰ-አንቀጹ “ምርጫዎች፤ የኢትዮጵያ ተምሳሌትነት” በሚል ርዕስ እንዳሰፈረዉ “ካለፈዉ ምርጫ ጀምሮ ገዢዉ ፓርቲ የመሰብሰብና የንግግር መብቶች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እና አፈና አድርጓል።” ገዢዉ ፓርቲ ተቃዋሚዎችንና ተፎካካሪዎችን በተፈበረከ ዉሸት በሽብርተኝነት ይከሳል፥ ይደበደባል፥ ያስራል፥ ወይም አገር ጥለዉ እንዲሰደዱ ያደርጋል። ኢህአዴግ እ.ኤ.አ. በ2014 ብቻ ከሰላሳ በላይ ጋዜጠኞች አገር ጥለዉ እንዲወጡ አድርጓል፤ በቁጥር ያልተገለጹ ተቃዋሚዎችን በማሰር ያለፍትህ እንዲማቅቁ አድርጓል። የፍትህ ስርዓቱ የፖለቲካ ወገንተኝነት ሌላዉ እራስ ምታት ነዉ። እ.ኤ.አ. በ2009 የወጣዉ ፀረአክራሪነት ህግና የመያዶ ድርጅቶችን አዋጅ የሲቢል ማህበራት በመንግስት ላይ ተቃዉሞ ሊያሰሙ በሚችሉ ድርጅቶች ላይ የተቃጣ ስለት ሆኗል።

ሲምፖዚያሙ በቅርቡ የሚደረገዉ ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች የተለየ እንዳልሆነና፤ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት (Human Rights Watch) እንዳለዉ በግንቦት 2007 ዓ.ም. ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በነጻነትና በአግባቡ መንቀሳቀስ እጅግ ከባድ ፈተና ሆኖባቸዋል። አንድ ኢትዮጵያዊ አክቲቪስት፥ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን አስፈሪ ድባብ እና ጭቆናን አስመልክቶ ለሰብአዊ መብቶች ድርጅት “ባደባባይ ሰልፍ ብንወጣ እንታሰራለን፤ ስለፖሊሲ መቀየር ቢሮያቸዉ ሄደን ብንጠይቅ “አሸባሪ” እንባላለን፥ በፍርድ ቤት ብንከስ ነጻነት የለንም፤ ዘብጥያ እንወርዳለን። ስለዚህ ምን ማድረግ ይሻለናል?” ሲል ምሬቱን ገልጿል። ዘጋርዲያን የተባለዉ ጋዜጣ “ኦርዌሊያን” ብሎ በሰየመዉ አይነት ኢትዮጵያ በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር በጭካኔ የምትመራ አገር ሆናለች። የኢትዮጵያ መንግስት በየአመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አንድ ለአምስት (1፡5) ለተባለ የአፈና አደረጃጀትና ለስለላ መዋቅሩ ያባክናል። አንድ ለአምስት የተባለዉ የአፈና አደረጃጀት፥ አንድ ሰዉ የሌሎችን 5 ሰዎች ውሎ (ሰዎቹ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸዉን ግንኙነት፤ ህብረትና፥ እንቅስቃሴ) ቀን በቀን እየተከታተለ ለበላይ ሃላፊዎች ሪፖርት የሚያደርግበት መዋቅር ነዉ። የገዢዉ ፓርቲ ጠላት ተብሎ የተፈረጀ ወይም የተጠረጠረ ግለሰብ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይታሰራል፥ ይደበደባል፥ ይንገላታል። ስልክ ኢንተርኔት ማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፤ ከኢትዮጵያ ዉጭ የየትኛዉም ሚዲያ በአገር ዉስጥ እንዲሰራጭ አይፈቀድም። አፈናዉ መበርታት ለአመጽና ለሽብርተኝነት በር ይከፍታል።

ሲምፖዚየሙ ሂዉማን ራይትስ ዎች በቅርቡ በኢትዮጵያ ፓርላሜንታዊ ምርጫ ላይ ያቀረበዉን ግምገማ እጅጉን ያደንቃል። በቅርቡ የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፖለቲካ ጉዳዮች የበታች ሃላፊ የሆኑት ዊንዲ ሸርማን “ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ አገር ናት። የሚቀጥለዉ ምርጫ ነጻ፥ ፍትሃዊ፥ ታማኝ፥ ግልፅና፥ አሳታፊ ይሆናል” የሚል የተሳሳተ አስተያየት ሰጥተዉ ነበር። ሂዉማን ራይትስ ዎች ከዋሽንግተን ፖስት ጋር ተቀራራቢ የሆነ ርዕሰ አንቀጽ እ.ኤ.አ. በግንቦት 1 2015 “ማስመሰል እንደኢትዮጵያ” በሚለዉ ሓተታዉ “በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጭቆና ዋሽንግተ ማዉገዝ እንጂ ማድነቅ አይገባትም” በማለት የሃላፊዋን አስተያየት ኮንኗል። ፍሪደም ሃዉስ፥ ሂዉማን ራይትስ ዎች፥ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፥ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ፕሮጄክት፥ የጋዜጠኞች ተከላካይ ድርጅት፥ ኢንተርናሽናል ሪቨርስ እና ኢትዮጵያዉያን ዊንዲ ሸርማን ንግግራቸዉን እንዲያስተባብሉ ለአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የተቃዉሞ ደብዳቤ ፅፈዋል። የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች ከላይ ከተገለጸዉ ርዕሰ አንቀጽ ጋር በመስማማት ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ አገር ለመሆኗ ምንም በመረጃ የተደገፈ ነገር አለመኖሩን አስምረዉበታል። በተቃራኒዉ የኢትዮጵያ መንግስት ተስፋ የሚያስቆርጥና ፍርሃት የነገሰበት አፋኝ ስርዓትን በመፍጠር በቋፍ ላይ ያለችዉን አገር ወደባሰ አዘቅት ዉስጥ እየገፋት ይገኛል። በኢትዮጵያ ዉስጥ ሰፍኗል የተባለዉ የዉሸት ሰላምና መረጋጋት በጉልበትና በአፈና ላይ የተመሰረተ ነዉ።

ይሁን እንጂ የአንድ አገር አለመረጋጋት ወደመበታተን ሊመራ እንደሚችል የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች ያምናሉ። ጭቆናዉና አፈናዉም ወደማያባራ የእርስ በእርስ ህዝባዊ አመጽና ጦርነት ሊሸጋገር ይችላል። ይህ ድርጊት ሊቆም የሚችለዉም የምራባዊያን ዲሞክራሲያዊ አገራት በተለይም አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት የዲሞክራሲ እሴቶችንና፥ የህግ የበላይነትን እንዲያከብር የተፅእኖ ሃይላቸዉን ማሳረፍ ሲችሉ ብቻ ነዉ። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉን ከገጠማቸዉ አስከፊ ሁኔታዎች አንጻር ሲምፖዚየሙ የሚቀጥሉትን ዉሳኔዎች በማስተላልፍ የመትሄ ሃሳቦችን አስቀምጧል።

  • ክርስቲያ ወንድሞቻችን በአይኤስ በግፍ መታረዳቸዉን፥ ህግ አክባሪ ኢትዮጵያዉያን በደቡብ አፍሪካ መገደላቸዉን፥ በየመን ኢትዮጵያዉናንና ሌሎች በአየር የመደብደባቸዉን ድርጊት እናወግዛለን፤ የኢትዮጵያን መንግስትም ህዝብን ያማከለ አሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርግ የስራ ፈጠራ እድገት መርሃ ግብር እንዲያወጣ እንጠይቃለን።
  • በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም ተቃዋሚዎች፥ የሲቪል፥ ፕሮፌሽናልና የሃይማኖት ድርጅቶች፥ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ቡድኖች፥ አክቲቪስቶችና ምሁራን አንድነትን በብዘሃነት መነጽር እንዲያዩትና እንዲደግፉ፥ ለአንድ አላማ አብሮ ለመስራት ቆርጠዉ እንዲነሱና አማራጭ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩባት፥ ዲሞክራሲያዊነት የጎለበተባት፥ ሁሉን አቀፍ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እንዲረባረቡ እንጠይቃለን።
  • ሁላችንም የተገነዘብነዉ ነገር የኢትዮጵያ ህዝብ፥ አፍሪካ ቀንድና የምራባዉያን አገሮች በዘላቂነት የሰብአዊ መብት እንዲከበር፥ ነጻነት እንዲኖር፥ ተጠያቂነትና አሳታፊነት እንዲጎለብት ይፈልጋሉ፤ ለዚህም ይታገላሉ። በመሆኑም የአሜሪካ መንግስት ትርጉም ያለዉ ለዉጥ ለማምጣት በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደር የፖለቲካ ምህዳር እንዲሰፋ፥ ብሄራዊ እርቅ እንዲደረግና፥ ሁሉም አካላት የስልጣን ተካፋይ እንዲሆኑ በማመቻቸት ችግሮቹ ከመባባሳቸዉ በፊት አወያይቶ ሊፈታ ይገባል።
  • የአሜሪካ መንግስትን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የሚያወጣቸው የማስመሰል መግለጫዎችና የተለሳለሱ አቋሞች ወይም አቀራረቦች እንደማይሰሩ እንዲረዳልን እንፈልጋለን። አሜሪካ ሚዲያን፥ ፖለቲካ ፓርቲዎችንና ተቃዋሚዎችን ለሚያፍነዉ መንግስት ትርጉም ያለዉ ለዉጥ እስካልመጣ ድረስ ድጋፏን እንድታቆም እንጠይቃለን።
  • አለም አቀፍ ማህበረሰብ አባላት በተለይም ምዕራባውያን ለጋሽ አገራት፥ መንግስታትና የዉጭ ኢንቨስተሮች ኢትዮጵያ ሚሊዮኖችን ከስራ ዉጭ ያደረገች፥ ኢፍትሃዊነት እንዲነግስባት የተደረገች፥ ሁሉንም ቡድኖች ያላማከለ የአስተዳደር ችግር ያለባት አገር መሆኗን እንዲገነዘቡ እንፈልጋለን። በቅርቡ በአይስ (ISIS) የተደረገዉ የጅምላ ግድያ ኢትዮጵያ ዉስጥ አለ የተባለዉ እድገት የተጣመመ ለመሆኑ አመላካች ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በዉጭ አገር ስራ ለማግኘት ሲሉ ህይወታቸዉን ለአደጋ በመስጠት ለህገወጥ የሰዉ አዘዋዋሪዎች ገንዘብ ይከፍላሉ። የኢትዮጵያ መንግስት ወደ 400 ገደማ የሚጠጉ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያጋብሱ የህገወጥ ሰዉ አዘዋዋሪ ደላሎችንና ድርጅቶችን እንዲዘጋና የወጣቶች የስራ ፈጠራ ፕሮግራሞችን በአስቸኳይ እንዲነድፍ እንጠይቃለን።
  • የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈታ፤ የፀረሽብርተኝነትና የመያዶ ህጎችን እንዲሽራቸዉ እንጠይቃለን።
  • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር፥ የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ ማህበራት ወደኢትዮጵያ ቢመለሱ ችግር ለሚደርስባቸው በሊቢያና በየመን ዉስጥ በችግር ለሚሰቃዩ የኢትዮጵያ ስደተኛ ወገኖች ከለላ እንዲሰጣቸዉ በአሜሪካና በሌሎች አገሮች ጥገኝነት እንዲያገኙ እንዲያመቻችላቸዉ ስንል እንጠይቃለን። የምራባዉያን መንግስታት፥ ጃፓን እና ሃብታም አገሮች ለኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን ፎር ማይግሬሽንና (IOM) ለሌሎች ድርጅቶች ለስደተኞች ግልጋሎት የሚዉል ገንዘብ እንዲለግሱ እንጠይቃለን።
  • የአሜሪካ የኮንግሬስ አባላት የሰብአዊ መብት ጥበቃ፥ የህግ የበላይነትና ዲሞክራሲን ያግዛል የተባለለትን የ2007 የዲሞክራሲና ተጠያቂነት ረቂቅ ህግ እንደገና እንዲያንሸራሽር በጥብቅ እንጠይቃለን። ኢትዮጵያዉያን ነጻነት፥ ክብር፥ የሰብአዊ መብት ከለላ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ከመቼዉም ጊዜ በላይ እንደሚያስፈልጋቸዉ እናምናለን።

 

የስብሰባዉ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰብሳቢዎቹን ቀልብ የሳቡ ርዕሶችን በጊዜ እጥረት ምክንያት በበቂ ሁኔታ ሳያወያይባቸዉና ሳይሸፍናቸዉ ቀርቷል። ለወደፊቱ ግን በእነዚህ ርእሶች ላይ በጥልቀት እንድወያይ መድረኮችን ያመቻቻል።  ከርዕሶቹ በጥቂቱ

  1. የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት
  2. ዕርቅና ሰላም በአፍሪካ ቀንድ
  3. አዲሱ ሚዲያ (ፌስቡክ፥ ትዊተር፥ ዩቲዩብ፥ ወዘተ) በመንግስት፥ በዲሞክራሲ፥ እና በሰብአዊ መብት ግንዛቤ ዙሪያ ላይ ላይ ያለዉ ሚና
  4. ተቀራራቢነት ያላቸዉ ሌሎች ሃሳቦችም ይስተናገዳሉ።

 

Contact information:

 

ጥያቄ ካለዎት  ኢሜይል ethio-horn@ethsat.com ሊያገኙን ይችላሉ። በስልክም እንዲሁ በ571- 335-4964 ይደዉሉልን።

 

The post ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ነጻነት፥ ሰብአዊ መብትና፥ ዲሞክራሲ ወሳኝ ግብዓቶች ናቸዉ። appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>