Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: የሚቹ ቀጣይ ዕጣ

$
0
0

michu swansa city

ባለፈው የውድድር ዘመን ሚቹ 30 ሚሊዮን ፓውንድ ተገምቶ ነበር፡፡ ነገር ግን በኦክቶበር 2013 ወዲህ ኳስ እና መረብ አላገናኘም፡፡ በአንድ ወቅት የስዋንሲ ጨራሽ አጥቂ የነበረው ስፔናዊ ራሱን በውሰት በናፖሊ የተጠባባቂ ወንበር ላይ ተቀምጦ አገኘው፡፡ በዚያም ቢሆን ንቁ ተሳትፎ እያደረገ አይደለም፡፡
የስዋንሲ ባሳለፈው የመጀመሪያ የውድድር ዘመን የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ተጨዋች በጉዳት እና በቂ ተሳትፎ አለማድረግ ምክንያት አቋሙ ተንሸራተተ፡፡ ለናፖሊ ተሰልፎ በተጫወተባቸው ስድስት ጨዋታዎች አንድም ጎል አላስቆጠረም፡፡

የስዋንሲው አሰልጣኝ ጋሪ ሞንክ በመጪው ክረምት ከተጫዋቹ ጋር በቆይታው ዙሪያ ይነጋገራል፡፡ ለመወሰን እንደሚቸገርም ይጠበቃል፡፡ የሞንክ ውሳኔ ምን ይሆን? የክለቡ የቀድሞ ኮከብ ጎል አግቢ በሊበሪቲ ስታዲየም እንዲቆይ ያገባዋል ወይስ የ29 ዓመቱ አጥቂ በኮንትራቱ ላይ ቀሪ የአንድ ዓመት ጊዜ እየቀረበው በዝቅተኛ የዝውውር ሂሳብ አሳልፎ ይሸጠዋል?
‹‹ከሚቹ ጋር መልካም ግንኙነት አለን፡፡ የቡድን ጓደኞች ስለነበርን በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡ አሰልጣኝ ከሆንኩ በኋላ ግንኙነታችን ቀጥሏል›› ይላል ሞንኮ፡፡ ‹‹ባለፈው ክረምት በሚገባ አነጋግሬዋለሁ፡፡ መሄድ እንደፈለገ ተመለከትኩ፡፡ እኔም በሃሳቡ ተስማማሁ፡፡ በመጪው ክረምት የሚፈጠረው ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡››

‹‹ድንቅ አጀማመር››

ስዋንሲ እርሱን ከራዮ ቫ ዩካኖ ለማዘዋወር 2 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍሏል፡፡ የእግር ኳስ ተንታኞች የ2012/13 የውድድር ዘመን ትንበያቸውን ሲሰጡ እርሱን ዘልለውት ነበር፡፡ እርሱ ግን ወደ ፕሪሚየር ሊግ መምጣቱን በሚያስገርም መልኩ አወጀ፡፡ ስዋንሲ በመጀመሪያ ዕለት ጨዋታ ኪውፒአርን 5-0 ሲረታ ሁለት ጎሎችን አስቆጠረ፡፡
ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ስዋንሲ የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ መምራት ጀመረ፡፡ ክለቡ ሶስቱንም ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ሚቹ በሶስቱም ጎል አስቆጥሯል፡፡ ግዙፉ ባለረዥም ፀጉር አጥቂም ወዲያውኑ መነጋገሪያ ሆነ፡፡ አሰልጣኝ ማይክል ላውድሮፕ እርሱን በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለፁት ‹‹የውድድር ዘመኑ ምርጥ ግዢ›› በማለት ነው፡፡ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ይህንን የመሰለ ተሰጥኦ ሳይመለከቱት እንዴት ሊያመልጣቸው እንደቻለ የምልመላ ዲፓርትመንት ባልደረቦቼን አነጋግራለሁ በማለት ቀልደዋል፡፡ የተወሰኑ ታላላቅ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በዙሪያው እያንዣበቡ እንደሆነም መነጋገር ጀመረ፡፡ በጃንዋሪ 2013 ስዋንሲ አጥቂውን አዲስ ኮንትራት አስፈረመው፡፡ በተሻሻለው ኮንትራቱ የተነቃቃው ስፔናዊ አጥቂ በሁሉም ውድድሮች ላይ 22 ጎሎችን አስቆጠረ፡፡ የካፒታል ካፕ ዋንጫን ባሸነፉበት የማይረባ የውድድር ዘመን የስዋንሲ የውድድር ዘመኑ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ ተመረጠ፡፡
michu swansa

ለብሔራዊ ቡድን የተጫወተው አንድ ጊዜ ብቻ ነው
የሚቹ ዕድገት ማቆሚያ ያለው አይመስልም ነበር፡፡ ሁለተኛ የውድድር ዘመኑን በስዋንሲ ሲጀምር ድንቅ ብቃቱ አብሮት ቀጠለ፡፡ ስዋንሲ በዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ማልሞን 4-0 ሲያሸንፍ የስዋንሲን የዩሮፓ ሊግ ዘመቻ የመጀመሪያ ጎል አስቆጠረ፡፡ ከሜዳቸው ውጪ ቫሌንሲያን 3-0 ሲያሸንፍ ኳስ እና መረብ አገናኘ፡፡
የሚቹ እንቅስቃሴ አንፀባራቂ ነበር፡፡ የስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቪሴንቴ ዴል ቦስኬን ቀልብ ገዛ፡፡ በ2013 ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ቢላሩስን ሲገጥሙ የመጀመሪያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን አደረገ፡፡ ዣቪ እና ሴስክ ፋብሪጋዝን የመሳሰሉ ተጨዋቾችን የያዘው ቡድን አካል ሆነ፡፡ ነገር ግን ያ ጨዋታ ብቸኛው አጋጣሚ ሆነ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ የውድድር ዘመኑ ወደ አልሆነ አቅጣጫ ሲጓዝ ተመለከተ፡፡ ከአንድ ወር በኋላ በደቡብ ዌልስ ደርቢ በካርዲፍ ሲቲ 1-0 ሲሸነፉ ቀላል የሚመስል የቁጭምጭሚት ጉዳት አጋጠመው፡፡ በዲሴምበር ወደ ሜዳ ተመልሶ በሁለት ጨዋታዎች ላይ ቢሰለፍም እስከ ማርች ድረስ ከሜዳ ተገለለ፡፡ በውድድር ዘመኑ ለመጨረሻ ጊዜ ያስቆጠራት ጎል የተገኘችው በኦክቶበር ነበር፡፡
Michu

በስዋንሲ ጥሩ የማይባል ሁለተኛ የውድድር ዘመን ካሳለፈ በኋላ ሚቹ ለአንድ የውድድር ዘመን በሚዘልቅ የውሰት ስምምነት ወደ ናፖሊ አመራ፡፡ አላማው ወደ ቀድሞ ብቃቱ ለመመለስ እንደ መንደርደሪያ ሊጠቀመው ነበር፡፡ ሆኖም ወደ ጣልያን ያደረገው ጉዞ ሚቹ ያለመውን መነቃቃት አላስገኘለትም፡፡ ስፔናዊው በዚህ የውድድር ዘመን ተሰልፎ መጫወት የቻለው በስድስት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ ጉዳቶች የ29 ዓመቱን አጥቂ ዕድገት አስተጓጉሎበታል፡፡ ነገር ግን ለጨዋታ ብቁ በሚሆንበት ጊዜ እንኳን የመሰለፍ ዕድል የሚያገኘው ከጎንዛሎ ሂግዌይን፣ ሎሬንዞ ኢንሴፔ፣ ድራይስ ማርቴንስ፣ ማግሎ ጋቢያዲን፣ ማሬክ ሃምሲክ እና ሌሎች የፊት መስመር ተሰላፊዎች በኋላ ነው፡፡
ሞንክ ሚቹ ወደ ሙሉ ጤንነቱ ሲመለስ የቀድሞውን ብቃቱን መልሶ እንደሚያገኝ ያምናል፡፡ ‹‹ለዚህ ያበቁት ጉዳቶቹ ናቸው፡፡ ለጨዋታ ብቁ ሆኖ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየት አልቻለም፡፡ ያንን ማድረግ ለተጨዋች ፈታኝ ነው፡፡ ሌላ ምንም አይደለም፡፡ ዕድለኛ አልነበረም፡፡ ከጉዳት ነፃ ሆኖ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየት ቢችል ተመሳሳዩን ብቃት መመልከት እንችላለን፡፡›› በማለት ለአጥቂው ያለውን መልካም ስሜት ይገልፃል፡፡

ጊግስ ወንድሙን ይቅርታ ጠየቀ
የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ክንፍ ተጫዋች ሪያን ጊግስ ይቅርታ ለመጠየቅ ወደ ወንድሙ መደወሉ ታምኗል፡፡ የቀያይ ሰይጣናቱ ታሪካዊ ተጨዋች ከወንድሙ ሮድሪ ሚስት ናታሻ ጋር ለስምንት ዓመታት ፆታዊ ግንኙነት እንደነበረው ይፋ ከወጣ በኋላ የወንድማማቾቹ ግንኙነት ሻክሮ ነበር፡፡ አሁን ያንን ግንኙነት ለማደስ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
‹‹ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሪያን ሳይታሰብ ለሮድሪ ደወለለት፡፡ ሮድሪ ጥፋት የሰራው እርሱ ስለሆነ ቀድሞ ሊደውሉልኝ የሚገባው ሪያን ነው በሚለው አቋሙ ፀንቶ ነበር›› በማለት ለወንድማማቾቹ ቅርበት ያለው ምንጭ ተናግሯል፡፡ የ41 ዓመቱ ሪያን እና የ38 ዓመቱ ሮድሪ የፋሲካ ዕለት በአንድ ቡና ቤት ውስጥ አንድ ላይ ታይተዋል፡፡ በዚያ የነበረ እንግዳ ‹‹ዳግም ጥሩ የአብሮነት ቆይታ እያደረጉ ነበር›› ብሏል፡፡
ጉዳዩ ይፋ ከሆነ በኋላ ለሶስት ዓመታት አልተነጋገሩም ነበር፡፡ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ሮሪ በቻናል ፋይቭ ላይ በሚተላለፍ በክህደት ዙሪያ በሚያጠነጥን ፕሮግራ ላይ ተሳታፊ ሆኖ ነበር፡፡ ‹‹አንድ ቀን ናታሻ ተሰወረችብኝ፡፡ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ሄጄ እግር ኳስ ተጫወትኩ እና በጊዜ ተኛሁ፡፡ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ስነቃ ቤት ውስጥ አልነበረችም፡፡ 12 ሰዓት ላይ እናቷ ጋዜጣ እና ደብዳቤ ይዛ በር አንኳክታ ገባች፡፡ እየሆነ ያለውን ነገር ያወቅኩት ከእናቷ ጎን ቁጭ ብዬ ጋዜጣውን በማንበብ ነው›› ሮድሪ ይቀጥላል፡፡
‹‹ደውዬ በጋዜጣ ላይ የወጣው ታሪክ እውነት ነው ወይ ብዬ ጠየቅኩት፡፡ በጭራሽ ብሎ አስተባበለ፡፡ በወቅቱ ማንን ማመን እንዳለብኝ አላወቅኩም ነበር፡፡ ሁለት ልታምናቸው የሚገባ ሰዎች በአጠገብህ ኖረው ሁለቱንም ማመን ትፈልጋለህ፡፡ ነገር ግን ናታሻ የፅሑፍ መልዕክቶችን አሳየችኝ፡፡ ሪያን የላካቸውን የራሱን ፎቶግራፎችም ተመለከትኩ፡፡
‹‹በኋላ ላይ ምንም ማለት እንዳልሆነ እና ከሚስቱ ጋር ከወሲብ ያለፈ ነገር እንዳልነበራቸው ነገረኝ፡፡ ለወሲብ ብሎ ቤተሰቤን አፈረሰ፡፡ ተስፋ ቆርጬ እርሱን ላለመናገር ወሰንኩ፡፡ ጥሩ ሰርተሃል፡፡ ደስ ይበልህ ወንድሜ የሚል የፅሑፍ መልዕክት ላኩለት፡፡›› ሮድሪ እና ናታሻ ለትዳራቸው ዕድል ለመስጠት ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም፡፡ በ2013 በፍቺ ተለያዩ፡፡

The post Sport: የሚቹ ቀጣይ ዕጣ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>