ሊቢያ ውስጥ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግፍ የተሞላበት ግድያ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት በማለት የጠየቁ የሰራዊት አዛዦች እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ::
ለደህሚት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው የምዕራብ እዝ 7ኛ ሜካናይዝድ የሬጅመንት ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሙሉአለም የተባለ መኮነን የኢህአዴግ ገዥው መንግስት በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በየመን በኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ላለው አስቃቂ ግፍ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት ብሎ ስለጠየቀ ብቻ ፀረ ሰላም ነህ ተብሎ ባህር ዳር መኮድ በተባለ ቦታ እንደታሰረ ምንጮቻችን አስታወቁ።
ስርዓቱ በአይ ኤስ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ፍላጎት ስለሌለው የዜጎቻችንን ደም መመለስ አለብን የሚል ጥያቄ ለሚያነሱ ሰዎች እንደ ጠላት እያዬ ወደ እስር ቤት እያስገባቸው እንደሚገኝ የገለፀው ይህ መረጃ የመከላከያ ሰራዊትም በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ላለው የሚያሳዝን ተግባር ዋነኛ ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ ስርዓት መሆኑን በተደጋጋሚ እየገለፁ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ ገልጿል።
The post በአይሲስ ላይ ኢትዮጵያ የሃይል እርምጃ መውሰድ አለባት ያሉ የሠራዊቱ አዛዦች ታሰሩ appeared first on Zehabesha Amharic.