Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሊቢያ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን እስካሁን የ14ቱ ማንነት ተለይቷል * አያልቅበት ስንታየሁና ብርሃኑ ጌታነህ ማንነታቸው ተለይቷል

$
0
0

birhanu getaneh

Ayalkibet sintayehu
(ዘ-ሐበሻ) በሊቢያ በአይሲኤል አንገታቸውን በመታረድ እና በጥይት በመመታት ሕይወታቸውን ያጡት 28 ኢትዮጵያውያንን ማንነት ለማወቅ የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው:: እስካሁን የ12ቱ ማንነትን በዘ-ሐበሻ ላይ አቅርበንላችሁ ነበር:: ዛሬ ደግሞ የ2ቱ ማንነት ታውቋል በሚል በመንግስት ሚድያዎች ተዘግቧል::

እንደ መንግስት ሚድያዎች ዘገባ አሁን ደግሞ አቧሬ እና ገርጂ አካበቢ ነዋሪ የነበሩ ሌሎች ወጣቶች በአይ ኤስ መገደላቸው ታውቋል። ወጣቶቹ አያልቅበት ስንታየሁ እና ብርሃኑ ጌታነህ ይባላሉ።

አያልቅበት የ30 አመት ወጣትና ከሶስት አመት በፊት ወደ ሱዳን ያቀና ሲሆን፥ ከእናቱ ጋር ሲኖር የነበረ መሆኑን ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ ያመለክታል::
አያልቅበት ስንታየሁ ብቸኛ ልጃቸው እንደነበርም እናቱ ተናግረዋል ።

ብርሃኑ ጌታነህ ደግሞ ባለትዳር እና በፎቶግራፉ ላይ እንደምንመለከተው የስምንት እና የአራት አመት ልጆች ያሉት ወጣት ነበር ። በአዲስ አበባ አቧሬ አካባቢ ይኖር የነበር ሲሆን፥ ከአገር ከወጣ አራት ወር አልፎታል። ባለቤቱ ብርቱካን ጌቱ ስትባል በአሁኑ ወቅት ባለቤቷን ማጣቷ ተደራራቢ ችግር ላይ እንደጣላት ገልፃለች።

እስካሁን ያወቅናቸው፦
1. ኢያሱ ይኵኖአምላክ
2. ባልቻ በለጠ
3. ዳንኤል ሐዱሽ
4. ቡሩክ ካሳሁን
5. ኤልያስ ተጫኔ
6. በቀለ ታጠቅ
7. በቀለ አርሰማ
8. ዳዊት ሐድጉ
9. መንግሥቱ ጋሼ
10. ጀማል ራህማን
11. አወቀ ገመቹ
12. እንዳልክ ሐጎስ አየለ
13. ብርሃኑ ጌታነህ
14. አያልቅበት ስንታየሁ

The post በሊቢያ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን እስካሁን የ14ቱ ማንነት ተለይቷል * አያልቅበት ስንታየሁና ብርሃኑ ጌታነህ ማንነታቸው ተለይቷል appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles