Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሴቶች ፕሪምየርሊግ የአዳማ ከተማ ተጫዋቿ ሕይወት በመርዝ ማለፉ ተዘገበ

$
0
0

በሴቶች ፕሪምየር ሊግ የደቡብ ምስራቅ ዞን የ12ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማክሰኞ ቀን ሚያዚያ 20/2007 ተከናውነዋል ከነዚህም መካከል አሰላ ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከአዳማ ከተማ ጋር 1ለ1 የተለያዩበት ጨዋታ ይገኝበታል:: በዚህ ቀን ለክለቧ አዳማ ግቧን ያስቆጠረችው የኔነሽ ጌቱ ወይም በጓደኞቿ አጠራር የኑ ነበረች በማግስቱ ረቡዕ ከረፋድ 3 ሲል ከቡድኑ አባላት ጋር ናዝሬት ማረፊያ ካምፓቸው ውስጥ ነበረች ሀኪም ቤት የተኛች አያቴን ልጠይቅ ብላ ፈቃድ ወስዳ ሄዳለች በኋላ ላይ ወደ ክለቡ የደረሰው ወሬ መልካም አልነበረም ተጫዋቿ መርዝ በመጠጣት ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች ቀደም ብሎ ሂወቷን ለማዳን ወደሆስፒታል የወሰዳት ወንድሟ ነበር ነገር ግን ሳይሳካለት ቀርቷል።
merz
ድሬቲዩብ የቡድኑን ቡድን መሪዋን ወ/ሮ ጀሚላ ኡስማንን አነጋግሯል << በተብራራ መልኩ ስለምክንያቱ የምናውቀው ነገር የለም ግን ከኛ አያቴን እጠይቃለሁ ብላ ነበር የወጣችው ካምፕ ቱሀን አለ ብላ መርዙን ስለማግኘቷ ሰምተናል ገዝታ ነው ወይም ከሀኪም ቤቱ አግኝታ ስለሚለው ግን ማወቅ አልቻልንም ወሳኝ የቡድናችን ተጫዋች ነበረች በጣም አዝነናል ነፍሷን ይማርልን>> ብለዋል::

ከ2005 ጀምሮ የቡድኑ አባል የነበረችው የኔነሽ ጌቱ የቀብር ስነስርአቷ ሀሙስ ሚያዚያ 22 በናዝሬት መድሀኔአለም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።

ምንጭ – ድሬ ቲዩብ

The post በሴቶች ፕሪምየርሊግ የአዳማ ከተማ ተጫዋቿ ሕይወት በመርዝ ማለፉ ተዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles