የደህሚት ድምጽ እንደዘገበው በገዢው የኢህአዴግ ስርአት ውስጥ የሚገኙ የማእከላዊ እዝ ሰራዊት አባላት ወደ ከተሞች በመሄድ ህውከት እየፈጠሩ እርስ በራሳቸው እየተገዳደሉ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለፁ።
እንደምንጮቻችን መረጃ መሰረት ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ላይ በሚገኝ “ብሄራዊ ሆቴል” ውስጥ ሚያዚያ 4/2007 ዓ/ም የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑት ወታደሮች መጠጥ በመጠጣት እርሰ በራሳቸው ተጣልተው ከፍተኛ ግርግር እንደተነሳ የገለፀው መረጃው ህውከት ፈጣሪ ከሆኑት የሰራዊቱ አባላትም መቶ አለቃ ደሳለኝና ምክትል መቶ አለቃ አየለ ናሳ የተባሉት መሆናቸውና በጠርሙስና ሌሎች የሆቴሉን ንብረት በማንሳት እየተወራወሩ መደባደባቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በተከሰተው ብጥብጥ ሁለቱም መኮንኖች በከባድ መጎዳታቸውና በተለይ ምክትል መ/አለቃ አየለ ናሳ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ከሁለት ቀን በኋላ እንደሞተ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
The post የማዕከላዊ ዕዝ አባላት በከተማ ውስጥ የሠራዊቱ እርስ በራሳቸው እየተገዳደሉ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.