Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ከኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሁሉን አቀፍ አማራጭ ሀይል የማቋቋም ሂደትና ወቅታዊነቱን አስመልክቶ የተሰጠ የጋራ መግለጫ

$
0
0

ሚያዝያ 17፣ 2007  (April 25, 2015)

entc-logo-5Ethiopian_Youth_Movement_Logoሀገር በቀሉ የወያኔ አፓርታይድ ሰርአት በሃገር ውስጥ በህዝባችን ላይ የሚያደርገው  የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ አፈና፤ እስር፤ ግድያ፤ በዘር ከፋፍሎ ማጋጨት፤ ዘረፋና ሀገራዊ ጥቅምን ለባእዳን አሳልፎ መሸጥ የዘወትር ተግባራቶች ከሆኑ አመታት ተቆጥረዋል። ይህንን ግፍ በመሸሽ በአፍሪካና በአረብ አገሮች በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን የዜጎቹን መብት የሚያስጠብቅ ኣትዮጵያዊ መንግስት ባለመኖሩ እጅግ አሳዛኝና ዘግናኝ ለሆኑ ስቃይና ግድያወች ተጋልጠዋል። ይህን ፋሽስታዊ ድርጊትና ተደጋጋሚ ብሄራዊ ቅሌት ለማስቆም የወያኔን መሰሪ ስርአት ከስሩ ነቅሎ ለመጣል በቆራጥነት በጋራ መታገል ብቸኛው መፍትሄ ነው።

ህዝብንና አገራችንን ወደከፍተኛ አደጋ እየገፋ የሚገኘውን ይህን ፋሽስታዊ ስርአት ማስወገድ ያለመቻላችን ምክንያትና የጋራ ችግራችን፤  የኢትዮጲያ ዲሞክራሲ ሃይሎች በማስተባበርና በአንድ ማእከል በመንቀሳቀስ የነጻነት ትግሉን ማካሄድ የሚችል፤ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፍ ህብረተሰቡ አማራጭ የሚሆን ሁሉን አቀፍ ያማራጭ ሃይል ማቋቋም ያለመቻላችን ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ምክር ቤት (ENTC) እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና (EYNM)  ቀደም ሲል ጀምሮ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አብሮ ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል። በጁላይ 2013፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ  በዋሽንግተን ዲሲ ባዘጋጀው ታሪካዊ የምክክር ጉባኤ ላይ፤ በርካታ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በመገኘት በተሳተፉበት ወቅት ሁለቱ ድርጅቶች ትግሉን በመደጋገፍ ለማካሄድ በተለያዩ ነጥቦች ላይ የመግባቢያ ሰነድ (Memorandum of Understanding) በመፈራረም ለህዝብ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይህንን መሰረት በማድረግ፤ በሃገራችን ኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የተሳካ እንዲሆንና በተለያዩ ጐራዎች በተናጥል የሚደረጉ ትግሎች የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘውን ነፃነት እውን ለማድረግ በቂ አለመሆናቸውን በመረዳት፤ ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ሃይል መኖር እጅግ አስፈላጊ፣ ወሳኝና፣ ወቅታዊ መሆኑን በመገንዘብ፤ የአማራጭ ሃይል የማውጣት ሂደቱን በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ተግባራዊ ለማድረግ፤ የሁለትዮሽ ውይይቶችንና ግንኙነቶችን ወደወል ባስቸኳይ በማሸጋገር በጋራ ለመስራት ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሰናል።

በዚህ አጋጣሚ ዛሬም እንደወትሮው ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ  ይህን ወቅታዊ አጀንዳ የግል ጉዳይ በማድረግ አስተዋጽኦና ግፊት ያደርግ ዘንድ አገራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC) እና

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)

The post ከኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሁሉን አቀፍ አማራጭ ሀይል የማቋቋም ሂደትና ወቅታዊነቱን አስመልክቶ የተሰጠ የጋራ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>