Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ኢትዮጵያ ውስጥ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ ነው –አደጋ ላይ ነን!

$
0
0

gay-flag
ካስደነገጥኳችሁ አዝናለሁ ግን በጣም መደንገጥ አለባችሁ፡፡በመላው የአዲስ አበባ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤቶች ማለት ይቻላል በነSave The Children ፊት አውራሪነት እየተሰጠ ያለው የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ሳረዳችሁ ከፍተኛ ሀዘን እየተሰማኝ ነው፡፡እስካሁን ከ40 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ት/ቤቶች ውስጥ ለውስጥ በአንድ ክፍለ ጊዜ በ120 ብር በተቀጠሩ የየትምህርት ቤቱ የባዮሎጂና የአይሲቲ መምህራን አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡ሁለት አይነት ነው ትምህርቱ፡፡Life Skill (ላይፍ እስኪል) እና Comprehensive Sexuality Education (ከምፕሬኤንሲቭ ሴክሽዋሊቲ ኤጁኬሽን) የሚባሉ፡፡በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ዙር ስልጠናው አልቋል፡፡ሁለተኛ ዙሩ የተግባር ትምህርት ነው፡፡ በቪዲዮና በተግባር እንቅስቃሴ የተደገፈ፡፡ ከሚሰጡት ትምህርቶች መካከል FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) እና MASTERBATION (ማስተርቤሽን)የሚባሉ የልቅ ወሲብ አይነቶች አሉበት፡፡ ልቅ ስል በ FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) ጊዜ ጾታ ሳይለይ የፈለጉትን ደፍሮ መሳም ሲሆን በ MASTERBATION (ማስተርቤሽን) የሚለው ደግሞ ሴቶችም ወንዶችም በቪዲዮ የታገዘ የ Pornography (የፖርኖ) ፊልሞች እያዩ እንዲተገብሩት የታሰበ ነው፡፡ ለዚህም አላማ ከየትምህርት ቤቱ ጎበዝ የተባሉ ተማሪዎች ተመርጠው ተዘጋጅተዋል፡፡

ጉዳዩ እስከ ትምህርት ሚኒስተርና ቢሮ ቢደርስም እስካሁን መልስ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡አንዳንድ የክፍለ ከተማ ሀላፊዎች እንዳሉት እነSave The Childern (ሴቭ ዘቺልድረን) በኢትዮጵያ የተለያዩ ስራዎች ስለሚሰሩልን አቁሙ ብንላቸው ግንኙነታችን ይበላሻል፡፡በላይ አመራሩም ዘንድ ያለው እሳቤና አቋም ይሄ ነው ብለዋል፡፡የተከበራችሁ የአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፤ ወላጆች ፤ቤተሰቦች ይህ የምነግራችሁ ነገር ተራ አሉባልታ አለመሆኑን በተለያየ ጊዜ ለማሳያ የተለጠፉ መረጃዎችን አይታችሁ መፍረድ ትችላላችሁ፡፡ የተከበራችሁ ተማሪዎች ወላጆች እና በዚህ ጉዳይ እንደ እኔ የተንገበገባችሁ ሁሉ አደጋ ላይ ነን፡፡በተለይ ድርጅቶቹ ነገሩን እንዲሰሩላቸው የመረጧቸውን ሰዎች ለመግዛት እያወጡት ያለው ምራቅ የሚያስውጥ ገንዘብ በየክፍሉ ከሚያስተምሩላቸው መምህራንና ከተባባሪ የትምህርት ቤት አስተዳደሮችም አልፎ እስከ ላይ ድረስ ኪስ ሳያሞቅ አልቀረም፡፡ የእናንተ እርዳታ ቆፍጠን ያለ ውሳኔ ያስፈልጋል፡፡

ተማሪዎችና ወላጆች በአዲስ አበባ በብዛት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ቢያነጣጥርም ነገሩ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሌሎች ክልልሎች ግን እስከ ታችኛው ክፍል ድረስ በስነተዋልዶ፣በጸረኤድስና በስርአተ ጾታ ሰበብ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ሳረጋግጥላችሁ በአውነት ነው፡፡ ስለዚህም ተማሪዎች፣ ወላጆች የሚመለከታችሁ ሁሉ አይናችሁን ወደ ትምህርት ቤት አንሱ!! ተማሪዎች በገንዘብ በተደለሉ ግለሰቦች እተረጨባቸው ያለውን መርዝ አስቁሙ፡፡በተለይ በአሁኑ ወቅት አስረኛና አስራ ሁለተኛ ክፍሎች ትምህርት በጨረሱበት ጊዜ እየሆነ ያለው ተማሪዎችን በክረምት ትምህርትና ስልጠና ሰበብ ለዚህ ተግባር እየመዘገቡ ያሉ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ልነግራችሁ እችላሁ፡፡ሴቭ ዘቺልድረን በክረምት ወራት ትምህርት ቤቶችን በክረምት ትምህርት አሳቦ በመከራየት የሰዶማዊነት ትምህርት ሊሰጥ መሆኑን ስነግራችሁ ያለምንም ጥርጥር ነው፡፡አስካሁን የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ሁለተኛ ዙር ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነው ካሉ ትምር ቤቶች መካከል፡ ሚኒሊክ፤መድሀኒአለም፣ባልቻ አባነፍሶ፣ኤስኦኤስ፣ህዳሴ፣አፍሪካ ህብረት፣የካቲት 23 ፣መነን፣አየርጤና እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ይህ ነገር ሀሰትነው ብላችሁ የምትጠራጠሩ ከሆነ በተለይ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለይ ወላጆች አንደኛ በየክፍለ ከተማ የሚገኙ የስርአተ ጾታ ሀላፊዎችን ፣በአዲስ ትምህርት ቢሮ በተለይ አቶ ሀይለ ስላሴ የተባሉ የስራ ሀላፊን መጠየቅ ይቻላል፡፡በተጨማሪም በኢትዮጵያዊነት ድምጽ ላይ የተለጠፉ የመማሪያ ሰነዶችን ማየት ይቻላል፡፡ወላጆች ልጆቻችሁን አድኑ!!

የተከበራችሁ ተማሪዎች በየትኛውም አጋጣሚ በትምህርት ቤትም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጪ በስነተዋለዋልዶና ስርአተ ጾታ ስም የሚሰጠውን ፍጹም የግብረሰዶማዊነት ትምህርት አንማርም ንድትሉ ብትሉም እራስን የማዳንና የመከላከል ተግባርና እርምጃ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ መምህራንም ሆኑ በገንዘብ ተደልለው ሊያስተምሩ የተዘጋጁ ተማሪዎችን አምርራችሁ እንድታገሉ ሁላችንም በፈጠረን አምላክ ስም እለምናቿለሁ!!

ኢትዮጵያ የግብረሰዶማዊነት መቀበሪያ ትሆናለች እንጂ መቼም ከግብረሰዶማዊነት ጋር አትጋባም!!

ጭንቀት ካደረበት መምህር

The post ኢትዮጵያ ውስጥ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ ነው – አደጋ ላይ ነን! appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>