የአቋም መግለጫ
ሪሳላ ኢንተርናሽናል በሚኒሶታ የሚገኝ ማእከል ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥየሃይማኖት መብት ጥሰት በመቃወም በሚኒሶታ ዋና ከተማ ሴንትፖልህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል::
ባለፉት ሶስት ፈታኝ አመታት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እና ክልሎች ህዝባዊ ሰላማዊ ተቃውሞዋቸውን በመግለጽ መንግሥት ከውጪ ያስገባውን አህባሽ የሚባለዉን መጤ ሃይማኖት ህዝቡ በግድ እንዲቀበል ጫና ማድረጉን እንዲያቆሙ ጠይቋል::ተቃውሞውን የቀሰቀሰው መንግስት እና ሃይማኖት እንደሚለያዮ የምናደርገውን የህገ መንግስትን በመጻረር በመዲናይቱ የሚገኘውን ታዋቂየእስልምና ትምህርት ማእከል አወሊያ ኮሌጅን በቁጥጥር ስር ለማዋልየወሰደው እርምጃ ነው። ተቃዋሚዎቹ በመንግስት የተወከሉ የመንግስትአመራሮች ከሃላፊነታቸው ወርደው በምትኩ የኣማኙ ነጻ ፈቃድና ምርጫ የሚወክል አካለ እንዲመራ ቢጠይቅም መንግሥት እነኚህን ጥያቄዎች በቀና መንፈስ ተቀብሎ ማስተናገድ ሲገባው ሙስሊሙ ይህንን ጉዳይ እንዲያስፈጸሙለት የመረጣቸው ተወካዮች በማሰርና ማንኛውም አይነት ተቃውሞ በማፈን ጸረ ሽብርተኝነትን አዋጅ ተንተርሶ በሀገር መክዳት ክስ መስርቶባቸዋል::
ይህ እርምጃ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፉን እንዲቀላቀሉ አድርጓል ለዚህም የመንግስት ምላሽ በዜጎች ላይ የሽብር ማዕበል በመክፈት ከህግ ዉጪ ንጹሃን ዜጎችን ማስፈራራት፣ ማሰር፣መደብደብ እና መግደል የቀን ተቀን ስራው አደረገው፤ ይህም ህገ ወጥ እርምጃ በአለም የዜና አውታሮች ተድጋግሞ ተዘግቧል። ህዮማን ራይትዎች፣
አምኒስቲ ኢንተርናሽናል፣ በአለም አቀፍ የሀይማኖት መብት የአሜርካኮሚሽን፣ የሰብኣዊና የህዝቦች መብት እንዲሁም የአፍርካ ኮሚሽን በህገ ወጥ መንገድ የታሰሩትን አመራሮችን እና ሰላማዊ ተከተዮቻቸውን አሳዛኝ እጣ አስመልክቶ የተለየዮ መግለጫወችን አዉጥቷል።
በአሁኑ ጊዜ እነኚህ ንጹሃን የምእመናኑ የህዝብ ተወካዮች የፈጠራ ክስ ተመስርቶባቸው በህግ ሳይሆን በፖለቲካ ፍላጎት የሚመራ ፍርድ ቤት ብይን እየተጠባበቁ ናቸዉ። ሰልፉን አስመልክቶ በማንኛውም ቦታ የሚደረግ የፍትህ ጥሰት በሁላችንም ላይ የተቃጣ ነው። ስለሆነም ታሳሪዎቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን በማለት የሪሳላኢንተርናሽናል ሊቀመንበር አቶ ወዚር ጃዋር ተናገሩ ። በማስከተልም የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ጣሃ ሰመሩ ድምጻቸውን ለተነፈጉት ድምጽ ለመሆን ያለን የሞራል ግዴታ በኢትዮጵያ ድምጻቸውን ከተቀሙት የህሊና እስረኞች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር በአጋርነት እንድንቆም ያስገድደናል ። በሰብአዊ መብት ጥሰት እየታወቀች የመጣችው ኢትዮጵያ በጸረ ሽብር ዘመቻ ስም የአሜሪካ የጦር እርዳታ ከሚጎርፍላቸዉ የአፍሪካ ሃገሮች መካከል ዋነኛዋ ናት።
ይሄም እየሆነ ያለው የነጻነት ቤት freedom house ኤፕሪል 17/2015 ወይንም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዚያ 9/2007 ባወጣው የአቋም መግለጫ የብዙሃን ፖለቲካ እና ኢትዮጵያውያን የመሰብሰብ፤ የመደራጀት ብሎም ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸው ከዛሬ አስር አመት በላይ መገደቡን እና ይሄውም የሚያሳየው መንግስት ለመሰረታዊ ህዝባዊ እና የፖለቲካ መብቶች በአደገኛ ሁኔታ ማሻቀቡ ነው ሲል ገልጿል ።
በመሆኑም በሚኒሶታ ክፍለ ግዛት የመንግስት ምክር ቤት ፊት ለፊት የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካኖች የሚሰበሰበው ግብር ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የመብት ጥሰት እንዳያግዝ የሚጠይቅ ነው።
በማከልም ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደዉ የመብት ረገጣና በስራ እጦት ተገደው ለስደት ለተዳረጉ በየመን፣ በሊቢያ እና በድቡብ አፍርካ ለተገደሉት እንዲሁም ከፍተኛ አደጋ ስር ለወደቁት ወገኖቻችን ያለንን አጋርነት መግለጽ ይሆናል ።
ሪሳላ ኢንተርናሽናል ሚኒሶታ
The post በሚኒሶታ የሚገኘው ሪሳላ ኢንተርናሽናል በሊቢያ በየመን እና በደቡብ አፍሪካ ከወደቁት ኢትዮጵያውያን ጎን እንደሚቆም አስታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.