በተወለዱባትና እትብታቸውን በተቀበረባት እናት ምድር ላይ እንደ ሰብኣዊ ፍጡር – እንደ ዜጋ በነፃነታቸው፣ በማንነታቸውና በኢት}ዮያዊነታቸው ኮርቶውና አልሞቶው በሰላም የመኖር አማራጭ ያጡና ተስፋው የጨለመባቸው ወገኖቻችን ሳይወዱ በግድ ስደት በመምረጥ መድረሻ አጥተው ሲንከራተቱና የሞት ፅዋን ሲቀበሉ የሚያሳይ በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪቃ፣ በሜዲተራኒያን ባህርና በየመን አካባቢ የደረሰባቸውን ዘግናኝና ልብ ሰባሪ ዜና ስንመለከት በዘመናችን ታይቶ የማይታወቅ እጅግ አስደንጋጭ በመሆኑ በጣም አዝነናል ተቆጥተናልም::
ኢትዮ}ያ ለዘመናት የነፃነት፣ የኩሩ ህዝብና የጀግና ሀገር ተምሳሌት እየተባለች በዓለም ማሕበረሰብ ዘንድ ወርቃማ ታሪክ ይዛ ተከብራና ታፍራ እንዳልቆየች ሁሉ ዛሬ ግን ገፀ ባህሪዋንና የነፃነት ድባብዋን በሀዘን ጨለማ ተቀይሮ ረሃብ፣ ስደት፣ ሞት፣ ውርደትና እልቂት የነገሠባት፣ ባለቤት ያጣች፣ የልቅሶና የዋይታ ምድር ሆና ስናያት በጣም ያሳዝነናል:: ይቆጨናልም::
ጨዋ፣ ኩሩ፣ እንግዳ አክባሪና የዋሁ ህዝባችንም ሀገርና መንግስት እንደሌለው ተቆጥሮ የውሻን ያህል እንኳን ክብር ሳይሰጠው እንደ በግ እየታረደ፣ እንደ ቆሻሻ ባህር ውስጥ እየተወረወረ፣ ከቦታ ቦታ በመንከራተትና እስር ቤት በመታጎር በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ የሚያነሳው ያጣ፣ የተዋረደና የረከሰ ህዝብ ሆኖ ስናይ እጅግ የሚያሳዝን የትውልድ ሐፍረት ነው::
በቅርቡ ከሳውዲ ዓረቢያ ወደ ሩብ ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎቻችን ከሰብኣዊ ርህራሄ አያያዝ ውጭ በጭካኔ ተደብድበውና ተዘርፈው ባዶ እጃቸውን በተባረሩበት ወቅት የደረሰባቸው የስነ ልቦና፣ የማሕበራዊና የኢኮኖሚ ቀውስ ጠባሳው እስካሁን ድረስ አልሻረም:: ለደረሰው ጉዳትና ታሪካዊ በደልም ተመጣጣኝ መልስ የሚሰጥና ከወገኖቻችን ጎን የሚቆም የሀገርና የህዝብ ፍቅር ያለው መንግስትም አልተገኘም:: ይልቁንም ከኛ የበለጠ እውቀትና ዓቅም የሌላቸው ዓረቦች ባዶ ሀገር ስላገኟት ደማችንን ብቻ ሳይሆን አንጡራ ሀብታችንም ጭምር እየጋጡና ሕብረተሰባችንንም ከሚኖርበት መሬት እያፈናቀሉ ለስደት የሚዳርጉት መሆናቸውም ጭምር ነው:: ሰሞኑን አይሲሲ የተባለው የአውሬ መንጋ በውድ ወንድሞቻችን ላይ የፈፀመው አስደንጋጭና አስነዋሪ ድርጊት እንቅልፍ የሚነሳና ልብን የሚያደማ አረሜናዊ ተግባር ነው::
በዚሁ ፈታኝ፣ አስቸጋሪና አስደማሚ በሆነበት አጋጣሚም
- ኢ-ሰብኣዊ በሆነ ተግባር ሰለባ ለሆኑት ወገኖቻችን ሁሉ ጥልቅ ሀዘን እየተሰማን ለሁሉም ቤተሰቦቻቸውና ለመላ የኢትዮ}ያ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን:: ለሞት ፅዋ የተዳረጉት ሰማእታቱንም ታሪካቸው ህያው ሆኖ በምድር ላይ ይኖራልና ነብሳቸውን በመንገስተ ሰማይ ያኑርልን::
- በሀገር ውስጥና በስደት ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን ሁሉ በዚሁ አሳዛኝ ክስተት ምክንያት ምን ያህል ልባችሁ እንደ ተሸበረ እኛም ይሰማናል:: ይህ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስፈሪና አሰቃቂ በደል የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም:: ነገም ከዚህ በባሰ መልኩ በእያንዳንዳችን ሊደርስ የሚችል ችግር ነው:: በመሆኑም መፍትሄው አንድና አንድ ነው:: እሱም ሀዘናችንን ዋጥ አድርገን ይህ የሰማእታቱን ጥሪ ለኛ መተባበርና እብረን ስለነገ ህልውናችንን ማሰብ እንድንጀምር አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ንስሓ የምንገባበት ጊዜ ነው::
- እኛን በሀይማኖት፣ በዘር፣ በቋንቋና በቦታ ከፋፍለውና እርስ በራሳችን አናቁረው ዘላለም ለመግዛት የሚፈልጉ አምባ ገነኖችም የችግሮቻችንን መንሲኤ ናቸው እንጂ በፍፁም የመፍትሄ አካል ሊሆኑ አይችሉም:: የተፈጠረውን አሳዛኝ ሁኔታም ህዝቡን የማስፈራሪያ፣ የማናቆሪያና የማለያያ ፕሮፓጋንዳ አድርገው ለመጠቀም ወደሗላ እንደማይሉ እሙን ነው:: ስለሆነም ሳይጨልም አይነጋምና የተከሰተው መጥፎ ሁኔታ አንገታችንን የሚያስደፋንና የሚስደነግጠን ሳይሆን ቀፎው እንደተነካ ንብ ከእንቅልፋችን የሚቀሰቅሰን፣ የሚለያየን ሳይሆን የበለጠ የሚያስተሳስረን፣ የሚያናቁረን ሳይሆን የበለጠ የሚያስተቃቅፈንና የሚያፋቅረን መሆኑና በተለይም ከነሱ በፊት ቀድመንና በልጠን በመገኘት የቀውጥ ቀን ለጆች መሆናችንን በተግባር ማሳየት ይኖርብናል:: ኢትዮ}ያዊ ነኝ ማለቱ መገለጫው ይኸው ነውና::
- ሰሞኑን የተከሰተው አስደንጋጭ ሁኔታ አላማው ኢትዮያውያንን ለማዋረድ፣ ለማሳፈርና ማንነታችንን ለማንቋሸሽ ሲባል በህዝባችንና በሀገራችን ላይ የተቃጣ የስነ ልቦና ጦርነት መሆኑን እሙን ነው:: ይህም በሕብረተሰባችን ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም:: ሰለሆነም በሀገር ውስጥም ሆነ በዲያስፓራ በመንቀሳቀስ ላይ የምትገኙ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የሀይማኖት ተቋማትና አባቶች፣ የሲቢክ ማሕበራትና ሰብኣዊ መብት ተሟጓቾች ድርጅቶች፣ ምሁራኖች፣ አርቲስቶች፣ ወጣቶች፣ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ የሚዲያ አውታሮችና ሌሎች ዜጎች በሙሉ ጨዋነት፣ ሃላፊነትና ጥበብ በተሞላበት አኳሃን ህዝቡን ለጋራ ችግሩ በጋራ ለመቆም ይችል ዘንድ ለማስተባበር የምትፈተኑበት ጊዜው አሁን ነው::
የጋራ ችግራችንን በጋራ ለመፍታት ተባብረን እንቁም
ኢትዮ}ያ ሀገራችን በልጆችዋ ተከብራ ለዘላለም ትኑር
Bega2260@comcast.net
The post ባለቤት ያጣ ትውልድ እንደ በግ ሲታረድ – በዲያስፓራ የዓረና ትግራይ ድጋፍ ከሚቴ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.