ፖሊስ የሆናችሁት ሕዝቡን እንድትጠበቁና ሕዝቡን እንድታገለግሉ ነው። የሕወሃት ባለስልጣናት ሕዝቡን እንድትደበድቡ፣ እንድታሸበሩ፣ እንድታወኩ መመሪያ ሲሰጧችሁ፣ መመሪያዉን ተቀብላችሁ ተግባራዊ ለማድረግ መሯሯጣችሁ አሳዛኝ እና ትልቅ ወንጀል ነው።
በአሁኑ ዘመን የምታደርጉት ሁሉ በፎቶና በቪዲዮ እየተቀረጸ ነው። አለም ሁሉ እያየው ነው። ማንነታችሁ እየተመዘገበ ነው። ከእኩይ ተግባራችሁ እንድትቆጠቡ፣ የአለቆቻችሁን ኢሰብዓዊ መመሪያ አንቀበልም እንድትሉ እናሳስባለን።
ሕዝቡ ድምጹን ማሰማቱን ይቀጥላል። ተቃዉሞው ይቀጥላል። ለውጥ መምጣቱ የግድ ነው። ሕወሃት ለ24 አመታት ገዝቶ፣ በስብሶ ሊወድቅ ትንሽ ነው የቀረው። ሕወሃት አገር የማስተዳደር አቅምና ብቃት የለዉም። በሕዝቡ ከዳር እስከ ዳር የተጠላ ነው። የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ በማያሻማ መልኩ አረጋግጧል። ከሕዝባችሁ ጎን ብትቆሙ ይሻላቹሃል !!!!!
ነገ ሚያዚያ 15 ቀን “ስራ የለም” ተብሏል። ነገ ቤታችሁ ተቀመጡ !!!!
የሕውሃት ባለስልጣናት አንድ ነገር ቢፈጠር እናንተን አጋልጠው ነው አገር ለቀው የሚሄዱት። ከሕዝቡ ገንዘብ ዘርፈው ወደ ዉጭ አውጥተዋል። ልጆቻቸዉን ወደ ዉጭ ልከዋል። እናንተ ናችሁ ሜዳ ላይ የምትቀሩት !!!!! ስለዚህ ለራሳችሁና ለቤተሰባችሁ ስትሉ መልካሙን መንገድ ምረጡ። ከሕዝብ ጎን ቁሙ!!!!!!!
The post ለፌዴራል ፖሊሲ አባላት appeared first on Zehabesha Amharic.