================
ማጣቱ ዘልቆ ሳይጎዳኝ ፣
ድህነቱን ችየ በኖርኩኝ ፣
እህ ብየ ተመስገን ብየ ኑሮ በገፋሁኝ ፣
የመኖሬን ተስፋ ቀማችሁኝ ፣
ልጀን ወዳጀን ነጠቃችሁኝ ፣
ደጋፊየ ጠዋሪየን በግፍ ቀማችሁኝ !
እኔማ …. ደካማ እናት ነኝ ፣
ልጀን በጨካኞች በግፍ ያጣሁኝ ፣
አሳቢ ልጀን የተቀማሁ ፣ የጎደለብኝ ፣
እኔማ አድሜ ጠገብ ፣ ደከማ ነኝ ፣
ለበቀል የሚሆን ጉልበት የከዳኝ ፣
የተገፊ እናት ነኝ ፣ ሀዘን ጠልቆ የተሰማኝ ፣
አዎ! አቅም ያጣሁ ምንዱብ እናት ነኝ !
ብቻ ተስፋየ በሱ ነው ፣ በማይተወኝ ፣
የፈጠረኝ መድሐኒአለም ይፋረደኝ ፣
በቀል አይቀርም ተስፋ አለኝ !
እሱ አንድየ ይድረስልኝ !
መድሐኒአለም ይፋረደኝ ! ”
አዎ እናታለም ፣ መድሐኒአለም ይፋረደን !!!
አዎ እናት አለም …
የበቀል አምላክ ዝም አይልም ፣
መድሐኒአለም ይፈርዳልም !ነቢዩ ሲራክ
በጨለመው ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓም
The post መድሐኒአለም ይፋረደኝ ! – ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.