Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በደቡብ አፍሪካም እንዲህ ሆነ – (ሄኖክ የሺጥላ)

$
0
0

ethiopia south africa
ከ 17ኛው ክፍለ ዘመን እስከ በቀደም በነጮች ( በመጀመሪያ በ-ቡሮች ወይም ደቾች ቀጥሎም በ 19ኛው ክፍለ ዘመን የአልማዝ መገኘትን ተከትሎ በእንግሊዞች ) የባርነት ቀንበር ስር ስትማቅቅ የኖረችው ደቡብ አፍሪካ ፣ በብረት እሾህ ታጥራ ልጆቿን በስልጡን የጀርመን ውሻዎች (Geremen Shippered) ስታዘነጥል የኖረችው ደቡብ አፍሪካ ፣ ነጭ ባለፈበት እንዳታልፍ ፣ እንዳትማር ፣ እርስ በእርስ እንዳትነጋገር ፣ ህዝቦቿ በገዛ ሀገራቸው አራተኛ ወይም የመጨረሻ ዜጋ ተደረገው ( ከ እንግሊዝ ፣ ከደች ፣ ከ ሕንድና ኤስያ ቀጥሎ ) ለመቶ አመታቶች ነጻነት ምን እንደሆነ ሳታውቅ የኖረችው ደቡብ አፍሪካ ፣ ነጻነትን ከትናንት ወዲያ ያገኘች ው ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦጠሊቃዊ ፣ ሰላማዊ ፣ ሰዋዊ ስብሰባዎችም ሆነ ማንኛውም የሰለጠነ እና እንደሰው የሚኖር ሰው የሚያደርጋቸው ተፈጥሯውዊ ክንውኖች ተነፍጏት የኖረችው ደቡብ አፍሪካ ( ለምሳሌ እኔ ደቡብ አፍሪካ በነበርኩበት ግዜ ሴቶቹ ደቡብ አፍሪካውያን ሲሰክሩ በአብዛኛው በቁማቸው እንደሚሸኑ አይቻለሁ )፣ አዎ ያቺ የባርነት ተምሳሌት ፣ የመረገጥ እና የውርደት ቤት የነበረችው ደቡብ አፍሪካ ፣ ከመሬቷ ሲሶ ያህሉ እንኩዋ የሷ ያልሆነው (ያልነበረው ) ፣ የምድሯን በረከት ፣ የልጆቿን ደም ፣ አንጡራ ሀብት በሉት ፣ እምቅ ሀብት ፣ ወርቁን እና ፣ አልማዙን ቆፍረው እና አጥለው ፣ ኖራውን እና የድንጋይ ከሰሉን በድማሚት አፍርሰው ፣ ረስተንበርግን እንደ ኩይሳ ከላይ ያፈር ክምር ፣ ከስር የምስጥ ቤት አስመስለው ፣ ጆሃንስበርግን ( ወይም ኢጎሊን ) የወርቅ ምድር እያሉ እያሞካሹ ህዝቦቿን እያሹ ኑረው ፣ ኑረው የተትረፈረፉባትን ጌታዎቿን ፣ ደምና ውስኪ እኩል ያፈሰሱባትን ገዳዮቿን ይቅርታ ያለችው ያቺ ሳውዝ አፍሪካ ፣ የዘመን በደሏን ረስታ ፣ የባርነት ቀንበር ህሊናዋ ላይ ክርክር ቢሰራም ፣ በፍቅር ተረታሁ ፣ ሰውነት ከበደል እና ከክፉ ታሪክ በለጠብኝ ብላ ፣ በ ጁሃን ስበርግ ( በሱዌቶግዛት ወይም ከተማ )፣ በ-ደርባን ፣ በ ፖርት ዔልዛቤት ፣ በ ኬፕታወን ፣ በዋና ከተማው በፕሪቶሪያ ፣ በራንጉሌ ፣ በጃካራንዳ፣ በሮቢን ደሴት ፣ እና በወዘተ፣ እነ ሜምቄጺ፣ እኔ ሲቦንጊሌ ፣ እነ ታቱ ፣ እነ ዙማ ፣ እነ ማዲባ ፣ እነ ወዘተ በባቡር መሳፈርያው ሆነ ፣ በአሳንሱር ላይ ፣ በመንገድ ላይ ሲጏዙም ሆነ አምጠው ሲወልዱ ፣ በዚህ በኩል እንዳትሄዱ ፣ በዚህ በኩል ሂዱ ( NET NIE BLANKES ( None white person only blacks ) ) እየተባሉ የኖሩት ደቡብ አፍሪካውያን ፣ በአንድ ምህረት ፣ ሁለት ገጽ የይቅርታ ደብዳቤ ተቻችለው መኖር የለመዱት ደቡብ አፍሪካውያን ፣ ሲቸገሩ ድንበር አቋርጠው ያስጠጏቸውን ሞዛምቢኮች ፣ መሳሪያ ደብቀው ያሸገሩላቸውን ዚምቡዋቤዎች ፣ መሪዎቻቸውን ወስደው ያሰለጠኑላቸውን ኢትዮጵያውያኖች ዛሬ በእሳት አቃጠሉ ፣ በድንጋይ እንደ ዘማይ በአደባባይ ወገሩ ፣ እንደ ጌቶቻቸው እነሱም የባርነት ግፋቸውን ፣ ያደፈ ልባቸውን ፣ ያቄመ ልቦናቸውን በወንድሞቻቸው ላይ አነሱ ።

እንደ እንሰሳ ለዘመናት የገዟቸውን ፣ እንደ ትል የረገጧቸውን ፣ እንደ ትቢያ ያረከሷቸውን ፣ አጥንታቸውን የከሰከሱትን ፣ ደማቸውን የመጠጡትን ፣ እምቅ ሀብታቸውን የዘረፉትን ይቅርታ ማድረግ ያልከበዳቸው ደቡብ አፍሪቃውያን ፣ ዛሬ ግን በደም እና በቀለም የሚመስሏቸውን ፣ በችግር የደረሱላቸውን ፣ በ ጨለማ መብራት የሆኑላቸውን ፣ አብረዋቸው የመከራ ጽዋ ( ገፈት ) የቀመሱ አፍሪካዊ ወንድሞቻቸውን አይን ማየት አስጠላቸው ፣ ህጻናትን የፈጁትን የአፓርታይድ መሪዎች ፣ ወታደሮች ፣ እና ወዘተ ይቅርታ ማድረግ ያልከበዳቸው ደቡብ አፍሪቃውያን ፣ በቢሊዮን ምናልባትም በትርሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ለመቶ አመታት የዘረፏቸውን ፣ የወረፏቸውን እንደ እንስሳ ያዩዋቸውን ቀኝ ገዢዎች ይቅርታ ማለት ግድ ያላላቸው ደቡብ አፍሪቃውያን ፣ ዛሬ ጨርቅ ነግዶ ፣ በየ ቅያሱ ( ሎኬሽን ) ብርድ-ልብስ አዙሮ ፣ ነጠላ ጫማ በየ መንገዱ አንጥፎ ፣ ቻፓቲ ሸጦ ህይወቱን ለማሸነፍ የሚውተረተረው ጥቁር ንብረት አስቆጣቸው ፣ በሱዌቶ የህጻን ልጅ ደም በ መትረየስ ( አውቶማቲክ ጠብ መንጃ ) የቀጠፈውን አፓርታይድ ይቅርታ ማድረግ ያልከበዳቸው ደቡብ አፍሪካውያን ፣ we are passionate about South Africa የሚል ጽሑፍ ሽንጡ ላይ ለጥፎ በጎዳናዋ ላይ የሚሽከረከረው የመአድን መጫና ባቡር ሳይሆን በብሪ ፣ ዴሊቨር እና ጂፒ ጎዳናዎች ላይ የተከፈቱት ጥቃቅን ሱቆች ደማቸውን አፈላው።

የሚከተሉትን ሕጎች የተቀበሉት (Population Registration Act, 1950 – This Act demanded that people be registered according to their racial group. This meant that the Department of Home Affairs would have a record of people according to whether they were White, Coloured, Black, Indian or Asian. People would then be treated differently according to their population group, and so this law formed the basis of apartheid. It was however not always that easy to decide what racial group a person was part of, and this caused some problems.

Group Areas Act, 1950 – This was the Act that started physical separation between races, especially in urban areas. The Act also called for the removal of some groups of people into areas set aside for their racial group. Well known removals were those in District Six, Sophiatown and Lady Selborne (also see Cato Manor, Fietas and Curries Fountain (Grey Street area)). People from these areas were then placed in townships outside of the town. They could not own property here, only rent it, as land could only be white owned.

Promotion of Bantu Self-Government Act, 1959 – This Act forced different racial groups to live in different areas. Only a small percentage of South Africa was left for black people (who comprised the vast majority) to form their ‘homelands’. Like the Group Areas Act, this act also got rid of ‘black spots’ inside white areas, by moving all black people out of the city. This Act caused much hardship and resentment. People lost their homes, were moved off land they had owned for many years and were moved to undeveloped areas far away from their place of work.

Bantu Education Act, 1953 – established an inferior education system for Africans based upon a curriculum intended to produce manual laborers and obedient subjects. Similar discriminatory education laws were also imposed on Coloureds, who had lost the right to vote in 1956, and Indians. The government denied funding to mission schools that rejected Bantu Education, leading to the closure of many of the best schools for Africans. In the higher education sector, the Extension of University Education Act of 1959 prevented black students from attending “white” universities (except with government permission) and created separate and unequal institutions for Africans, Coloureds, and Indians respectively. The apartheid government also undermined intellectual and cultural life through intense censorship of books, movies, and radio and television programs.

The Suppression of Communism Act, 1950 (originally introduced as the Unlawful Organisations Bill) – The Act was introduced in an attempt to curb the influence of the CPSA and other formations that opposed the government’s apartheid policy. It sanctioned the banning/punishment of the CPSA or any group or individual intending to bring about political, economic, industrial and social change through the promotion of disorder or disturbance, using unlawful acts or encouraging feelings of hostility between the European and non-European races of the Union of South Africa. The Act was progressively tightened up in 1951, 1954, and yearly from 1962-1968.
) እና ለነዚህም ይቅርታ ያደረጉት ደቡብ አፍሪቃውያን ፣ የጥቁር ወንድሞቻቸው ገላ ላይ እሳት ጫሩ ።

መደምደሚያ

ጥንትስ ቢሆን ሰው ወገኑን ካዋረደ ለግፍ ጥሎ
ባለቤት ያቀለለውን ባለ ዕዳ መች ተቀብሎ ! ይላል አባት ዓለም ጸጋዬ ገ/መድህን ። እኛም

ባገራችን በአድ ሆነን በመአዳችን ቀላዋጭ
በሰው ሀገር የሰው ዝቃጭ !

ሀገር የሌለው ክብር ፣ ዘር ፣ ሕይወት እና ተስፋ የለውም ! የትም የኛ አይደለም ! የኛ ኢትዮጵያ ብቻ ነች !
ለነጻነታችን ካልተጋን ፣ ካልተዋጋን ፣ በየመን የሰማይ እሳት ፣ በቀይባይ ባህር የመአበል እሳት ፣ በሳውዲ አረቢያ የሹርጣ እሳት ፣ በ ሳውዝ አፍሪካ የቆራጣ ባርያ እሳት ይበላናል ። ሀገር ይኑረን ! ነጻነታችንን እናስመልስ !

ሄኖክ የሺጥላ

The post በደቡብ አፍሪካም እንዲህ ሆነ – (ሄኖክ የሺጥላ) appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>