Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ከአረብ ሀገር እስከ ደቡብ አፍሪካ * የስደተኛው ሮሮና የመንግስት ቸልተኝነት ! (ይድረስ ለክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም …)

$
0
0

ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

የማለዳ ወግ …ከአረብ ሀገር እስከ ደቡብ አፍሪካ
የስደተኛው ሮሮና የመንግስት ቸልተኝነት !

* ይድረስ ለክቡር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም …
* ኢህአዴግን እንዴት እንምረጥ ?

ትናንት በሁከት ፣ ዛሬ በመፈራረስ በሚመስል አደገኛ የለውጥ ሂደት ውስጥ ባለችው የመን የኢትዮጵያውያን የድረሱልኝ ድምጽ ከነኡኡታው ሰላም ይነሳል ። በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ ከኢራቅና ሶርያ አይ ኤስ አይ ኤስ ISIS ጽንፈኞች ባላነሰ ከፍ ሲል በሰብአዊው ዜጋ ፣ ዝቅ ሲል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በተለያዩ የውጭ ዜጎች ላይ የተጀመረው ጥቃት ሊያዩት ሊሰሙት ይከብዳል ። በሰላ ገጀራ ፣ ሰንጢ የሰው ፍጡር የመቆራረጥና ፣ በእሳት የማቃጠልን የአውሬ ተግባርን መመልከት ዘልቆ ልብን ይሰብራል ። ይህ ሁሉ ሲሆን ” መንግስ አለን !” ባዮች ኢትዮጵያውያን ፈጥኖ ደራሽ ቀርቶ ጉዳቱን አጥብቆ የተቃወመ መንግስት ባለማየታችን አዝነናል !
Saudicry
በአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ” ኢህአዴግን ምረጡ !” በሚል በማህበራዊ መገናኛ የፊስ ቡክ ቅስቀሳ ዘመቻዎ ባስተላለፉት መልዕክት የፈረደበት መንገድ ፣ ህንጻውንና ግድቡን በፎቶ አሸብርቀው ” እነሆ ሰርተን አሳይተናል ፣ ስራ ላይ ነን !” በማለት “የወሬ የለው ፍሬ ” በሚልና “ስራ እንጅ ወሬ አናውቅም ” የሚል አንድምታ ያለው መልዕክት አስተላልፈው ተመልክቻለሁ ። ለድርጅትዎ ቀናኤ መሆንዎን አልቃወምም ። ዳሩ ግን በስደት ህይዎቴ በድርጅትዎ የሚወከሉ ባለስልጣኖችም ሆኑ ተራ የድርጅትዎ ካድሬዎች የመንገድ ህንጻውንና ግድቡ ከእነ ተሳላጠው የሃገር እድገት እያነሱ በመጣል ከመደስኮር ፣ ለድጋፍ ገንዘብ ለመሰብሰብ ከሚደረገው ድግስና የስብሰባ ጥሪ ባሻገር ለዜጋው መብት ማስከበር ቆመው አይቸ ፣ ሰምቸ አላውቅም ። እናም ሀገር የማለት ትርጉሙ ቅጥ አንባሩ ይጠፋብኛል !

በማዲባ ምድር በደቡብ አፍሪካ በዜጎች ላይ እየተፈመ ያለውን አሰቃቂ ግፍ እንደ ዜጋ አሞኛል ። ድርጊቱን በአደባባይ የሚያወግዝልን መንግስት ማጣታችን አውጥቸ አውርጀ ለዜጎች መብት ማስጠበቅ ተግቶ የማላውቀው ኢህአዴግን ብመርጥ ሀገሬ ህዝቤ ምን እንደሚሆኑ ማሰቡ አልተሳነኝም ። …አናም መንግስትዎ እንደ ዜጋ የስደተኛ መብታችን ካስጠበቀልን እንጅ ግዑዙን መንገድ ስለሰራ ፣ ህንጻውን ስላቆመና ግድቡ ስለገደበልኝ ፣ በአንጻሩ መሆን አለበትን ? ስል ከራሴ የወጣ ፈታኝ ጥያቄ አንገላታኝ… እናም ትናንትም ሆነ ዛሬ ኢህአዴግ ለዜጎች መብት እስካልተጋ ድረስ እንዴት ኢህአዴግን እንምረጠው ? አልኩ ቢቸግረኝ …

የሆነው እና እየሆነ ያለው ቢያከፋኝና ፣ ቢያስጨንቅ ፣ ቢያስጠብበኝ ወቀሳ ቢጢ ልልክልዎ ነሸጠኝ … ! ብዕሩን በቀለም ነከሬና ወረቀቱን አቅርቤ የታወከው ውስጤ እርሙን ያወጣ ዘንድ እንደለመድኩት በማለዳ ወጌ ብሶቴን መተንፈሱን መረጥኩ … ንዴት ብስጭቴ አይሏልና ክብርዎን እንዳልነካ በመጠንቀቅ እራሴን አረጋግቸ ስሞታ ፣ ቅያሞቴን አሳምሬ በማውቀው የአረብ ሀገሩ ስደት በጨረፍታ ልጀምረው ፈቀድኩ … !

ከሁሉ በማስቀደም ከ20 ዓመታት ወዲህ ዘንድሮ ወግ ደርሶን ባለሙያ ወደ አካባቢው መላኩን ባልክድም ፣ ከዚህ ቀደም በአረብ ሃገራት በዜጎች መብት ጥበቃ የገጠመን የባለሙያ ተወካይና የመንግስት ትኩረት እጦት ፈተና ግን እንዲህ በአጭሩ የሚገለጽ አለመሆኑን ከጅመሩ አስረግጨ ልነግርዎ ደስ ይለኛል ! …ግን በአጭሩ ልሞክረው …

እርስዎ የጤና ጥበቃ ሃላፊ ከመሆንዎ በፊት ጀምሮ እስከዚህች ሰዓት ላለፉት 20 አመታት በአረብ ሀገር የመ ብት አስጠባቂ ተቆርቋሪ አጥተን ስለመናቅ መዋረዳችን ፣ ስለመገፋት መገደላችን ፣ ስለ ስደቱ አስከፊነት የሚደ ርሰውን በደል በከፊልም ቢሆን በማቀርባቸው መጣጥፎች ባለፈ በአንጋፋው የጀርመን ራዲዮ የዜጎችን ይዞታ ላልሰሜ ለማሰማት ሞክሬያለሁና ” ሁሉን ቢባገሩት ሆድ ባዶ ይቀራ ል ” የምል ዜጋ አይደለሁም ! እኔን ሆንኩ መሰሎቸ የዜጎች መብት ይከበር ፣ የመብት ጥበቃ ይደረግልን እያልን ድምጻ ችን ያሰማን ቢሆንም ሰሚ በማጣታችን ግፉ ከጠበቅነው በላይ ሆኖ አሁን ድረስ ቀጥሏል …

የእኛ እውነት የእናንተ ስህተት …
====================

ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …
እርስዎ የተኳቸው የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአሁኑ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለጉብኝት መጥተው የኮንትራት ስራ ኢትዮጵያውያንን ለመቀበል ሳውዲዎች ፍላጎት ማሳየታቸ ውን ለሳውዲ ታዋቂ ጋዜጦች መግለጫ ሰጥተው እንደ ሄዱ ያለምንም ቅድመ ዝግጅትና ጥናት የኮንትራት ስራውን ሲጀመር ከቀሩት ወገኖቸ ጋር በመሆን ህጋዊ የኮንትራት የሁለትዮሽ ውል ሳይደረግ ዜጎችን መላኩ አደጋ አለው በሚል የተቃውሞ ድምጻችን ስናሰማ የስምምነት ህጋዊ ውሉን መፈራረምና አማራጩ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ነው ብንልም ሰሚ አላገኘንም ። በአጭር ጊዜ ህጋዊ ውል በሌለው ስምምነት በኮንትራት ስራ ስም ዜጎች ይላኩ ጀመር ። ከጅምሩ እስከ አሁን ያለውን አሰቃቂ የእህቶቻችን የመከራ ዋይታ መስማት ጀመርን ። እርስዎ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ያለምንም ጥናትና ቅድመ ዝግጅት የተጀመረውን በድርጊቱ ሁሉ ከታመሙት መካከል የምወዳት ሃገሬ እጓለማውታ ስደተኛ አንዱ እኔ ነኝ !
Tedros-Adhanom-
ምንም እንኳን ዛሬ መንግስትዎ ዜጎችን ያለ ሁለትዮሽ ውል ወደ አረብ ሀገራት ለስራ መላኩ ስህተት እንደነበር ማመኑን ሳስበው እታመማለሁ። ዛሬ እውነቱ በሂደት ፍን ትው ብሎ ወጥቶ እኛ የሰጠነው መረጃ ትክክል እናንተ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በኮንትራት ስራ ስም ያለ ውል መላካ ችሁ ስህተት መሆኑን ብታምኑም የዜጎች ህይዎት የተገበረበት የአካሄድ ስህተት አንኳ ይቅርታ አልጠየቃችሁም። ይባስ ብላችሁ አሁንም ባለ ድርሻ አካላት በግልጽ ያልመከሩበት አዲስ ህግ ተረቆ ለትግበራ ጥድፊያ ላይ መሆናችሁ ለዜጎች ታስቦ ነው አልልም ። ያኔ እንደ ዜጋ አግብቶን ስንናገር ባለመሰማታችን እናንተ ተሳሳታችሁ እነደነበር ዛሬ በአደባባይ አመናችሁ ፣ ዛሬም እንደ ዜጋ አግብቶን ረቂቅ ህጉን ባለድርሻ ዜጎች ይወያ ዩበት ስንል ሰሚ አጥተን ” ግመሏ ትሄዳለች ውሻዎች ይጮሃሉ! ” አይነት የተለመዴ አካሄድ የተያዘ ለመሆኑ የሚያሳብቁ ኩነቶች ታጅበን እየተጓዝን እንገኛለን ! ከአንድ አመት በፊት ” ስደት ይብቃ !” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየ ም አዳራሽ ከአፍ እስከ ደገፉ የሞሉ ታዋቂ ሰዎችና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ልብ አሸብሮ ያስለቀሰው ግፍ እንዲፈጸም ምክንያቱ ስህተታችሁ አልነበረምን? ዛሬስ እንዴት ያ ሁኔታ ባለበት እንዲቀጥል ትፈቅዳላችሁ ? ለምንስ አትሰሙም ?

በደቡብ አፍሪካስ ለኢትዮጵያውያን የት አላችሁ?
==============================
ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ…

ወገን በደቡብ አፍሪካ ለሳምንት በአጣብቂኝ ውስጥ ወድቆ ከአይሲኤስ በማይተናነሱ የደቡብ አፍሪካ አውሬዎ ች በኢትዮጵያውያን ላይ ግፍ ሲፈጽሙ የት አላችሁ ? ኢት ዮጵያውያን ስደተኞች ሃብት ንብረታቸውን እየተቀሙ ፣ እየተ ዘረፉ ሲሳደዱ ፣ ሲወገሩ ፣ በእሳት ሲነዱንና ጨፈጨፉ ሲፈጸምባቸው ማትረፍ ባትችሉም እንዴት ድርጊቱን ማውገ ዝ ተሳናችሁ ? ዜጎች መደፈር የአገር ህመም አልሆን ብሎ ፣ የሀገራቱ ሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊው ግንኙነት እንዳይ ናጋ ይሆን ? እውነት እልዎታለሁ … እርስዎ በከፍተኛ ኃላ ፊነት ያስቀመጠዎ መንግስት ፣ እርስዎም እንደ ውጭ ጉዳይ ኃላፊነትዎና እንደ ዜጋ የዜጎችን መብት ለማስከበር ተቃውሞ ድመወጻችሁን ለአለም አላሰማችሁም ። ይህም ስታደርጉ ትልቁን ሃላፊነት አልተወጣችሁምና አዝኛለሁ !
south africa
ከአፖርታይድ የነጻነት እለህ አስጨራሽ ትግል በደ ገፍናት ፣ ለመሪዋ ለማንዴካ መሸሸጊያ ፣ ለታጋይ ፋኖዎቿ መጠጊያና ስንቅ ትጥቅ ያቀበለችው ሃገር ዜጎች በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ ወሮበሎች ተደፍረናል ። በህግና በስርአት በምትመራ በምትባለው ስልጡን አፍሪካዊት ሀገር በደቡብ አፍሪካ ፣ በአለማችን የነጻነት ታጋይ በክቡር ኔልሰን ማን ዴላ ምድር ፣ ነጻነቷን ከወራሪ አስከብራ የኖረችው ሀገር የኢትዮጵያ ልጆች ግፍ ተፈጽሞብናል ። በዘር ጥላቻ የወገን ደም ረክሶ በሰላ ገጀራ አካላቸው ሲጎመድ ፣ ሲቃጠሉን ሲገደሉ እያያችሁ ዝምታን መምረጣችሁ እኔ በግል በመን ግስት ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎኛል ። አፋጣኝ የወ ገን አለኝታነትን አለማሳየታችሁ እኔን ብቻ ሳይሆን ሀገር ወዳዱን ደጋፊዎችዎን ሁሉ ማስቆጣቱን ማምሻውን በለቀ ቁት ብጣሽ መረጃ ስር የተጻፈውን የሰላ ሂስ ማንበቡ ብቻ በቂ ይመስለኛል ።

ክቡር ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ በደቡብ አፍሪካ ዜጎ ቻችን ላይ አፋጣኝ እርምጃ አለመውሰዳችሁ በመስሪያ ቤትዎም ሆነ በመንግስት ተስፋ ያልቆራጥን የነበርንን ጥቂት ገለልተኛ ነን የምንል ወገኖችን ሞራል አልጠበቀል ንም ። ከእኛ አልፎ ሲደግፉ ያው ግዑዙን መንገድ ህን ጻውን ፣ ግድቡን ፣ “ተንፈላሰሳችሁበት ” የሚሉንን ሞክ ራሲና እድገቱን ከመጥቀስ ፈቀቅ የማይሉ ፣ የሚሰደደውን ህልቀ መሳፍርት ዜጋ ድህነት ፣ የኑሮ ውድነትና የአውራ ፖርቲ ፖለቲካ ትንኮሳ ምክንያት አስረግጠው ለማስረዳት በቂ ምክንያት የሚያጥራቸውን ከነፍሳቸው ጋር የታረቁ ደጋፊዎቻችሁን ተቀይመዋችኋል። እነሱን ለማጽናናት ሲባል ቢያንስ
” … የኢህድሬ መንግስት ና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዜጎቹ የሚፈጸመውን አሰቃ ቂ በደል በመቃዎም የደቡብ አፍሪካን አንባሳደር በአስቸኳ ይ ጠርቶ አፋጣኝ እርምጃ እንዲዎስድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ ! ይህ ካልሆነ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እስከመቋረጥ የሚያደርስ እርም እንደሚወስድ መንግስት ያወጣው መግለጫ አስታወቅ !”
ተብሎ በቴሌቪዥንና በራሳችሁ ራዲዮ መስማቱን ናፍ ቀነው የውሃ ሽታ ሆኖ ሳንሰማው ቀረን … እርስዎም ቢሆን መረጃው እንደ ደረሰዎ በትኩሱ በለመድነው ዘመነኛ መረ ጃ ቅበላዎ የረባ መረጃ ስላልሰጡን የለውጥ ተስፋ ያለን ሁሉ ምኞት ከንቱ መሆኑን አሳይቶ የማይጨበጠውን ተስፋ አጨናግፎታል !

እንደ ከሸፍን እንዳንቀር ፣ ከኢትዮጵያ መንግስት የምንጠብቀው …በጥሞና ይስሙኝ !
==========================

ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …
ክቡርነትዎም ሆኑ የሚመለከታችሁ እንዲህ እንደ ተዋረድን ፣ እንደ ከሸፍን እንዳንቀር ፣ በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመብንን ግፍ የሚመለከት ከእርስዎና ከኢትዮጵያ መንግስት የምንጠብቀው ከብዙ በጥቂቱ ሃሳቤ የሚከተለው ነውና በጥሞና ስሙኝ !

1ኛ / የኢትዮጵያ መንግስት በደቡብ አፍሪካ እየተፈጸመባቸው ላለው ግፍና በደል ለድርድር እንደማይቀርብ በማስገንዘብ ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በአደባባይ ከዚያም አልፎ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጠንከር ያለ መግለጫ መስጠት አለበት ።

2ኛ / ለነጻነት ትግሉ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረገችው ሃገር የኢትዮጵያ ዜጎች በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመባ ቸውን ግፍ ህዝብን ያስከፋ ያስቆጣ ድርጊት መሆኑን በሀገር ቤት መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር በግልጽ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ መፍቀድ ።

3ኛ / ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ያደረጉትን የደቡብ አፍሪካ ፣ የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታትን ከፍተኛ ኃላፊዎች በመጥራት በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው በደል የሁለቱን ሃገር ግንኙነት እስከ ማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ እንደሚያስከትል ከበድ ማስጠንቀቂያ መስጠት ።

4ኛ / በህግና ስርአት የፕሬ ጃኮብ ዙማ ትተዳደራለች በምትባለው የደቡብ አፍሪካ መንግስት ግፍ በዜጎቻችን መፈጸሙን በአጽንኦት ለማስረዳት በጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ በእርስዎ የሚመራ ቡድን በአስቸኳይ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊሄድ ይገባል ።

5ኛ / ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ የሚፈልጉ ዜጎች ለጉዳታቸወና ለተዘረፉት ንብረት ካሳ መጠየቅ ።

6ኛ / ወደ ሀገር መመለስ ለሚፈልጉ ተመላሽ ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ፣ ወደ ሶስተኛ ሀገር መሔድ ለሚፈልጉ መብታቸውን ማክበር ይገባል ።

በደቡብ አፍሪካ ያላችሁ ዜጎች ብርታቱነን ይሰጣችሁ !
የሞቱትን ነፍስ ይማር ከማለት ባለፈ መሄድም ሆነ ክብራች ን መመለስ ባይቻልም ፣ ሀገርና መንግስት አለን ለማለት አፋጣኝ እርምጃ ከመንግስትዎና ከመስሪያ ቤትዎ እንጠብቃለን !

ሀገር ማለት ህዝቡ ነው !

ከሰላምታ ጋር !

አክባሪዎ

ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 9 ቀን 2007 ዓም

The post ከአረብ ሀገር እስከ ደቡብ አፍሪካ * የስደተኛው ሮሮና የመንግስት ቸልተኝነት ! (ይድረስ ለክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም …) appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>