ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ቀናት በደቡብ አፍሪካዋ የቱሪስት ከተማ የደርባን ተወላጆች_የውጭ አገር ዜጎች ከአገራቸው እንዲወጡ ለማስገደድ በወሰዱት ጥቃት 3 ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን አጇንስፍራንስፕሬስዘግቧል።
ኢትዮጵያዊያኑ ሱቆቻቸው ውስጥ እንዳለ በጋስ በተሞላ ቦንብ መቃጠላቸውን አንዳንዶች ተደብድበው መሞታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። በደርባንና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጭንቅ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ቢቢሲ ባቀረበው ዘገባ ደግሞ አንድ ኢትዮጵያዊ አገራችን ችግር ላይ ነች፣ አገር የለንም የት እንደምሄድም አላውቅም ብሎአል።
የአሁኑ ተቃውሞ የዙሉ ባህላዊ ንጉስ ጎድ ዊል ዝዌልቲኒ የውጭ አገር ዜጎች ሻንጣዎቻቸውን ሸከፍው እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ የተፈጠረ ነው። የፕሬዚዳንት ዙማ ልጅ በበኩሉ ” የውጭ አገር ዜጎች አገሪቱን በረጅም ጊዜ ሊቆጣጠሩዋት ይችላሉ” በሚል የሰጠው መግለጫ ለግጭቱ መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገልጿል። ማላዊ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ በማውጣት የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች።
Source:: Ethsat
The post በደቡብ አፍሪካ በውጭ አገር ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንደቀጠለ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.