Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በስለላ ከሆላንድ የተባረረው የጋዜጠኛውን አንገት እቆርጣለሁ አለ (ድምጹን ይዘናል)

$
0
0


ክንፉ አሰፋ

እለተ እሁድ ከቀትር በሁዋላ አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ቁጥሩ +251 945226530 ነበር። ስልኩን አነሳሁት።
“ሃሎ”
“አቤት”
“አለማየሁ ነኝ። መን አባክ ነው የምትጽፈው። እኔ አላማዬ ነው። አንተን ግን አንገትህን ቆርጬ ነው የማሳይህ። ለማየት ያብቃህ። ያን የምትጽፈውን ጽሁፍ… እኔ ምንም ልሁን ምን እንደዚህ አይደለሁም። እሺ። እናትክን ልብ… (ይህንን ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)። … ደግሞ ኢህአዴግ ዘርህን ይበ… (ይህንንም ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)።
alemayehu-sentayehu
ይህ ጸያፍ ዘለፋ እና ማስፈራርያ እንግዲህ ወያኔ ምን ያህል እንደወረደ ያሳየናል። ከነውረኛ ስድቡ ባሻገር ደግሞ ቀላል የማይባል ድንበር ዘለል ሽብር ነው። ለዚህ ሽብር ተጠያቂ የሚሆነውም ተላላኪውና ሆድ አደሩ ብቻ ሳይሆን ላኪውም ጭምር ነው። ህወሃትን በመጠለል ልክ እንደ ISIS አንገትህን እቆርጥልሃለው ሲል መናገሩ መንግሥታዊ አሸባሪነት ለለመሆኑ ግልጽ ነው። ለዚህ ሰው ሲከራከር የነበረው ተሾመ ቶጋም ይህንን ሰምቶ ዝም የሚል ከሆነ የወንጀሉ ተባባሪ ይሆናል።

በዚህ አይነት ማስፈራራት አላማቸውን ማስፈጸም ካሰቡ ግን በጣም ተሳስተዋል። እንዲህ አይነቱ ነገር የበለጠ እልህ ውስጥ ያስገቡናል እንጂ በስራችን ላይ ቅንጣት ያህል ተጽእኖ ሊፈጥሩ አይችሉም። እንደጋዜጠኛ ለመስራት ስንነሳ ፍርሃትን ከእትብታችን ጋር ቀብረነው ነውና ይህንን የምትሞክሩ ተስፋ ቁረጡ ነው የምንላችሁ።

ይህ ሰው ከሆላንድ የመኖርያ ፈቃዱ ተነጥቆ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሰ በተለያዩ የዜና አውታሮች መዘገቡ ይታወሳል። ስለዚህ ሰው ጉዳይ ተሾመ ቶጋ (የወያኔ አምባሳደር) ከብራስልስ ማስተባበያ ሰጥቶ ነበር። ማስተባበያው ባጭሩ፣ “አለማየሁ ስንታየሁ ሰላይ አልነበረም። ከሆላንድም አልተባረረም። የተሰደደውም ከኢሃዴግ ዘመን በፊት ነው። … ይህ ደጋፊዎቻችንን ለማሸማቀቅ በአሸባሪ የተፈረጁ ሰዎች የሚያወሩት ወሬ ነው።” ይላል።

የሶስት ልህጆች አባት የነበረው አለማየሁ (ዘለቀ ፖላ) የሆላንድ የመኖርያ ፈቃዱን እና መኖርያ ቤቱን ተቀምቶ ከሄደ ሶስት ወራት አልፈዋል። ጉዳዩን ከሚመለከተው ክፍል በማጣራት የዜናውን እውነተኝነት አረጋግጠናል።

ዜናው በውጭ ያሉ የስርዓቱ ደጋፊዎችን በእጅጉ ያስደነገጠ በመሆኑ የተሾመ ቶጋ ማስተባበል የግድ ነበር። ውሸት ነው ማለታቸውም አይደንቅም። እውነት ተናግረው ሰምተናቸው ስለማናውቅ። አለማየሁ ስንታየሁ ችግር እንደነበረበት እና አስፈላጊውን ደብዳቤ ከኤምባሲው ተቅብሎ ወደ ኢትዮጵያ መሄዱን አቶ ተሾመ በቃለ-ምልልሱ አልሸሸጉም።

የተሾመ ቶጋን ውሸት ከሰማሁ በኋላ ጉዳዩን ለማጣራት የሚመለከታቸው የሆላንድ መንግስት አካላትን አነጋግሬአለሁ። ሶስት ክሶች ተመስርተውበት ነበር። አንደኛው ከወያኔ ካድሬዎች ጋር በመመሳጠር አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሃብትን እንዲታፈን በማድረጉ፤ ሁለተኛው ክስ የአሱን ስም በማጭበርበር እና፤ ሶስተኛ የሆላንድ መንግስትን ዋሽቶ የስደት ፈቃድ ከገኘ በህዋላ ለገዢው ፓርቲ ይሰልላል የሚሉ ነቸው።
ጭንቀት ውስጥ በነበረ ጊዜ ከአንዴም ሁለቴ ደውሎ በጉዳዩ ላይ አነጋግሮኛል። ከሚኖርበት አካባቢ እንዳይርቅ በሆላንድ መንግስት ታግዶ በነበረበት ወቅትም ከመገኛኛ ብዙሃን፤ በተለይ ከጀርመን እና ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር እንዳገናኘው ጠይቆኝ ነበር።

ይህ ሰው ወደ ሆላንድ የገባው በ1994 (ወያኔ ስልጣን ከያዘ ከአንድ አመት በህዋላ) በሰላም ተጓዥ ስም ነበር። ከዚያ ለበርካታ አመታት በስውር ከዚያም በግልጽ ለወያኔ ሲሰራ ነበር።

ጋዜጠኛ አፈወርቅ አገደው በፌስቡክ ገጹ ላይ ስለዚህ ሰው እንዲህ ሲል አስነብቦናል። “ይህን ግለሰብ በአካል አውቀወለሁ። ብዙ የቅርብ ጓደኞቼም ስለሚሠራቸው የስለላ ሥራዎቹ ያውቃሉ። ከራሱ አፍ እንደሰማሁት ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፖላ ነው። እዚህ ስደት የጠየቀበት ስሙ ዓለማየሁ ስንተሰየሁ ነው። የወላይታ አካባቢ ተወላጅ ነው። ተቃዋሚ መስሎ ለህወሓት ኤምባሲ ብዙ የስለላ መረጃዎችን የወያኔ ተቃወሚዎችን በሚመለከት እንደሚያቀብል ይታወቃል። … አንዳንዴ ስብሰባዎቹ ሌሎችን በሚያገልል መልኩ በትግርኛ ሲደረግ ዘለቀ ፖላ ይሳተፋል። ምኑ ገብቶህ ነው በማታውቀው ቋንቋ የምትሳተፈው ስንለው ጆሮዬ ክፉ ክፉውን ስለሚሰማ ለእናንተ ወሬ ለማቀበል ነው ይል ነበር።”

The post በስለላ ከሆላንድ የተባረረው የጋዜጠኛውን አንገት እቆርጣለሁ አለ (ድምጹን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>