(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ የመኪና አደጋዎች እየተባባሱ መጥተዋል:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሰሙ የሚመጡት ዜናዎች ዘግናኝ ከመሆናቸውም በላይ የሚጠፋውም የሰው ሕይወት በዛው ልክ ሆኗል:: ኢትዮ ኪክ ከአዲስ አበባ ባሰጨው ዜና የመከላከያው አማካኝ ተጨዋች ተክለወልድ ፍቃዱ በትላንትናው እለት በትውልድ ስፍራው ደብረዘይት አካባቢ በድንገተኛ የመኪና አደጋ እይወቱ አልፏል።
በመኪና አደጋው የተወልደ ወንድም ህይወቱ ሲያልፍ አብሮ የነበረው አንዱ ጓደኛቸው በከፍተኛ አደጋው እግሩ አጥቷል።
በትንሳኤው በዓል መዳረሻ በዚህ ከፍተኛ አደጋ ከአንድ ቤተሰብ ሁለት ነፍስ ማጣት ለቤተሰቦቻቸው እጅግ መራራ ሀዘን እንደሚሆን መገመት አይከብድም።
The post ታዋቂው እግር ኳስ ተጫዋች ከወንድሙ ጋር በመኪና አደጋ ሕይወቱ ጠፋ appeared first on Zehabesha Amharic.