በደቡብ ወሎ ዞን፤ ደሴ ከተማ ውስጥ አንድ የፖሊስ አባል ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን ደህሚት ዘገበ::
በተገኘው መረጃ መሰረት በአማራ ክልል፤ ደቡብ ወሎ ዞን፤ ደሴ ከተማ፤ 05 ቀበሌ፤ አሬራ በተባለው አካባቢ ሳጅን ሃቢብ እንዳለ የተባለው የጎጃም አካባቢ ተወላጅ የሆነው የፖሊስ አባል ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መጋቢት 2/2007 ዓ/ም ተገድሎ መገኘቱ ታውቋል::
መረጃው በማስከተል በአማራ ክልል የሚገኘው ህዝብ በአገር ደረጃ ለ5ኛ ግዜ በሚደረገው አስመሳይ ምርጫ አንሳተፍም፤ የምንመርጠው አካልም የለም ብሎ በመቃወም ላይ ባለበት ባሁኑ ግዜ በስርዓቱ ካድሬዎችና ፖሊሶች ተገዶ ከቤቱ እንዲወጣ በማድረግ የማትመርጥበት ምክንያት ምንድ ነው እያሉ እረፍት ነስተውት እንደሚገኙ የገለጸው መረጃው በፖሊሱ ላይ የተወሰደው እርምጃም በድርጊቱ የተቆጡት ወገኖች የፈጸሙት ሊሆን እንደሚችል በርካታ ወገኖች በመገመት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል::
The post በደቡብ ወሎ ደሴ ከተማ አንድ ፖሊስ ተገድሎ ተገኘ appeared first on Zehabesha Amharic.