(ዴ.ም.ህ.ት) በ12ኛ ክፈለ ጦር ለሚገኙ ወታደሮች ደመወዝ ለመክፈል ሲሄዱ የነበሩ አራት መኮነኖች ከመተማ ወደ ኮር-ሁመር በሚወስደው መንገድ ላይ ተገድለው እንደተገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ::
እነዚህ በወታራዊ መኪና እየተጓዙ የነበሩ የ12ኛ ክፍለ ጦር የፋይናንስ ሰራተኛ የሆኑ አራት መኮነኖች መጋቢት 2/2007 ዓ.ም ከመተማ ወደ ኮር ሁመር በሚወስደው መስመር ላይ ሲደርሱ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እንደተገደሉ የገለፀው ይህ መረጃ ይዘውት የነበረው የክፍለ ጦሩ ጠቅላላ ደመወዝ 4 ሽጉጥ፤ 4 ክላሽና ሌላም ንብረታቸውን ባልታወቁ ገዳዮች እንደተወሰደ ሊታወቅ ተችሏል::
እነዚህ ለጊዜው ስማቸው ያልተገለፀው ሟቾች የስርዓቱ የወታደር አባላት ሁለት የፋይናንስ አባላት የሺህ አለቃ ማዕረግ ያላቸው አንድ ሻንበልና አንድ ደግሞ የመቶ አለቃ ማዕረግ ያላቸው አራት መኮነኖች እንደሆኑ የደረሰን መረጃ አክሎ አስታውቋል::
ምንጭ. ዴ.ም.ህ.ት
The post በ12ኛ ክፈለ ጦር የሚገኙ አራት መኮነኖች ተገድለው ተገኙ appeared first on Zehabesha Amharic.