Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ኢንጂነር ይልቃል “የጠመንጃው ትግል ሰላማዊ ታጋዮችን ከማስበላት ውጭ በ24 ዓመታት ውስጥ ያመጣው ለውጥ የለም”አሉ

Next: Hiber Radio: “በሳዑዲ አረቢያው ላይ እንደተደረገው በየመን ላሉ ኢትዮጵያውያን መጮህ አለብን ተባለ.. የቻይና የባህር ሀይል አባላት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከየመን ከ200 በላይ የ10 አገር ዜጎችን ታደጉ…አቶ እንዳርጋቸው ፅጌን ለማስለቀቅ የእንግሊዝ መንግስት ዛሬም ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየ.. የግብጹ ሚድያ ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር የፈረሙትን ፊርማ የግብፅን ህዝብ አይወክልም አለ…የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ልደት ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከበረ…እና ሌሎችም
$
0
0

Hiber Radio Interview with Eng Yilkal Getnet
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በቦስተን ለኢትዮጵያውያን በስካይፕ ባደረጉት ንግግር የጠመንጃ ትግል ለ24 ዓመታት ተደርጎ አንዳችም ውጤት አላመጣም ሲሉ ተናገሩ:: ኢንጂነሩ በንግግራቸው በጠመንጃ ይደረጋል የተባለው ትግል ሰላማዊ ታጋዮችን ከማስበላት ውጭ ያመጣው ውጤት የለውም ብለዋል::

‹‹ሰላማዊ ትግል አያዋጣም የሚባለው ትክክል አይደለም፡፡ ጠመንጃ ያወጣል የሚሉት የራሳቸውን መንገድ መምረጥ መብታቸው ነው፡፡ ነገር ግን ለ3000 አመት የጠመንጃ ትግል ውስጥ ነን፡፡ ግን ምንም አይነት ውጤት አላመጣም፡፡ ለ24 አመት የጠመንጃ ትግል አለ፡፡ ግን አንድ ቀበሌ ሲቆጣጠር አላየንም፡፡ እንዲያውም ብዙዎቹን ሰላማዊ ታጋዮች አስበልቷል፡፡ ይህ ሁሉ ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ የታሰረው ሰላማዊ ትግሉ ስጋት ስለፈጠረበት ነው፡፡ ይህንን ስንል ግን ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ ለትግሉ ቅን ናቸው ከሚል አይደለም›› የሚሉት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹ሰማያዊ ትግሉ የፖለቲከኞች ሳይሆን የህዝብ እንዲሆን እየሰራ ነው፡፡›› ብለዋል::

‹‹ዋጋ በከፈልን ቁጥር ይህ የከፈልነው ዋጋ ወደ ህዝብ እየወረደ እየበዛን እየመጣን ነው፡፡ እነ እስክንድርና እነ አንዱዓለም ሲታሰሩ እኔ የግል ስራዬን ነው የምሰራ ብዬ ትግሉን ብተወው፣ ሌሎቹም እንደዛው ቢያደርጉ ተስፋ ያስቆርጥ ነበር፡፡ አሁን ግን እየተበራከትን ነው፡፡ አንድነትን ሲያፈርሱት አባላቱ ከትግሉ አልሸሹም፡፡ እናም የምንከፍለው ዋጋ እየባከነ አይደለም፡፡›› ያሉት የሰማያዊ ፓርቲው ሊቀመንበር ‹‹እኛ ሊያስሩን ይችላሉ፡፡ ከምርጫው ወጥተዋል ብለው ሊያወሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ለራሳቸው ነው የሚብቸው፡፡ በደላቸው ይበልጡንም የሚያጠናክር ነው የሚሆነው፡፡ ዛሬ ስልጣኑ ላይ ቢሆኑም አፈናው በእነሱ ጩኸት እንዲበዛባቸው የሚያደርገው፡፡ ነውረኛ ተግባራቸው ይበልጡን እህልና ቁጭት ይፈጥራል እንጅ ከትግል አያባርረንም፡፡›› ብለዋል::

‹‹እኛ የምንለው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ይደረግ ነው፡፡ ኢህአዴግ እኛ በምርጫ ስም ብጥብጥ እንደምንፈጥር ነው የሚሰጋው፡፡ ነገር ግን ይህ እነሱ የሙፈሩት ነገር የሚመጣው እነሱ ሲፈሩና ይበልጡንም ነገሮችን ሲያበላሹ ነው፡፡ ህዝብ በገዥውም ሆነ በተቃዋሚዎች ተስፋ ሲያጣ ያንን መንገድ መምረጡ አይቀርም፡፡ እኛ ይህ ችግር እንዳይከሰት ነው እየሰራን ያለነው፡፡›› ያሉት ኢ/ር ይልቃል ፓስፖርታቸው ካልተመለሰ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ተይዞላቸው የነበረው ስብሰባ በስካይፕ እንደሚቀጥል ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::

The post ኢንጂነር ይልቃል “የጠመንጃው ትግል ሰላማዊ ታጋዮችን ከማስበላት ውጭ በ24 ዓመታት ውስጥ ያመጣው ለውጥ የለም” አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>