Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ድምጻችን ይሰማ:- ትግላችን ከየት ወደየት?

$
0
0

ክፍል 1 –

ላለፉት 3 ዓመታት በጽናትና በህዝባዊነቱ እያደገ የሄደው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሃይማኖት መብት የማስከበር ህዝባዊ ትግል ከእርከን እርከን እየተሸጋገረ አሁን ያለበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ገና ከጅምሩ መንግስት የሙስሊሙን የመብት ማስከበር ትግል ለማኮላሸት ያላደረገው ጥረት አልነበረም፡፡ መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ከውስጥ ለመሰንጠቅ በመሞከር እና የሙስሊሙ የመብት ጥያቄ በሌላው እምነት ተከታይ እና በሃገር ላይ የተቃጣ አደጋ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ ያካሄደው የከሸፈ ፕሮፓጋንዳ በቀላሉ የሚረሳ አይደለም፡፡ ግና የመንግስትን የጥፋት ተልዕኮ ገና ከጅምሩ የተረዳው ህዝባችን ሁለቱንም ሰንኮፎች ለመንቀል ያደረገው ጥረት የተሳካ ነበር፡፡
muslim 1
በእነዚህ ውጣ ውረድ በተሞላባቸው ዓመታት ህዝባዊ ትግሉ የተሳኩ መስጂድ ተኮር ተቃውሞዎችን ከማካሄድ አልፎ አቻ የማይገኝላቸው የአደባባይ ትዕይንተ ህዝቦችን በሁለቱ የዒድ በዓላት በተደጋጋሚ ለማካሄድ ችሏል፡፡ በእነዚህ እንቅስቃሴዎች የሙስሊሙን አንድነት ከማጠናከር በተጨማሪ የመንግስት የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ማሽኖች በማህበረሰባችን ዘንድ ሊያሰርጹት የሞከሩትን እኩይ ሴራ በብቃት ለመመከት ተችሏል፡፡ በመላው የሃገሪቱ ክፍሎች በተካሄዱ የተቃውሞ መርሃ ግብሮች የህዝበ ሙስሊሙን የሰለጠነና ህገ መንግስታዊ አካሄድ ለማመስከር የተቻለ ሲሆን የመንግስትን ፕሮፓጋንዳም ባዶ ለማስቀረት ተችሏል፡፡ እንቅስቃሴው በአዲስ አበባ በተጀመረበት ሰሞን በክልል ከተሞች የሚገኘው ማህበረሰብ በመንግስት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ተፈጥሮበት የነበረው ብዥታ እንዲጠራ ማድረግ የተቻለውም ብዙም ሳይቆይ እንቅስቃሴውን ወደ ክፍለ ሃገራት በማሳደግና ማህበረሰባችን እውነቱን በአይኑ አይቶ የሚፈርድበትን እድል በመፍጠር ነበር፡፡
muslim1
በእርግጥ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በአፋኝ አምባገነናዊ ስርዓት ውስጥ የሚካሄድ እንደመሆኑ መጠን በስጋት የተሞላ ነበር፡፡ ሆኖም ህዝባችን በስነ ልቦናም ሆነ በተከተለው ስልት መንግስትን በልጦ በመገኘቱ በኢትዮጵያ ምድር የሰላማዊ ትግል ፈር ቀዳጅነትን ተጎናፅፏል፡፡ መንግስት መንግስት ከሚያሰኙ ባህሪያት ወጡ ጋጠወጥነቶችን በሚፈጽምበትና ሰላማዊውን የትግል መስመር ለማደፍረስ ከደህንነት ሃይሎቹ አልፎ ፖሊሶችና መከላከያ ሓይሎችን ጭምር ባሳተፈበት ወቅት ሁሉ ሰላማዊነቱን ጠብቆ ከሁለት ዓመታት በላይ የተሳኩ የተቃውሞ ትዕይንቶች ማካሄድ ፈታኝ ቢሆንም ህዝባችን ግን የሚቻል የማይመስለውን አድርጓል፡፡ የመርሃ- ግብሮቹ ስኬት በተሳታፊው ማህበረሰብ የንብረት፣ የአካል፣ ብሎም የህይወት መስዋዕትነት የተገኘ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ አሳሳ፣ ገርባ፣ አወሊያ፣ ደሴ፣ ከሚሴ፣ ሻሸመኔ፣ ወልቂጤ፣ አንዋር፣ ፍልውሃ… የፈሰሰው ደም፣ የተደፈረው ሰብዓዊ መብት፣ የተዘረፈው ንብረት ሁሉ ህዝባችን ለሃይማኖቱ ያለው ቀናኢነት እና ሃይማኖታዊ መብቱን ለማስከበር የማይከፍለው መስዋዕትነት እንደሌለ ያሳየበት የማይፋቅ የመስዋእትነት አሻራ ነው፡፡ (ይቀጥላል…)

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!

The post ድምጻችን ይሰማ:- ትግላችን ከየት ወደየት? appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>