‹‹የህዝብ ወኪሎችን በነጻ ከማሰናበት ያነሰ ብይን አንቀበልም!››
አርብ መጋቢት 18/2007
በወኪሎቻችን የሽብር ክስ ‹‹የተከሰስነው እኛ ነን!›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 21/2007 ሊካሄድ የነበረው ሁለተኛው የትዊተር ዘመቻችን ወደ ሚያዝያ 19/2007 ተዛወረ! ይህ እንዲሆን የተወሰነው የውድ ወኪሎቻችን የብይን ቀጠሮ ባለፉት ቀናት በፍርድ ቤት ትእዛዝ ከመጋቢት 30 ወደ ሚያዝያ 30 እንዲሸጋገር በመደረጉ ነው፡፡
ለዘመቻው የምናደርገው ህዝባዊ ቅስቀሳ እና ዝግጅት እስከሚያዝያ 19 ባለበት እንደቀጠለ የሚቆይ ሲሆን ሰፊ የቅስቀሳ ጊዜ መኖሩም ዘመቻውን በተሻለ ስኬት ለመስራት ይበልጥ አመቺ እንደሚያደርገው የሚታመን በመሆኑ ሁላችንም የፌስቡክ ገጻችንን ፎቶ አሁን በተለጠፈው ፎቶ ዳግም በመቀየር በጀመርነው የቅስቀሳ ስራ ይበልጥ እንድንገፋበት አደራ እንላለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!
‹‹የህዝብ ወኪሎችን በነጻ ከማሰናበት ያነሰ ብይን አንቀበልም!››
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
The post ሁለተኛው የትዊተር ዘመቻ ከመጋቢት 21 ወደ ሚያዝያ 19 ተዛዋረ!!! appeared first on Zehabesha Amharic.