(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባርን ይዘው ወደ አዲስ አበባ የገቡት ኦቦ ሌንጮ ለታ ኢትዮጵያ በገቡ በ72 ሰዓታት ውስጥ ወደ አውሮፓ መመለሳቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ:: ኦዴፍ ውስጥ ያሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደገለጹት ኦቦ ሌንጮ ለታ በኢትዮጵያ መንግስት ተባረዋል የሚባል ነገር ቢሰሙም ማረጋገጥ ግን አልተቻለም::
ዘ-ሐበሻ የአቶ ሌንጮ ለታን ጉዳይ ለማጣራት ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሌንጮ ባቲ ጋር የደወለች ሲሆን ከ7 ጊዜ በላይ ብንሞክርም ስልካቸው ስለማይነሳ ሌንጮ ለምን እንደተመለሱ ማረጋገጥ አልተቻለም::
The post ወደ ኢትዮጵያ የሄዱት ሌንጮ ለታ በ72 ሰዓት ወደ አውሮፓ ተመለሱ * መንግስት አባሯቸው ነው ይባላል appeared first on Zehabesha Amharic.