የትግራይ ነጻ አውጪ ኢትዮጵያን መምራት ከጀመረ 24 አመታትን አስቆጥራል። በዚህ የጭለማ ዘመን ኢትዮጵያዊው በወያኔ ጭፍን ጥላቻ እንደ ጭቃ እየተረገጠ መገዛት ከጀመረ አመታቶች ተቆጠሩ። እነዚህ ጨለምተኞች በአፋቸው እውነት የማይናገሩ ልቦናቸው ቂም ያረገዘ፣ አእምሮአቸው በክፋት የተመረዘ፣ የአስተሳሰብ ደሃ፣ ዘረኛ እና ዘረኝነትን በሰው ልቦና የሚዘሩ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ የተጠሉ የደደቢት በቆልቶች ናቸው::
ኢትዮጵያን ከTPLF አፓርታይድ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት የሚታገለው ግንቦት 7 አሸባሪ ነውን? እስቲ በከፊል እንመልከት፡-
ወያኔ ያሰመረው መስመር አለ ያም መስመር ኢትዮጵያን የሚያጠፋ መስመር ነው። ህዝብን ከህዝብ ጋር፣ ዘርን ከ ዘር ጋር፣ ጎሳን ከጎሳ ጋር፣ የሚያጋጭ መስመር ነው። ኢትዮጵያኑ ሀይማኖታቸውን በነጻነት እንዳያምኑ የሃይማኖት አባቶችን እንዳይመርጡ በነጻነት ፈጣርያቸውን እንዳያመልኩ የሚያደርግ መስመር ነው። ዜጎች ሲኖሩበት ከነበረው ቄያቸው ካለበቂ ካሳ የተወሰኑ አካላትን ለመጥቀም ሲባል ብቻ ለልማት በሚል ሰበብ ማፈናቀል እና የጎዳና ተዳዳሪ ተመጽዋች የሚያደርግ መስመር ነው። ነፍስ ጡር እህቶቻችንን አጥንታቸው እስኪሰበር የሚቀጠቅጥ መስመር …መብታቸውን የጠየቁ የነጻነት ታጋዮችን ወደ ጭለማ ቤት የሚወረውር መስመር… ኸረ ስንቱ ተጠቅሶ ይቻላል…።’
ይሄን የባርነት እና የሽብርተኝነት አገዛዝ አይኑን በጥቁር ጨርቅ ሸፍኖ ምንም እንዳልተፈጠረ እራሱን አሳምኖ የሚቀበል ካለ ወያኔ ከደገሰው ድግስ መመገብ ይችላል ወያኔ ከካበው የእንቧይ ካብ መሰቀል ይችላል።
ከመስመሩ ውጪ የሆኑትን ሁሉ ተለጣፊ ታርጋ እየተስጣቸው አንተ ግንቦት 7 ነህ፣ አንተ ኦነግ ነህ፣ አንት ኦብነግ፣ እያሉ የፖለቲካ እንቅስቃሲያቸውን ለማጥፋት ይጠቀሙበታል። እውን ግን በዚህ በማፈን ስራ እና በማጠልሽት ድርጊታቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ሊያቆሙት ይችላሉን?
የወያኔው መሪ በአንድ ወቅት ጠንካራ ተቃዋሚ የለም ብለው በተናገሩ ማግስት መሬት ያንቀጠቀጠ ደጋፍ ያገኙት ቅንጅቶች ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በምርጫ በካርድ አሳያቸው ይሄን ያዩ ጊዜ ወደ ሚኒሊክ ቤተመንግስት በታንክ እንጂ በካርድ መች ገባን በማለት የተሰረቀው ድምጻችን ይመለስል ብለው አደባባይ በወጡ ሰላማዊ ዜጎቻችን ላይ ግንባራቸው ላይ 11 ቁጥር ታፔላ ባስገጠሙ አጋዚ ወታደሮች በጠራራ ጸሃይ በጥይት ተቆሉ የንጹሃን ደም በየጎዳናው ፈሰሰ ያን ጌዜ ነበር የኢትዮጵያ ህዝብ በመረጣቸው አካላት ሊመራ እንደማይችል በመረዳታቸው ይህን መሰዋትነት ለመክፈል የተዘጋጁ በጥቂት ግዜ ውስጥ ግንቦት 7፣ አርበኞች ግንባር እንዲሁም ሌሎች ብረት አንስተው ወደ ጫካ ተመሙ። ይሄም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የህዝብ ቁጣ ሲያዩ ውስጣቸው ተሸበረ ስራቸውንም ስለሚያውቁ መርዘኛ ተግባራቸውን ማሰራጨት ጀምረዋል።
ወያኔ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ግልጽ እና እውቀት ያለው እንዲሁም ሰለ አገር አሳቢውን በተሰመረላቸው መስመር ላይ ይገቡ ዘንድ ግድ ይላቸዋል። በዚህ መስመር ያልገቡትን በሙሉ ስም ይለጥፍላቸዋል አንተ ከኢሳት እና ከ ግንቦት7 ጋር ግኑኝነት አለህ የሻብያ ተላላኪ ነህ አልያም እነዚህ ድርጅቶች ትረዳለህ በሚል ሰበብ ክስ ይቀርብባቸውና ወደ እስር ቤት ይወረወራሉ።
ወያኔ በፖለቲካና ፖለቲከኞች ዙርያ በወያኔ አዙሪት ውስጥ እንዲዞሩ ይጠየቃሉ በዚህ አዙሪት ውስጥ ገብተው አራሳቸውን አዙረው የኢትዮጵያን ህዝብ አዙሪት ውስጥ እንዲከቱ ይደረጋሉ የለም የወያኔ ፖለቲካ አዙሪት ኢትዮጵያን አጥፊ ነው ስርዓቱም የበሰበሰ የዘረኝነት ፖለቲካ የሚከተል ነው ይህ የዘር ፖለቲካ ደግሞ እንደ ርዋንዳ ከመጨራረስ እና ከመተላለቅ ውጭ ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት ነገር የለም። ይህ የዘር ፖለቲካ በአንድ አገር የሁሉንም መብት ባለማክበር እልቂትን የሚያመጣ እንጂ እድገትና ፍቅርን አይሰጠንም። ይሄ የዘር ፖለቲካ ለመሰረተውም ለሚከተለውም እንዲሁም ለሁሉም ህብረተሰብ በመጠፋፋት የፀፀት ታሪክ እንጂ የወደፊታን ኢትዮጵያን አይጠቅማትም ብለው የፖለቲካ ፓርቲ መስርተው አቋማቸውን በግልጽ አሳውቀው እየተንቀሳቀሱ ባሉት ፓለቲከኞች ላይ በ 24 አመት ውስጥ ምንም ያልተለወጠውን የወደቀ እና የተናቀ ስራውን በመስራት የአሸባሪነት ስም ሰጥቶ እስር ቤቱን የንጹሃን ዜጎች ማሰቃያ ካደረገው አመታቶችን ቆጥሩ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አንድ ሆነን የምንሳበት ጊዜው አሁን ነው። ከአሁን በኋላ ወያኔ እያሰረን እየገደለን እንዲኖር ለደቂቃም ቢሆን መፍቀድ የለብንም። ዘርን ከዘር፣ ሐይማኖትን ከሐይማኖት፣ አጋጭቶ እራሱ ጥግ ሆኖ ሊስቅ የፈለገን በኢትዮጵያን ምድር ላይ የበቀለ ወያኔ የተባለውን ባንዳ ጠላት በጋራ ሆነን እናሰወግድ። ለነጻነት እና ለፍትህ ለእኩለነት የሚታገለው የግንቦት7 መሪዎችን የምናውቃቸው አብረውን የነበሩ ሰለ ኢትዮጵያ መጽአኢ ተስፋ ቀን ከለሊት የሚተጉ ሰለ አንዲቷ ኢትዮጵያ ሲሉ መስዋት ለመሆን የተዘጋጁ መሆናቸውን ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው። ስለዚህ የቻልን ወደዚህ የትግል ጎራ እንቀላል። ሁሉም በያለበት ለነጻነቱ ሲል ይደራጅ። ገበሬውም ሞፈሩን፣ ተማሪውም ብዕሩን፣ አስተማሪውም ጠሜኔውን፣ ነጋዴውም ብሩን፣ ወታደሩም ብረቱን ያንሳ። የሐይማኖት ሰዎችም ጸሎታችሁን ሰለ ኢትዮጵያ ብላቹህ በአንድነት አሰሙ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን የሚታደጋት አምላክ አላትና ። ለ24 አመት ኢትዮጵያን ሲያሸብር የኖረውን ወያኔን እናጥፋ። ሞት ለዘረኞች እና ለዘርዛሪዎች ይሆናል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ከሳሙኤል አሊ (ከኖርዌይ)
22.03.2015
samilost89@yahoo.com
The post ማነው አሸባሪ የትግሪይ ነጻ አውጪ ግንባር? ወይስ ኢትዮጵያዊው ግንቦት ሰባት? – ከሳሙኤል አሊ appeared first on Zehabesha Amharic.