የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል ‹‹መብቴን ካላከበርክ እኔም….. !›› ወደሚልበት የትግል ምዕራፍ መሸጋገሩ
ጋዜጠኛ ተመስገን በማረሚያ ቤት ህክምና መከልከሉ
የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ‹ሰጡ›
የደቡብ ሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ አማጽያንን ይደግፋል ተባለ
……..
አርበኞች ግንቦት 7 ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ!በሚል ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ከህወሓት ዘረኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የሚመኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲደራጅ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን! እያንዳንዱ ነፃነት ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ከሚያምነውና ከሚመስለው ወዳጁ ጋር ይቧደን፤ ቡድኑንም በሥርዓትና በሚስጢር ያደራጅ ብሏል በመግለጫው አክለውም
ከእንግዲህ “ምን እንሥራ፧ ትግሉን እንዴት እንርዳ?” እያሉ ለሚጠይቁ ወገኖቻችን በሙሉ መልሳችን “ከቻላችሁ ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ” የሚል ነው ያሉ ሲሆን ድርጅት ኃይል ነው። መደራጀት በራሱ ትልቅ ሥራ ነው። ድርጅት ድርጅት የሚሆነው ደግሞ በሥርዓት ሲዋቀርና በሥነሥርዓት ሲመራ ነው። ስለሆነም ነፃነት ናፋቂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ አደራጅና አስተባባሪ እንዲመጣለት ሳይጠብቅ በራስ አነሳሽነት እንዲደራጅ ይህ ጥሪ ተላልፏል ብለዋል::
በመጨረሻም
በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተባባሪና መመሪያ የሚጠብቅበት ጊዜ አልፏል። ህወሓት የዘረጋው የአፈና ሥርዓት የጠበቀ ትስስርና ቁጥጥር ያለው ድርጅት ማቆም እንዳይቻል አድርጓል። ስለሆነም ያለን አማራጭ ያለ በላይ አካል ትክክል ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር የሚችሉ ስብስቦችን በመላው የአገራችን ክፍሎች በአፋጣኝ ማደራጀት ነው። ይህንን ደግሞ ማድረግ ይቻላል።
ወቅቱ ህወሓትን ከጫንቃችን ላይ ለማውረድ የምንደራጅበት ነው። ድርጅት ኃይል ነው፤ አደራጅና አስተባባሪ ሳንጠብቅ በራስ ተነሳሽነት ዛሬውን እንደራጅ!የሚል ጥሪ አቅርባል::
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል ‹‹መብቴን ካላከበርክ እኔም….. !›› ወደሚልበት የትግል ምዕራፍ መሸጋገሩ ተገለፀ!
ለ 3 አመታት በተለያዩ የሰላማዊ ትግል ዘዴዎች መብቴን አክብሩ ሲል የቆየው ህዝበ ሙስሊም የህዝብን ድምፅ ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆነው የሃገራችን መንግስት በቀጣይ የህዝብን ድምፅ ይሰማ ዘንድ ወደሚያስገድዱ ህዝባዊ እንቢተኝነት ትግሉ መሸጋገሩን ድምፃችን ይሰማ አስታውቋል፡፡
የአንድ መንግስት ህልውና ህዝቡ ፍቃደኝነት ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ያለው የድምፃችን ይሰማ መግለጫ ሕዝብ ሲመረውም ‹‹መብቴ ይከበርልኝ›› ከሚል ጩኸት ‹‹መብቴን ካላከበርክ እኔም….. !›› ወደሚል ዛቻ መሄዱ አይቀሬ ነው ብላል ይህን ጊዜ ሕዝቡ ‹‹ትብብር የመንፈግ ትግል ውስጥ ገባ›› ይባላል፡፡ ይህ ዓይነቱ ትግል ውጤታማ መሆኑ አይቀሬ እንደሆነ የዘርፉ ምሁራን አጽንኦት ሰጥተው ያስተምራሉ፡፡በማለት አክለውም
በጨዋ ደንብ እና በአንጸባራቂ ሰላማዊ ስነ ምግባር ለሶስት ዓመታት መብቱን ሲጠይቅ እና ሲታገል የቆየው ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ‹‹መብቴ ይከበርልኝ›› ከሚል ያልተሰማ ጥያቄው ‹‹መብቴን ካላከበርክ እኔም….. !›› ወደሚልበት የትግል ምዕራፍ ላይ እነሆ ደርሰናል! ሰሞኑን ይህንኑ አስመልክቶ የምንለው ይኖራልና ሁላችንም ቃል የገባንበትን ትግል እስከድል ደጃፎች ለማድረስ ወገባችንን እናጥብቅ፤በማለት ጥሪ አቅርባል::
ጋዜጠኛ ተመስገን በማረሚያ ቤት ህክምና መከልከሉ ተነገረ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ: በእስር በሚገኝበት የዝዋይ ማረሚያ ቤት: በጤና አገልግሎት እጦት እንደተቸገረ ሲፒጄ አስታወቀ. የጋዜጠኞች የመብት ተቆርቋሪው ቡድን ሲፒጄ : ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነ: ጋዜጠኛ ተመስገን በማረሚያ ቤት የጤና አገልግሎት እንዳያገኝ ስለተከለከለ: በሆድና በወገብ ህመም እየተሰቃየ እንደሆነ አመልክቷል.
ጥቅምት ላይ የሶስት አመታት እስር ተፈርዶበት: በዝዋይ ማረሚያ ቤት የሚገኘው ተመስገን ደሳለኝ :ከመታሰሩ ቀደም ብሎ በየሳምንቱ የህክምና ክትትል ያደርግ እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን: አሁን ግን በእስር ቤቱ ባለስልጣናት: የህክምና አገልግሎት በመከልከሉ የተነሳ :በተለይ የጀርባ ህመሙ በመባባሱ: መሄድ እስከሚያቅተው እንደተቸገረ የሲፒጄ መግለጫ ይዘረዝራል.
የቀድሞው የፍትህ ጋዜጣ ባለቤት የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ: አመጽን የሚያነሳሱ የሀሰት ወሬዎችን በመጻፍ: እንዲሁም የሰዎችን መልካም ስም በማጉደፍ በሚሉ ወንጀሎች ተከሶ :የሶስት አመታት እስራት እንደተፈረደበት ይታወቃል.
ይሁን እንጂ የክሱን መዝገብ በሚገባ መገምገሙንና :ማጥናቱን የሚናገረው ሲፒጄ :ተመስገን ለእስር የተዳረገው :የተባሉትን ወንጀሎች ሰርቶ ሳይሆን :በሚያወጣቸው ጽሁፎች መንግስትን ደጋግሞ በመተቸቱ ነው ሲል: መንግስትን ይከሳል. እስር ቤት ከገባም በኋላ: የእስረኞችን አያያዝ በተመለከተ: አንድ ጽሁፍ ከዛው ሆኖ በመጻፉና በተለያዩ ሚዲያዎች በመታተሙ የተነሳ :በማረሚያው ባለስልጣናት ማንም ዘመድ ወዳጅና ቤተሰብ እንዳይጎበኘው ለወራት ተከልክሎ መቆየቱን ሲፒጄ :ይናገራል.
ድርጅቱ ማረሚያ ቤቱ በተመስገን ላይ የሚፈጽመውን የመብት ጥሰት ለማስቆም: ለኢፌድሪ ፍትህ ሚኒስቴር እንዲሁም አሜሪካ ላለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ :በተደጋጋሚ ጊዜ በስልክና በኢሜል ጥያቄ ማቅረቡን ጠቅሶ :ይሁን እንጂ ከመንግስት በኩል ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጠው ተናግሯል.
በሀገሪቱ የጋዜጠኞች ይዞታ ላይ የራሱን ጥናት እንዳደረገ የሚገልጸው ሲፒጄ :መንግስት 17 ጋዜጠኞችን ማሰሩንና: ከ 30 የማያንሱ ደግሞ መሰደዳቸውን ይናገራል. የኢትዮጵያ መንግስት: ተቋሙ የሚያወጣቸውን ሪፖርቶችና ማሳሰቢያዎች ወደጎን በማለት: ይህን ጋዜጠኞችን የማፈን ተግባሩን እንደገፋበት የሚገልጸው ድርጅቱ :በተለይ ከመጪው የግንቦት ምርጫ በፊት : ብዙሀኑን ነጻ ሚዲያና ጋዜጠኞች የማፈን ተግባሩን ቀጥሎበታል ሲል መንግስትን ከሷል.
የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ‹ሰጡ›
በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ :የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና :ሌሎች በተመሳሳይ መዝገቡ የተካተቱ ተከሳሾች: በተከሰሱበት ድርጊት ላይ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ አመራሮችን ጨምሮ 10 ተከሳሾች: መጋቢት 10/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን : ተከሳሾች በቀረበባቸው ክስ ላይ: የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መሰረት: ከአንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ጀምሮ፣ ‹‹በክሱ ላይ የተመለከተውን ድርጊት ፈጽመዋል ወይስ አልፈጸሙም?›› የሚል ተመሳሳይ ጥያቄ ለእያንዳንዳቸው የቀረበላቸው ሲሆን: ብዙዎቹ ተከሳሾች ምላሻቸውን በቀጥታ ለመስጠት አለመፈለጋቸውን አሳይተዋል፡፡
1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ: ለቀረበለት ጥያቄ፣ ‹‹በአቃቤ ህግ እና በፖሊስ ተቀነባብሮ የቀረበብኝን ክስ በተመለከተ ለክሱ እውቅና ላለመስጠት ምንም አልልም፡፡ በክሱ ላይ አስተያየት በመስጠት: ለጸረ-ሽብር አዋጁ እውቅና መስጠት አልፈልግም›› የሚል መልስ በመስጠቱ: ፍርድ ቤቱ ክሱን ክዶ ቃል እንደሰጠ አድርጎ መዝግቦታል፡፡
2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው በበኩሉ: ‹‹በክሱ ላይ የተመለከተውን ድርጊት እንዳልፈጸምኩ : እንኳን እኔ ከሳሾቼም በደንብ ያውቃሉ፡፡ ከሳሾቼ: እኔ ድርጊቱን የመፈጸም ፍላጎቱም ሀሳቡም እንደሌለኝ ያውቃሉ›› ብሏል፡፡
3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሽ ደግሞ፣ ‹‹እኔ ስለ ሽብር የሰማሁት ከአልቃይዳው መሪ ኦሳማ ቢላደን እና መለስ ዜናዊ ነው፡፡ እኔ አሸባሪ አይደለሁም፤ ሀሳቡም ሆነ ፍላጎቱም የለኝም፡፡ ባህሌና እምነቴም አይፈቅድልኝም›› ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡
4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ ‹‹አሸባሪ ማለት የፖለቲካም ሆነ ሌላ ዓላማውን: ሰላማዊ ዜጎችን በማሸበር ለማስፈጸም የሚሰራ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው አሸባሪ ድርጅት ህወሓት/ኢህአዴግ ነው፡፡ እኔ ደግሞ የዚህ አሸባሪ ድርጅት ተቃዋሚ ነኝ›› በሚል ምላሽ ሲሰጥ
5ኛ ተከሳሽ የሺዋስ አሰፋ በበኩሉ፣ ‹‹በመጀመሪያ ለመጨረሻ ጊዜ ስለሆነ የምናገረው እንዳታቋርጡኝ አደራ እላለሁ፡፡ ክሱ ቅንብር ነው፡፡ ዳኞችም ህጉ የሰጣቸው ነጻነት አይታይባቸውም፡፡ ይህ 19ኛ ወንጀል ችሎት የጦር ችሎት ነው የሚመስለኝ፡፡ ስለሆነም የጦር ችሎት በሚመስል ችሎት እየተንገላታን ነው›› ሲል ተናግሯል፡፡ የሺዋስ በዳኞች በተደጋጋሚ ንግግሩ እንዲቅረጥ ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም ክሱን ክዶ ቃል ሰጥቷል በሚል ተመዝገቦለታል፡፡
በአጠቃላይ ተከሳሾች ክሱ ላይ የተጠቀሰውን ድርጊት ክደው ቃል በመስጠታቸው አቃቤ ህግ ምስክሮችን እንዲያሰማ ለግንቦት 13፣ 14፣ 15/2007 ዓ.ም ለተከታታይ 3 ቀናት ምስክር እንዲሰማ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ በተየያያዘ ዜና
የዞን 9 ጦማሪያና ጋዜጠኞች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንደተሰጠባቸው ታውቃል
አቃቤ ሕግ በተከሻሾች ላይ ያቀረበው የኦዲዮ ሲዲ ማስረጃ እንዲደርሳቸው ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ችሎቱ ብይኑን ስላልጨረሰ ለመጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጠባቸው…….
የደቡብ ሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ አማጽያንን ይደግፋል ተባለ
በሳልቫኪር የሚመራው የደቡብ ሱዳን መንግስት ኢትዮጵያን የሚወጉ አማጽያንን እንደሚያደራጅና እንደሚደግፍ ተነገረ፡፡ ሱዳን ትሪብዩን የደቡብ ሱዳን አማጽያንን ጠቅሶ እንዳወራው ከሆነ የደቡብ ሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በገጠመው ቅያሜ ምላሽ ለመስጠት ሲል ኢትዮጵያን በጋምቤላ በኩል የሚወጉ አማጽያንን እያስታጠቀ ይልካል ሲል አውርቷል፡፡
አስተማማኝ መረጃ ማግኘታቸውን የገለጹት የደበብ ሱዳን አማጺያን መሪ የሪክ ማቻር ቃል አቀባይ ጋትዴት ዳክ ለሱዳን ትሪብዩን ሲናገሩ የደቡብ ሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ ላይ አማጽያንን እን…ደሚመለምል፣ እንደሚያሰለጥንና እያስታጠቀ ወደጋምቤላ ክልል እንደሚልክ ገልጸዋል፡፡
ይህ በደቡብ ሱዳን መንግስት በመደራጀትና ወደኢትዮጵያ ጋምቤላ ገብቶ ጥቃት ለመሰንዘር በመንቀሳቀስ ላይ ያለ ሀይል በደርግ ዘመን የጋምቤላ አካባቢ አስተዳደር በነበሩትና እአአ በ1991 አገዛዙ ሲወድቅ ወደውጪ በሸሹት ሰው በቶዋት ፓል ቻይ መሪነት የሚንቀሳቀስ እንደሆነ አማጺያኑ ለሱዳን ትሪብዩን ተናግረዋል፡፡
ቶዋት ፓል ቻይ በጋምቤላ አገዛዝ ዘመናቸው ያኔ በጆን ጋራንግ ለሚመራውና አሁን ላይ በሳልቫኪር እየተመራ ደቡብ ሱዳንን ለሚያስተዳድረው የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጪ ጦር ድጋፍ በመስጠት የሚታወቁ ሰው ሲሆኑ ኋላ ለይ በስደት ዘመናቸውም ሳልቫ የተመቻቸ ሀላፊነትና መጠጊያ ሰጥተዋቸው እንደቆዩ ተወስቷል፡፡
The post የሳምንቱ አበይት ዜናዎችና ዳሰሳ በዴሲሶን ሬዲዮ ይቀርብላቸዋል appeared first on Zehabesha Amharic.