Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ቋሚ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን መመሪያ ተፈጻሚነት አግዷል * ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ፓትርያርኩን አሳሰቡ

$
0
0

abune-matyas
Source: ሐራ ዘተዋሕዶ

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ: ፓትርያርኩ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ሲሉ መዋቅራዊ አሠራርን በእጅጉ የሚፃረረውን አካሔዳቸውን እንዲያጤኑ አሳሰቧቸው፤ ቋሚ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን መመሪያ ተፈጻሚነት አግዷል::

•የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ፓትርያርኩ ከሕግ አግባብ ውጭ ለሾሟቸው ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች የምደባ ደብዳቤ እንደማይጽፉ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ አስታውቀዋል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አስተያየታቸውን በጽሑፍ እንዲያቀርቡ አዝዟቸዋል፡፡
•አሠራሩ፣ ምርጫው እና መመሪያው ተቀባይነት የሚኖረው ሥራ አስኪያጆቹ ‹‹በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ተመርጠው ቀርበው ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የጋራ ስምምነት ተደርሶበት በፓትርያርኩ ሲሾሙ ነው፡፡››

* * *

•‹‹ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ለፓትርያርክ ተጠሪ ኾኖ አያውቅም፤ ሊኾንም አይችልም፤ የሕግ ድጋፍ ስለሌለው፡፡ ይህ ያልተለመደ የሥራ ሒደት ብቻ ሳይኾን ከሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቃለ ዐዋዲው እና ከአገሪቱ የሕግ አሠራር ጭምር ውጭ ኾኖ ተመልክቸዋለኹ፡፡››
•‹‹የሥራ አስኪያጅ ምርጫው እና የተሰጠው መመሪያ ከትዝብት ላይ የሚጥል መኾኑን ተረድተውልን ለቤተ ክርስቲያን ሰላማዊ አሠራርና ለኹላችንም ሰላም ሲባል ውሳኔዎን እንደገና እንዲያጤኑት እያሳሰብኹ በተሰጠው መመሪያ እንዲኹም በሥራ አስኪያጅ ምርጫ የማልስማማና ለማስተናገድ የምቸገር መኾኔን ለቅዱስነትዎ ሳቀርብ በታላቅ ትሕትና ነው፡፡››

/ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፤ የከምባታ ሐዲያና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ለፓትርያርኩ ከጻፉትና ለቅዱስ ሲኖዶስ በግልባጭ ከአሳወቁት ደብዳቤ/

The post ቋሚ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን መመሪያ ተፈጻሚነት አግዷል * ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ፓትርያርኩን አሳሰቡ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>