በሕብረተሰባዊ የዕድገት ታሪክ ውስጥ ሴቶች ለነፃነት፣ እኩልነት፣ ለሰብኣዊ መብትና ፍትሕ መረጋገጥ የከፈሉትን መስዋእትነት ትልቅ ስፍራ ይዞ ይገኛል:: ይህ በመሆኑም ዘንድሮም እንደ ተለመደው በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገራችን መከበሩ የሚያሳየን የማርች 8 በዓል ታላቅነት ነው:: በሀገራችን የትግል ታሪክም በተመሳሳይ መልኩ ሴቶች ያልተሳተፉበት የነፃነት ትግል አልነበረም ቢባል የተጋነነ አይደለም:: የባዕዳን ሐይሎች ሀገራችንን በወረሩበት ጊዜም እቴጌ ጣይቱን ጨምሮ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሴቶች ዘማችና አዝማች በመሆንና ከወንዶች እኩል በመሰለፍ ለኢትዮያችን ህልውና ኩቡር መስዋእትነትን ከፈለው አልፏል:: በዘመናችንም የስርዓት ለውጥ ለማምጣት የተካሄደው ሁለ ገብ መራራ ትግልም የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል:: በዚሁ መራራ ትግልም እነ ማርታን ጨምሮ በሽዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች ሴቶች አኩሪ መስዋእትነትን ከፍለው አልፏል:: —[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—
The post ማርች 8’ትን ስናስታውስ – በላይ ገሠሠ appeared first on Zehabesha Amharic.