* የሳውዲ መንግስት ህገ ወጥ ያላቸውን የውጭ ዜጎች የማጥራቱንና የመያዙን ዘመቻ አጠናክሮ የቀጠለበት ሲሆን በእስካሁኑ አሰሳ 50,254 በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል
* መረጃውን ያስተላለፉት የመዲና ፖሊስ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ሃዲ አል ሸሃራኒ መሆናቸውን የጠቆሙት የሳውዲ ጋዜጦች ህገ ወጦች የተያዙት በዋና ከተማዋ በሪያድ በጅዳ ፣ በመካ ፣ በመዲና በተቡክ መሆኑን ጠቁመዋል። ባለስልጣኑ በማከልም የተያዙት ህገ ወጦች ማጣራት እየተደረገ እንደ ተጠረጠሩበት ወንጀል እንደሚከሰሱና ወደ ሃገራቸው እንደሚሸኙ አስታውቀዋል።
* ዘመቻው ከተጀመረ ወዲህ ሁከትና ግርግር ብዙም ባይስተዋልም በርካታ በውጭ ዜጎች የሚተዳደሩ ሱቆች የተዘጉ ሲሆን ሞቅ ደመቅ ያለውን የጅዳና የተለያዩ ከተሞች የገበያ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩ ይጠቀሳል። ምሽት ላይም የተለመደው የሞቀ እንቅስቃሴ የተገታ መሆኑ መስተዋሉ ይጠቀሳል ።
* በተለያዩ ምክንያቶች የመኖሪያ ፈቃዳቸው ጊዜ ሳይታደስ ስለወደቀባቸው የውጭ ዜጎች ጉዳይ የተናገሩት ጀዋዛት ተብሎ የሚታወቀው የሳውዲ የፓስፖርት እና ኢሚግሬሽን ዋና ኃላፊ መ.ጀኔራል ሱሌማን የህያ ፖስፖርታቸው በጊዜ ያላደሱት ፣ ስላላሳደሱበት በቂ ምክንያት እስካላቀረቡ ድረስ ከተያዙ ወደ ሀገራቸው እንደሚሸኙ ባሳለፍነው አርብ ማስታወቃቸው አይዘነጋም ።
* ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሰሳው ስጋት ያደረባቸው ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ እየሰጡ የሚሄዱበት መንገድ እንዲያመቻቹላቸው የጅዳን ቆንስልና በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ከሳውዲ መንግስት ጋር በመነጋገር መንገዱን ያስተከሰክሉ ዘንድ ተማጽኗቸውን እንዳሰማ በተለያየ መንገድ ጠይቀውኛል።
እነሆ መልዕክቱን አድርሻለሁ!
እነሆ መልዕክቱን አድርሻለሁ!
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 7 ቀን 2007 ዓም
መጋቢት 7 ቀን 2007 ዓም
The post (የሳውዲ ጉዳይ …) ህገ ወጦችን የማጥራት ዘመቻ ከተጀመረ 50,254 ተይዘዋል – ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.