<…የኢትዮጵያ ሕዝብ የአገዛዙን ዘረኛ ቅስቀሳ ቦታ መስጠት የለበትም እውነተኛ የሀይማኖት መሪዎችም በሀይማኖት ስም ስርዓቱ አንዱን ከሌላው የሚያደርገውን ማጋጨት ሊያወግዙ ይገባል ።ይህን ስል ግን በሀይማኖት ስም የተሸሸጉ የአገዛዙ ካድሬዎች…> ጋዜጠኛና አክቲቪሰት አበበ ገላው የኢትዮጵያው አገዛዝ በይስሙላው ምርቻ ቅስቀሳ ላይ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ስለሚፈጽመው ቅስቀሳ አስመልክቶ ተጠይቆ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<…የኢትዮጵያ ሕዝብ ተቻችሎ የኖረ የዘመናት ታሪክ ባለቤት ያለው በመሆኑ ህወሃቶች እድሜያቸውን ለማራዘም በሀይማኖትና በብሄር ለማጋጨት የሚያደርጉትን ሴራ ጠንቅቆ ያውቃል…በሀይማኖት ስም የተሸሸጉ ሀሰተኛ ካድሬ የሀይማኖት ወኪሎችን ሴራ ማወቅ ያስፈልጋል ዱርዬዎችን አንስተው የሙስሊሙ ወኪሎች ሲሉ በቅርቡ አይተናል…> ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በይስሙላው ምርጫ ወቅት ስለሚደረጉ የአገዛዙ ዘርን ከዘር ሀይማኖትን ከሀይማኖት የማጋጨት ሴራዎች ላይ አስቀድሞ ሊወሰድ ስለሚገባው ጥንቃቄ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<…የዘንድሮው ምርጫ ቅርጫ ለመሆንም አልቻለም…ኢህአዴግ ሁለቱን ምርኩዞቹን ጠመንጃውንና ምርጫ ቦርድን ይጣልና በአንድ ወር እኛ እናሸንፈዋለን…ፕ/ት ግርማ እንኳን ቤተ መንግስት ከመግባታቸው በፊት የእኛ ወዳጅ ነበሩ…> ዶ/ር መረራ ጉዲና ስለወቅታዊው የምርቻ ቅስቀሳ፣ ስለ ቀድሞው ፕ/ት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ወቅተቀዊ አስተያየት ጠይቀናቸው ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
ዶ/ር ቴዎድሮስን ጨምሮ እነ አዶልፍ ሒትለርም እንደሳቸው ከሚዋሹ ፖለቲከኞች መካከል ይጠቀሳል። ሌሎቹስ(ልዩ ጥንቅር ስለ ውሸታም ፖለቲከኞች)
ሌሎችም ዜናዎቻችን
የኢህአዴግ የደህንነት ሹም ደገሃቡር ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ሰሞኑን ተገደሉ
ከኢትዮጵያ የተነሳ የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን የአልሸባቡን መሪ መግደሉ ተነገረ
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ኢህአዴግ ስልጣኑን ማጣት እንደማይፈልግና የዘንድሮው ምርጫ ግራ የሚያጋባ መሆኑን ገለፁ
አሰብ የኢትዮጵያ ናት ልትመለስ ይገባል ብለዋል
ኢትዮጵአያ፣ግብጽና ሱዳን ካርቱም ላይ በአባይ ጉዳይ ሊፈራረሙ ነው
ግብፅ ከወዲሁ ኢትዮጵያ ከመጠን ያለፈ ውሃ ካከ
ማቸች ስጋቴ ዘላለማዊ ነው ስትል አስጠነቀቀች
በደቡብ ኦሞ አጠገብ የሚገኙ አርብቶ አደሮች በልማት ስም እየሞትን ነው አሉ
በኢትዮጵያ 2.9 ሚሊዮን ህዝብ በአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል ተባለ
ዶ/ር መራራ ጉዲና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመኖሩ ማስረጃ አምጡ በሚል ከአገዛዙ የኦሮምኛ ቋንቋ ቴሌቪዥን የምርጫ ክርክራቸው መታገዱን ገለጹ
ለውጥ ፈላጊው ለኢህአዴግ የከፋፍለህ ግዛ ትኩረት ሳይሰጥ በጋራ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል
አንድ የእንግሊዝ የፓርላማ አባል ኢትዮጵያ አወዛጋቢውን የባድመን አካባቢ ለኤርትራ እንድትሰጥ ጠየቁ
ኤርትራ በብሔራዊ ውትድርና ስልጣኖች ላይ የምታደርገው ጫና ለመቀነስ ማቀዷን ገለፀች
በፈርጉሰን ሁለቱን ፖሊሶች ገሏል የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
ሚሼል ኦባማን ዘረኛ ስድብ የተሳደበው ጋዜጠኛ ከስራ ተባረረ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
(ህብርን ከዘሐበሻ፣አፍሮ አዲስ ድህረ ገጾችእና በሌሎችም ያዳምጡ። በተጨማሪ በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)ነ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።
The post የህብር ሬዲዮ መጋቢት 6 ቀን 2007 ፕሮግራም – የኢህአዴግ የደህንነት ሹም ደገሃቡር ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ሰሞኑን ተገደሉ ከኢትዮጵያ የተነሳ የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን የአልሸባቡን መሪ መግደሉ ተነገረ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ኢህአዴግ ስልጣኑን ማጣት እንደማይፈልግና የዘንድሮው ምርጫ ግራ የሚያጋባ መሆኑን ገለፁ አሰብ የኢትዮጵያ ናት ልትመለስ ይገባል ብለዋል ኢትዮጵአያ፣ግብጽና ሱዳን ካርቱም ላይ በአባይ ጉዳይ ሊፈራረሙ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.