Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

መረብህን ጥለህ አዞ አወጣህ – (ለአቤቱ ኤርሚያስ ለገሰ) –ከመኳንንት ታዬ (ጸሃፊ)

$
0
0

daniel ermias

ሰሞኑን   ድህረ ገፅ አንዲት  ቁመት የሌላት ግን ሆዷ ሰፋ ያለ የምትመስል አብዛኛውን  የሆዷን ክፍል ከፊል ገለባ ከፊል ፍሬ የሞላባት እንደው ክንብል ክንብል  ስትል  እንደ ዘበት ተመለከትኳትና ፡አዬ ጉድ የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል” ምነው ኤርሚዬ ስል  እንደው እንደዘበት ቆየሁ።አፍታም አልከረመ ከወደ ዳንኤል አንዲት  መልክት መጣች ።”የለም  እንደገና ይታይልኝ “ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ነው” ነገሩ ስትል።መለሰና  አልተሳሳትኩም ያለው አቶ ኤርሚያስ  ስምህ ዳንኤል ስለነበር አለመተንበይህ  አስገርሞኝ ነው  የማለት ያህል መልስ ሰጠ።እንዴት  እሱስ ኤርሚያስ አልነበረም  ወይ  ቢሉ አንድም  ከወያኔ ጋር ስለነበረ በድርጅቱ መሰረት  መተንበይ አይቻልም።አንድም መተንበይ ቢቻል አስቀድሞ የወያኔ አባል አይሆንም ነበር ሲል።አንድም  ብቃቱ የተገለጠለት አሜሪካን ከመጣ ነው ሲል  ብቻ አንድም እያለ ይቀጥልና  መጨራሻው የመለስ ቱርፋት ላይ ቆመ ወይም  ይቀጥላል። ማለፊያ  ነው ።ለትንቢቱ ዳንኤል ይቀርብ ነበር  አደል  መፆም መፀለዩን  ያበዛ  ቢሉ፤ የለም ኢሃዲግ በሚያስተዳድረው ሃገር  መተንበይ ጨርሶ  ሐገሩን  ለቆ ወጥቶአልና ።ዳ/ን ዳኤንልም  መተንበያ  አለፈው።

በዚህ ምክንያት  እንዲህ  ሲል መልስ ሰጠ። ኩቡር የ አቶ ኤርሚያስ ፍርድ ቤት ሆይ” ጽሑፉ የቀረበው ነሐሴ 25 ቀን 1999 ዓም አሜሪካ፣ ዴንቨር ኮሎራዶ ከተማ ተደርጎ በነበረው ሰባተኛው የአሜሪካ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ነው፡፡ የተለቀቀው ደግሞ ከአንድ ወይም ከሁለት ቀን በኋላ www.tewahedo.org በተሰኘ ገጸ ድር ነው፡፡ –  በማለት ለኤርሚያስ    ለማስረዳት  እና ለመረዳት እየሞከረ ሳለ አቶ ኤርሚያስ  አንዴም ዳቆኑነቱን እያከበ ሌላም ግዜ ወጣ እያለ ብቻ ዘመቻውን ቀጥሎ ዋለ። እርግጥ ነው  ፖለቲካው በግዜውና በስፍራው መፍትሄ ይኖረዋል።  እርሱ ሁሉም በቦታውና በባለቤቱ ያምራልና  ፍራሹ  ከተመቸህ እንደፈለገህ የመሆን መብቱ የተጠበቀ ነው።የአቶ ኤርሚያስ ለገሰ። ግን እሰቲ በእይታ እንቀሳቀስ;፤ጥያቄ አንድ ።አቶ ኤርሚያስ  ስለምን የ1999 ዓ.ም ን ጥናታዊ  ፅሁፍ  ዛሬ ላይ  ቦታና ቀን ለውጦ አድማጭና  አስተያየት  ሰጪ ሆነ?አቶ ኤርሚያስ  በቤተክርስቲያንና በልጆቿ ስራ ዛሬም ያላለቀ  የቤት ስራ እንዳለውስ።ለምንስ ዳንኤል ላይ ማተኮር አስፈለገ።እንዴትስ  አንተ የምትመገበውን ያላገሳ ሁሉ ስሙን አተኩረህ ታየው የነበረው  የወያኔ አባል ሊሆን ቻለ።እኔ አንድ የቤተክርስቲያኒቱ ልጅ ነኝ ።በብዙ አውደ ምህረት ላይ በመገኘት ተምሬአለሁ።
daniel
ጥናታዊ ፅሁፎቹንም  ተካፍያለሁ;  የሚያቀውንና  መናገር  ያለበትን  እኔም የማውቀውን  የደበቀበት ወይም የአስተባበለበት ግዜ የለም ። ስለዚህ  በዛን ግዜ ተፈፅሞ ያልጠቀሰው  ነገር እንኳን  ቢኖር  ወይ ያላወቀው አልያም የዘነጋው ካልሆነ በስተቀር  ለማደር የሞከረበትን ግዜ አላየሁም። እውነት ነው  አሁን እየሞገትኩህ ያለሁት  ስለዳንኤል ክብረት  መስሎህ  ከሆነ  አሁንም  ችግር አለ ማለት ነው ።ከሱ በስተጀርባ ስላለችው ስለ ቤ/ክ ነው ።ይህ ማለት እሱ ባይኖር  ቤ/ክ  ችግር ይገጥማታል  እያልኩህ አደልም። እእ  ደረጃውን ለማፍረስ  መጀመሪያ ጠጠሮቹን  መፈንቀል የሚል  መመሪያ   ካለ ብዬ ነው ።ግን እንደመጠቅልል  አንተም ታስፈልገኛለህ ።ዳንኤልም  እንዲሁ ለኔ በግሌ ሁለታችሁም  አንድ ናችሁ።ታዲያሳ  ይህን  ፅሁፍ ለመፃፍ ምን አነሳሳህ አትለኝም?። ግን መልሱ አንተን  ተከትሎ እየመጡ ያሉ ሲያዩአቸው  አንበሳ  የሚመስሉ ግን አበላላቸው እንደ ጅብ የሆነ  እያረፉ የሚያስቡ  ስም የለሾች ናቸው ። አስቲ አንተ የምታውቀውን  ግን አንተ ካልከውም ሆነ ለዳ/ን ዳንኤል ክብረት ከፃፍከው ፅሁፍ ጋር ምንም ተዛማጅነት የሌላቸውን  ከዚህ በታች  ያለውን  ጥቂት ነጥቦች ላስነብብህና  የቆምክበትን ቦታ ለካ።ከዛ እንቀጥላለን። አንተ መረቡን ጥለህ አሳ ልታወጣ የኃሊት ዞረህ  ስትስብ በቅርብ ከነበሩት  አዞዎች  ውስጥ የፈጠኑት ወጡ።ለዚህ ማስረጃ ደግሞ ይህን ከዚህ በታች ያለውን ፅሁፍ ማንበብ ብቻ በቂ ነው ።

1.ምነው የትናንቱን የነአባ ማትያስን የማኅበረ ቅዱሳን ክስ አልነገርከንም ?
2.ትናንት በታቦት መውረጃ ምክንያት የባሕር
ዳርን ምእመናን ደማቸውን ያፈሰሱት ወሀቢያ ናቸው አንዳትለን እደራ እላለሁ ።
3.ገና በመጀምሪያው ምእተ ዓመት እመቤታችን የጎበኘቻት አገር ፥
ስለ እመቤታችን አማላጅነት እንደ ትልቅ አጀንዳ አዲስ አድርጎ ማቅረብ ምን ይሉታል ?
ቅዳሴ ማርያም የሚቀደስባት ቤተ ክርስቲያን ትለናለህ ፥ ይህ ነገር እንዴት ሊመጣ ቻለ ? ።
4.የወር አበባ ትምህርትስ ከየት መጣ ?
በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እልባት አግኝቶ ያለፈውን የሚበሉና የማይበሉ የምግብ
ጥያቄ በዚህ ዘመን ለምን ተነሣ ? ።
5. የወር አበባ ትምህርትስ ከየት መጣ ?
በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እልባት አግኝቶ ያለፈውን የሚበሉና የማይበሉ የምግብ
ጥያቄ በዚህ ዘመን ለምን ተነሣ ? ።

 
እንግዲህ  እነኚህ ነጥቦች ስታይ ነው  የመቼት ጥያቄውን እያሰብክ  ምናልባት መረብህን ጥለህ አዞ ማጥመድህ የሚገባህ።ዳ/ን ዳንኤል  አንድ ሰው ነው ።ነገር ግን ከሱ በስተጀርባ  ማን አለ ነው ።እርገጠኛ ነኝ  ማለት የምፈልገው ይገባሃል።ዘመኑ በአህያ ተከልልኦ ጅብን የመግደል ዘመቻ ያላበቃበት ነውና ጥንቃቄና አውቀትህን እንድትጠቀም  የግድ ይላል።እርግጥ ነው  ይህን ፅሁፍ  ለፃፈው ስም የሌሽ የምለው  ቢኖር “”የማታውቅበትን የሰው ጃኖ ለብሳ ተመለሺ ቢሏት በየት  ተመልሳ”” በቂ ነው ።ለቦና ጥጃ ውስ መች አነሰው” ብለዋልና አለቃ ገብርሃና።

አንተ ግን የእውቀት ሰውም ሰለሆንክ እራስን መጥቀም ተፈጥሮን ማየትና ለሌላው መኖር እእምሮአዊ ብቃት  ገንዘብ ከማድረግም በላይ በብልፅግና ውስጥ መኖር ያልተሰወረ ሚስጥር ማለት ሳይሆን ቋጠሮን ለመፍታት  መፍትሄ አልባ ችግርን ማስወገድና ቀዳሚነትን ታሳቢ አድረጎ ለነገ የሚያኖሩትን  ፍለጋ  የህሊናን ቋጥኝ  በጠራራ ሃሳብ  አዝልቆ ከመቆፈር ብሂል ጋር  የማገናኘትን እውነትን የራስ ከማድረግ  እኔነት ጋር የተዛመደ ነው። ግና ሽፍታ ሰፈር  ጎጆህን  ቀልሰህ  ከሆነ መለስ መለስ ብለህ ማየት ተፈጥሮ የምትነግር ህግ ስለሆነ የድርሻህን አለመስራትህን ትዝ የሚልህ  ሌሎች ድርሻ እንደሌለህ ሲነግሩህ ሳይሆን  አንተ ድርሻ የሌኝም ስትል  ብቻ ነው።በጥቅሉ እንደማሰሪያ  አቶ ኤርሚያስ ዳንኤል ባቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ምክንያት ተተርሰህ  ስለ አማራ አተኩረህ  አልፈሃል። ።አንተም ካማራና ከኦሮሞ ተወልደህ እንደማትሳደብ በሁለተኛዋ ግዜ ጠቆም ጠቆም አድርገሃል። ማለፊያ  ነው።ግን አትርሳ  ታምራት ላይኔ  ሃረር ሔዶ ሰርቶ አዳሪ የሆኑትን  ሆዳም አማራ ብሎ ወደ ገደል ሲያስወረወር እሱ አማራ ነበር። ተፈራ ዋልዋ አዲሱ ለገሰ ተመሳሳይ ጥፋት ሲፈፅሙ አማራ ናቸው።በቅርቡ አቶ አለምነህ  ፤”በባዶ እግሩ እየሔደ የሚናገረው መርዝ ነው” እያሉ ሲያንቋሽሸው እሱም አማራ ነው;”ስለዚህ  አካሔድ(በ ኢሃድግኛ) ችግር አለና ይስተካከል።በተረፈው  ምርጥ የኢትዮጲያ ልጅ ነህ እንደ አቤሚልክ ከ66 አመት በኋላም ብትነቃም።ዋናው በነቁ ግዜ ጥሩ እቃ መሆኑ ነው ቁም ነገሩ።ምነው  ወያኔዎች  ዛሬ ነቅተው  አለን ባሉን  መታደል ነበር ። ግን ምን ያደርጋል ከተኙ 40 አመት አከበሩ። ህዝቡ ደግሞ ከነቃ80 አመቱን አከበረና  ሳይተዋወቁ እየኖሩ ናቸው።

በትንሳኤ ውስጥ ጀግንንት ትርጉም ያገኛል።ሞራል የፍርሃትን ጉም ጥሶ ከፀሃይ ሙቀት ጋር ደባልቆ ጠል  ሆኖ ሁሉን ያረሰርሳል ።ዝናብ አደለምና አያበሰብስም ።ብርድ የለውምና አያንቀጠቅጥም።ህብረት  እንዲህ  ምቾት አለው።ትላንት ብቻህን ዛሬ ከእኛ ጋር ነህና  በርታ ለክተህ ቁረጥ።
 
ቸር እንሰንብት

The post መረብህን ጥለህ አዞ አወጣህ – (ለአቤቱ ኤርሚያስ ለገሰ) – ከመኳንንት ታዬ (ጸሃፊ) appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>