Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል?

$
0
0

back pain
የጀርባ ሕመም
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
የጀርባ ሕመም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተሰባችን ክፍል እያጠቃ የሚገኝ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ይህ ሕመም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የተለመደ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን በወጣትነት የዕድሜ ክልል ባሉ ሰዎች ላይም እየተበራከተ ይገኛል፡፡

► የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል?
የጀርባ ሕመም ከማንኛቸውም የሰው ጀርባን ከሚሰሩ የሰውንት ክፍሎች ሊነሳ ይችላል፡፡
እነዚህም፤
✔ የጀርባ ጡንቻዎች መሳሳብ (መሸማቀቅ)
✔ ከባድ ዕቃን ያለአግባብ ለማንሳት መሞከር
✔ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ እንቅስቃሴ
✔ የዲስክ መንሸራተት
✔ የመገጣጠሚያ ላይ ኢንፌክሽን
✔ የአጥንት መሳሳት

► የጀርባ ሕመም ከዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታችን ጋር ይያያዛል፡፡
✔ ከባድ ዕቃን በመግፋት ወይንም በመጎተት
✔ ከባድ ዕቃን በመሸከም ወይም በማንሳት
✔ ለብዙ ሰዓት በመቆም
✔ ለብዙ ሰዓታት አጎንብሶ መቀመጥ
✔ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት መኪና ማሽከርከር

► የጀርባ ሕመምን እንዴት መከላከል ይቻላል?
✔ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡- ኤሮቢክስ የሚባለውን የስፖርት ዓይነት መሥራት የሰውነታችንን አቅም ከመጨመር ባለፈ ክብደታችንን በመቀነስ የጀርባ ሕመም ይከላከላል፡፡
✔ ሲጋራ ማጤስን ማቆም፡- ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሲጋራን የሚያጤሱ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ለጀርባ ሕመም ተጋላጭ ናቸው፡፡
✔ የሰውንት ክብደት መቀነስ፡- የሰውነት ክብደታቸው የጨመረ ሰዎች የጀርባ ሕመም ይኖርባቸዋል፡፡
✔ የተስተካከለ አቀማመጥ፡- በምንቀመጥበት ጊዜ ጀርባችንን የሚደግፍ እና እጃችንን የምናሳርፍበት ቀጥ ያለ አቀማመጥ መያዝ፡፡
✔ የተስተካከለ አቋቋም፡- በምንቆምበት ጊዜ የሰውነት ክብደታችን በሁለቱም እግሮቻችን በእኩል መጠን እንዲያርፍ ማድርግ እና ቀጥ ብለን ሳንቆለመም መቆም፡፡
✔ ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በአግባቡ ማንሳት፡- ክብደት ያላቸውን በምናነሳበት ጊዜ ክብደቱን ከወገባችን/ከጀርባችን ይልቅ በእግሮቻችን ላይ እንዲያርፍ ማድርግ ተገቢ ነው፡፡ ዕቃዎችን በምናንቀሳቅስበት ጊዜ ከመጎተት ይልቅ መግፋትተመራጭ ነው፡፡
✔ ጫማ፡- የጀርባ ሕመም እንዳይሰማን የምንጫማቸው ጫማዎች ምቹ ሊሆኑ ይገባል፡፡
✔ መኪና በምንሽከረክርበት ወቅት ጀርባችንን መደገፍ፡፡ ለረጅም ሰዓት የምናሽከረክር ከሆነ በየማሃሉ ከመኪና በመውረድ ሰውነትን ማንሳሰቀስና ዕረፍት መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

✔ የአልጋ ፍራሽ ምቾት፡- የምንተኛበት የአልጋ ፍራሽ ቀጥ ያለ መሆን አለበት፡፡
የጀርባ ሕመም ከባድ የሆኑ የጤና ችግሮች ምልክት ሊሆን ስለሚችል በቀላሉ ሊመለከቱት አይገባም፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የሚጠቀሱት ተጫማሪ ምልክቶች ካሉ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡እነዚህም፤
✔ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ወይንም መውደቅን ተከትሎ የመጣ የጀርባ ሕመም
✔ ከወር በላይ የቆየ እና እየባሰ የመጣ የጀርባ ሕመም
✔ በሕመም ማስታገሻ እና ዕረፍት በመውሰድ ለውጥ የማያመጣ የጀርባ ሕመም
✔ ከወገብ በታች የመደንዘዝ ስሜት
✔ ደም የቀላቀለ ሽንት መኖር
✔ ከፍተኛ ትኩሳት መኖር እና ሆድ ሕመም መሰማት ናቸው፡፡
በቤቶ ሆነው ሊያከናውኑት የሚችሉትን ይህን ቀላል የ አካል ብቃት እንቅስቃሴ በዚህ አድራሻ ማግኘት ይችላል፡፡

ጤና ይስጥልኝ

The post Health: የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል? appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>